Read ኤርምያስ Chapter 8 Online
Read ኤርምያስ Chapter 8 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኤርምያስ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኤርምያስ and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
ኤርምያስ 8
ምዕራፍ 8
1. በዚያን ዘመን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የይሁዳን ነገሥታት አጥንትና የመኳንንቶቹን አጥንት፥ የካህናቱን አጥንትና የነቢያቱን አጥንት፥ የኢየሩሳሌምንም ሰዎች አጥንት ከመቃብራቸው ያወጣሉ።
2. በወደዱአቸውና ባመለኩአቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጉአቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጉአቸዋል፤ አያከማቹአቸውም አይቀብሩአቸውምም፥ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ።
3. እኔም ባሳደድኋቸው ስፍራ ሁሉ የቀሩ፥ ከዚህች ክፉ ወገን የተረፉ ቅሬታዎች ሁሉ፥ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ።
4. እንዲህም ትላቸዋለሁ። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። የወደቁ አይነሡምን? የሳተስ አይመለስምን?
5. እንግዲህ ይህ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ዘወትር ስለ ምን ወደ ኋላው ይመለሳል? ተንኰልን ይዞአል ሊመለስም እንቢ ብሎአል።
6. አደመጥሁ ሰማሁም፤ ቅንን ነገር አልተናገሩም፤ ማናቸውንም። ምን አድርጌአለሁ? ብሎ ከክፋቱ ንስሐ የገባ የለም፤ ወደ ሰልፍም እንደሚሮጥ ፈረስ እያንዳንዱ በየመንገዱ ይሄዳል።
7. ሽመላ በሰማይ ጊዜዋን አውቃለች፤ ዋኖስና ጨረባ ዋልያም የመምጣታቸውን ጊዜ ይጠብቃሉ፤ ሕዝቤ ግን የእግዚአብሔርን ፍርድ አላወቁም።
8. እናንተስ። ጥበበኞች ነን የእግዚአብሔርም ሕግ ከእኛ ጋር ነው እንዴት ትላላችሁ? እነሆ፥ የጸሐፊ ብርዕ ሐሰተኛ ነው በሐሰትም አድርጎአል።
9. ጥበበኞች አፍረዋል ደንግጠውማል ተማርከውማል፤ እነሆ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ጥለዋል፤ ምን ዓይነት ጥበብ አላቸው?
10. ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስትን ያስባሉና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ በተንኰል ያደርጋሉና ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች፥ እርሻቸውንም ለሚወርሱባቸው እሰጣለሁ።
11. የሕዝቤንም ሴት ልጅ ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ፤ ሰላም ሳይሆን። ስለም ሰላም ይላሉ።
12. አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፤ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል እግዚአብሔር
13. ፈጽሜ አጠፋችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በወይን ላይ ፍሬ፥ በበለስ ዛፍ ላይ በለስ አይሆንም፥ ቅጠልም ይረግፋል፤ የሚያልፉባቸውንም ሰጠኋቸው።
14. ዝም ብለን ለም እንቀመጣለን? እግዚአብሔርን ስለ በደልን አምላካችን እግዚአብሔር አጥፍቶናልና፥ የሐሞትንም ውኃ አጠጥቶናልና ተሰብስባችሁ ወደ ተመሸጉ ከተሞች እንግባ በዚያም እንጥፋ።
15. ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፥ መልካምም አልተገኘም፤ መጠገንን በተስፋ ተጠባበቅን፥ እነሆም፥ ድንጋጤ ሆነ።
16. የፈረሰኞቹ ድምጽ ከዳን ተሰማ፤ ከአርበኞች ፈረሶች ማሽካካት የተነሣ ምድር ሁሉ ተንቀጠቀጠች፤ መጡም ምድሪቱንና በእርስዋም ያለውን ሁሉ፥ ከተማይቱንና የተቀመጡባትንም በሉ።
17. እነሆ፥ አስማት የማይከለክላቸውን እባቦችንና እፉኝቶችን እሰድድባችኋለሁ፤ እነርሱም ይነድፉአችኋል።
18. ኅዘኔ የማይጽናና ነው፥ ልቤም በውስጤ ደክሞአል።
19. እነሆ። እግዚአብሔር በጽዮን የለምን? ወይስ ንጉሥዋ በእርስዋ ዘንድ የለምን? የሚል የወገኔ ሴት ልጅ ጩኸት ድምፅ ከሩቅ አገር ተሰማ። በተቀረጹ ምስሎቻቸውና በባዕድ ከንቱነትስ ያስቈጡኝ ስለ ምንድር ነው?
20. መከሩ አልፎአል፥ በጋው ሄዶአል፥ እኛም አልዳንነም።
21. በሕዝቤ ሴት ልጅ ስብራት እኔ ተሰብሬአለሁ ጠቍሬማለሁ፤ አድናቆትም ይዞኛል።
22. በገለዓድ የሚቀባ መድኃኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለምን? የወገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለ ምን አልሆነም?
About ኤርምያስ Chapter 8
Read ኤርምያስ Chapter 8 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኤርምያስ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: ኤርምያስ
Chapter: 8
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኤርምያስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading ኤርምያስ Chapter 8 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is ኤርምያስ Chapter 8?
ኤርምያስ Chapter 8 is part of the Book of ኤርምያስ in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete ኤርምያስ Chapter 8 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from ብሉይ ኪዳን
Explore More from ኤርምያስ
- ኤርምያስ Chapter 20
- ኤርምያስ Chapter 5
- ኤርምያስ Chapter 7
- ኤርምያስ Chapter 16
- ኤርምያስ Chapter 50
- ኤርምያስ Chapter 23
- ኤርምያስ Chapter 44