ዘሌዋውያን Chapter 20

For English

Read ዘሌዋውያን Chapter 20 Online

Read ዘሌዋውያን Chapter 20 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ዘሌዋውያን in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ዘሌዋውያን and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ዘሌዋውያን 20

ምዕራፍ 20

1. እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

2. ፤ ደግሞ የእስራኤልን ልጆች እንዲህ በላቸው። ከእስራኤል ልጆች ወይም በእስራኤል ዘንድ ከሚቀመጡ እንግዶች ማናቸውም ሰው ዘሩን ለሞሎክ ቢሰጥ ፈጽሞ ይገደል፤ የአገሩ ሕዝብ በድንጋይ ይውገረው።

3. ፤ መቅደሴን ያረክስ ዘንድ፥ የተቀደሰውንም ስሜን ያጐሰቍል ዘንድ ዘሩን ለሞሎክ ሰጥቶአልና እኔ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብዳለሁ፥ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።

4. ፤ ዘሩንም ለሞሎክ ሲሰጥ፥ የአገሩ ሕዝብ ያን ቸል ቢለው ባይገድሉትም፥

5. ፤ እኔ በዚያ ሰውና በቤተ ሰቡ ላይ ፊቴን አከብዳለሁ፤ እርሱንም፥ ከሞሎክም ጋር ያመነዝሩ ዘንድ የሚከተሉትን ሁሉ ከሕዝባቸው መካከል ለይቼ አጠፋለሁ።

6. ፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም በሚከተል፥ በሥራቸውም በሚያመነዝር፥ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብዳለሁ፥ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።

7. ፤ እንግዲህ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ሰውነታችሁን ቀድሱ፥ ቅዱሳንም ሁኑ።

8. ፤ ሥርዓቴን ጠብቁ፥ አድርጉትም፤ እኔ የምቀድሳችሁ እግዚአብሔር ነኝ።

9. ፤ ማናቸውም ሰው አባቱን ወይም እናቱን ቢሰድብ ፈጽሞ ይገደል፥ አባቱንና እናቱን ሰድቦአልና፤ ደሙ በራሱ ላይ ነው።

10. ፤ ማናቸውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ወይም ከባልንጀራው ሚስት ጋር ቢያመነዝር አመንዝራውና አመንዝራይቱ ፈጽመው ይገደሉ።

11. ፤ ማናቸውም ሰው ከአባቱ ሚስት ጋር ቢተኛ የአባቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ሁለቱ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው።

12. ፤ ማናቸውም ሰው ከምራቱ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ፈጽመው ይገደሉ፤ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ደማቸውም በላያቸው ነው።

13. ፤ ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው።

14. ፤ ማናቸውም ሰው እናቲቱንና ልጂቱን ቢያገባ ርኵሰት ነው፤ በመካከላችሁ ኃጢአት እንዳይሆን እርሱና እነርሱ በእሳት ይቃጠሉ።

15. ፤ ማናቸውም ሰው ከእንስሳ ጋር ቢገናኝ ፈጽሞ ይገደል፤ እንስሳይቱንም ግደሉአት።

16. ፤ ማናቸይቱም ሴት ወደ እንስሳ ብትቀርብ፥ ከእርሱም ጋር ብትገናኝ፥ ሴቲቱንና እንስሳውን ግደል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው።

17. ፤ ማናቸውም ሰው የአባቱን ልጅ ወይም የእናቱን ልጅ እኅቱን ቢያገባ፥ ኃፍረተ ሥጋዋንም ቢያይ፥ እርስዋም ኃፍረተ ሥጋውን ብታይ፥ ይህ ጸያፍ ነገር ነው፤ በሕዝባቸውም ልጆች ፊት ይገደሉ፤ የእኅቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአልና ኃጢአቱን ይሸከማል።

18. ፤ ማናቸውም ሰው ከባለ መርገም ሴት ጋር ቢተኛ ኃፍረተ ሥጋዋንም ቢገልጥ፥ ፈሳሽዋን ገልጦአልና፥ እርስዋም የደምዋን ፈሳሽ ገልጣለችና ሁለቱ ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ።

19. ፤ የአባትህን ወይም የእናትህን እኅት ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ ይህን የሚያደርግ የዘመድን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ።

20. ፤ ሰውም ከአጎቱ ሚስት ጋር ቢተኛ፥ የአጎቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ፤ ያለ ልጅ ይሞታሉ።

21. ፤ ሰውም የወንድሙን ሚስት ቢያገባ ርኵሰት ነው፤ የወንድሙን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ያለ ልጅ ይሆናሉ።

22. ፤ እንግዲህ ትቀመጡባት ዘንድ የማገባችሁ ምድር እንዳትተፋችሁ ሥርዓቴን ሁሉ፥ ፍርዴንም ሁሉ ጠብቁ፥ አድርጉትም።

23. ፤ ከፊታችሁ በምጥላቸውም ሕዝብ ወግ አትሂዱ፤ ይህን ሁሉ አድርገዋልና ተጸየፍኋቸው።

24. ፤ ነገር ግን እናንተን። ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ ትወርሱአትም ዘንድ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር እሰጣችኋለሁ አልኋችሁ። እኔ ከአሕዛብ የለየኋችሁ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ።

25. ፤ እንግዲህ ንጹሑን እንስሳ ከርኩሱ፥ ንጹሑንም ወፍ ከርኩስ ትለያላችሁ፤ ርኩሶች ናቸው ብዬ በለየኋቸው በእንስሳና በወፍ በምድርም ተንቀሳቃሽ ሁሉ ነፍሳችሁን አታርክሱ።

26. ፤ እኔ እግዚአብሔር ቅዱስ ነኝና፥ ለእኔም ትሆኑ ዘንድ ከአሕዛብ ለይቻችኋለሁና ቅዱሳን ትሆኑልኛላችሁ።

27. ፤ ሰው ወይም ሴት መናፍስትን ቢጠሩ ወይም ጠንቋዮች ቢሆኑ ፈጽመው ይገደሉ፤ በድንጋይ ይውገሩአቸው፤ ደማቸው በላያቸው ነው።

About ዘሌዋውያን Chapter 20

Read ዘሌዋውያን Chapter 20 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ዘሌዋውያን in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ዘሌዋውያን
Chapter: 20
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ዘሌዋውያን. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ዘሌዋውያን Chapter 20 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ዘሌዋውያን Chapter 20?

ዘሌዋውያን Chapter 20 is part of the Book of ዘሌዋውያን in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ዘሌዋውያን Chapter 20 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ብሉይ ኪዳን

  1. አሞጽ Chapter 4
  2. አሞጽ Chapter 1
  3. አሞጽ Chapter 3
  4. አሞጽ Chapter 6
  5. አሞጽ Chapter 2
  6. አሞጽ Chapter 7
  7. አሞጽ Chapter 5

Explore More from ዘሌዋውያን

  1. ዘሌዋውያን Chapter 17
  2. ዘሌዋውያን Chapter 25
  3. ዘሌዋውያን Chapter 10
  4. ዘሌዋውያን Chapter 3
  5. ዘሌዋውያን Chapter 23
  6. ዘሌዋውያን Chapter 16
  7. ዘሌዋውያን Chapter 27

Related Chapters & Readings

  1. ዳንኤል Chapter 5
  2. ዘፍጥረት Chapter 36
  3. ሉቃስ Chapter 4
  4. ዮሐንስ Chapter 20
  5. ማቴዎስ Chapter 10
  6. ዕብራውያን Chapter 6
  7. ዘሌዋውያን Chapter 4
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *