ኤርምያስ Chapter 15

For English

Read ኤርምያስ Chapter 15 Online

Read ኤርምያስ Chapter 15 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኤርምያስ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኤርምያስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ኤርምያስ 15

ምዕራፍ 15

1. እግዚአብሔርም እንደዚህ አለኝ። ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አይዘነብልም፤ ከፊቴ ጣላቸው፤ ይውጡ።

2. እነርሱም። ወዴት እንውጣ ቢሉህ፥ አንተ። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ለሞት የሆነ ወደ ሞት፥ ለሰይፍም የሆነ ወደ ሰይፍ፥ ለራብም የሆነ ወደ ራብ፥ ለምርኮም የሆነ ወደ ምርኮ ትላቸዋለህ።

3. ሰይፍን ለመግደል ውሾችንም ለመጐተት የሰማያትንም ወፎች የምድርንም አራዊት ለመብላትና ለማጥፋት፥ አራቱን ዓይነት ጥፋት አዝዝባቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

4. የይሁዳም ንጉሥ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በኢየሩሳሌም ስላደረገው ሁሉ በምድር መንግሥታት ሁሉ መካከል ለመከራ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።

5. ኢየሩሳሌም ሆይ፥ የሚራራልሽ ማን ነው? የሚያዝንልሽስ ማን ነው? ወይስ ስለ ደኅንነትሽ ይጠይቅ ዘንድ ፈቀቅ የሚል ማነ ነው?

6. አንቺ እኔን ጥለሻል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ወደ ኋላሽም ተመልሰሻል፤ ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቼ አጥፍቼሻለሁ፤ ከይቅርታ ደክሜአለሁ።

7. በአገርም ደጆች ውስጥ በመንሽ አበጥሬአቸዋለሁ፤ የወላድ መካን አድርጌአቸዋለሁ፥ ሕዝቤንም አጥፍቼአለሁ፤ ከመንገዳቸውም አልተመለሱም።

8. መበለቶቻቸውም ከባሕር አሸዋ ይልቅ በዝተውብኛል፤ በብላቴኖች እናት ላይ በቀትር ጊዜ አጥፊውን አምጥቻለሁ፤ ጣርንና ድንጋጤን በድንገት አምጥቼባታለሁ።

9. ሰባት የወለደች ደክማለች፥ ነፍስዋንም አውጥታለች፤ ቀን ገና ሳለ ፀሐይዋ ገብታባታለች፤ አፍራለች ተዋርዳማለች፤ የተረፉትንም በጠላቶቻቸው ፊት ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣለሁ።

10. እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምድር ሁሉ የክርክርና የጥል ሰው የሆንሁትን ወለድሽኝ ለማንም አላበደርሁም፥ ማንም ለእኔ አላበደረም፥ ነገር ግን ሁሉ ይረግመኛል።

11. እግዚአብሔር እንዲህ አለ። በእውነት ለደኅንነትህ አጸናሃለሁ፤ በእውነት በመከራና በጭንቅ ጊዜ ጠላትህ እንዲለምንህ አደርገዋለሁ።

12. በውኑ ብረትን፥ የሰሜንን ብረት፥ ናስንም የሚሰብር አለን?

13. በዳርቻህ ሁሉ ስላለ ኃጢአትህ ሁሉ ባለጠግነትህንና መዝገብህን ለመበዝበዝ በከንቱ እሰጣለሁ።

14. የምታቃጥላችሁ እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና ከጠላቶችህ ጋር ወደማታውቀው ምድር አሳልፍሃለሁ።

15. አቤቱ፥ አንተ ታውቃለህ፤ አስበኝ ጐብኘኝም የሚያሳድዱኝንም ተበቀላቸው እንጂ አትታገሣቸው፤ ስለ አንተ ስድብን እንደ ታገሥሁ እወቅ።

16. ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ፤ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ።

17. በዋዘኞችና በደስተኞች ጉባኤ አልተቀመጥሁም፤ ቍጣን ሞልተህብኛልና በእጅህ ፊት ለብቻዬ ተቀመጥሁ።

18. ስለ ምን ሕመሜ አዘወተረኝ? ቍስሌስ ስለ ምን የማይፈወስ ሆነ? ስለ ምንስ። አልሽርም አለ? በውኑ እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃ ትሆነኛለህን?

19. ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ብትመለስ እመልስሃለሁ በፊቴም ትቆማለህ፤ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፥ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም።

20. ለዚህም ሕዝብ የተመሸገ የናስ ቅጥር አደርግሃለሁ፤ ይዋጉሃል እኔ ግን ለማዳን ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም።

21. ከክፉ ሰዎችም እጅ እታደግሃለሁ፥ ከጨካኞችም ጡጫ እቤዥሃለሁ።

About ኤርምያስ Chapter 15

Read ኤርምያስ Chapter 15 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኤርምያስ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ኤርምያስ
Chapter: 15
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኤርምያስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ኤርምያስ Chapter 15 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ኤርምያስ Chapter 15?

ኤርምያስ Chapter 15 is part of the Book of ኤርምያስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ኤርምያስ Chapter 15 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ብሉይ ኪዳን

  1. አሞጽ Chapter 4
  2. አሞጽ Chapter 1
  3. አሞጽ Chapter 3
  4. አሞጽ Chapter 6
  5. አሞጽ Chapter 2
  6. አሞጽ Chapter 7
  7. አሞጽ Chapter 5

Explore More from ኤርምያስ

  1. ኤርምያስ Chapter 25
  2. ኤርምያስ Chapter 5
  3. ኤርምያስ Chapter 49
  4. ኤርምያስ Chapter 39
  5. ኤርምያስ Chapter 13
  6. ኤርምያስ Chapter 27
  7. ኤርምያስ Chapter 20

Related Chapters & Readings

  1. 1 ሳሙኤል Chapter 4
  2. ኢሳይያስ Chapter 38
  3. ኤርምያስ Chapter 39
  4. መኃልየ መኃልይ Chapter 2
  5. ዮናስ Chapter 4
  6. 2 ዜና መዋዕል Chapter 2
  7. ዘፍጥረት Chapter 7
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *