ኢዮብ Chapter 9

For English

Read ኢዮብ Chapter 9 Online

Read ኢዮብ Chapter 9 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኢዮብ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

A+ A A-

ኢዮብ 9

ምዕራፍ 9

1. ኢዮብም መለሰ እንዲህም አለ።

2. ፤ በእውነት እንዲህ እንደ ሆነ አወቅሁ፤ ሰውስ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ መሆን እንዴት ይችላል?

3. ፤ ከእርሱ ጋር ይከራከር ዘንድ ቢወድድ፥ ከሺህ ነገር አንዱን መመለስ አይችልም።

4. ፤ ልቡ ጠቢብ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፤ ደፍሮትስ በደኅና የሄደ ማን ነው?

5. ፤ ተራሮችን ይነቅላል፤ አያውቁትም፤ በቍጣውም ይገለብጣቸዋል።

6. ፤ ምድርን ከስፍራው ያናውጣታል፥ ምሰሶችዋም ይንቀጠቀጣሉ።

7. ፤ ፀሐይን ያዝዛታል፥ አትወጣምም፤ ከዋክብትንም ያትማል።

8. ፤ ሰማያትን ብቻውን ይዘረጋል፥ በባሕሩም ማዕበል ላይ ይረግጣል።

9. ፤ ድብ የሚባለውን ኮከብና ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ፥ ሰባቱንም ከዋክብት፥ በደቡብም በኩል ያሉትን የከዋክብት ማደርያዎች ሠርቶአል።

10. ፤ የማይመረመረውን ታላላቅ ነገር፥ የማይቈጠረውንም ተአምራት ያደርጋል።

11. ፤ እነሆ፥ ቢመጣብኝ አላየውም፤ ቢያልፍብኝም አላውቀውም።

12. ፤ እነሆ፥ ፈጥኖ ቢነጥቅ የሚከለክለው ማን ነው? እርሱንስ። ምን ታደርጋለህ? የሚለው ማን ነው?

13. ፤ እግዚአብሔር ቍጣውን አይመልስም፤ ከእርሱ በታች ረዓብን የሚረዱ ይዋረዳሉ።

14. ፤ ይልቁንስ እመልስለት ዘንድ፥ ቃሌንስ በፊቱ እመርጥ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?

15. ፤ ጻድቅ ብሆን ኖሮ አልመልስለትም ነበር፤ ወደ ፈራጄም እለምን ነበር።

16. ፤ ብጠራው እርሱም ቢመልስልኝ ኖሮ፥ ቃሌን እንደ ሰማ አላምንም ነበር።

17. ፤ በዐውሎ ነፋስ ይሰብረኛል፥ ቍስሌንም ያለ ምክንያት ያበዛል።

18. ፤ እተነፍስ ዘንድ አይተወኝም፥ ነገር ግን መራራን ነገር አጥግቦኛል።

19. ፤ የኃይል ነገር ቢሆን እርሱ ኃያል ነው፤ የፍርድ ነገር ቢሆን። ጊዜን ወሳኙ ማን ነው? ይላል።

20. ፤ ጻድቅ ብሆን አፌ ይወቅሰኛል፤ ፍጹምም ብሆን ጠማማ ያደርገኛል።

21. ፤ ፍጹም ነኝ ራሴንም አልመለከትም፤ ሕይወቴንም እንቃታለሁ።

22. ፤ ይህ ሁሉ አንድ ነው፤ ስለዚህ። ፍጹማንንና ክፉዎችን ያጠፋል እላለሁ።

23. ፤ መቅሠፍቱ ፈጥኖ ቢገድል፥ በንጹሐን ፈተና ይሳለቃል።

24. ፤ ምድር በኃጥአን እጅ ተሰጥታለች፤ የፈራጆችዋን ፊት ሸፍኖአል፤ እርሱ ካልሆነ ማን ነው?

25. ፤ ዘመኔ ከሚሮጥ ሰው ይልቅ ይፈጥናል፤ ይሸሻል፥ መልካምንም አያይም።

26. ፤ የደንገል ታንኳ እንደሚፈጥን፥ ንስርም ወደ ንጥቂያው እንደሚበርር ያልፋል።

27. ፤ እኔ። የኀዘን እንጕርጕሮዬን እረሳለሁ፤ ፊቴን መልሼ እጽናናለሁ ብል፥

28. ፤ ንጹሕ እንደማታደርገኝ እኔ አውቃለሁና ከመከራዬ ሁሉ እፈራለሁ።

29. ፤ በደለኛ እንደሚሆን ሰው እሆናለሁ፤ ስለ ምንስ በከንቱ እደክማለሁ?

30. ፤ በአመዳይ ውስጥ ብታጠብ፥ እጆቼንም እጅግ ባነጻ፥

31. ፤ በአዘቅት ውስጥ ታሰጥመኛለህ፥ ልብሴም ይጸየፈኛል።

32. ፤ እንድመልስለት አብረን ወደ ፍርድ እንገባ ዘንድ፥ እርሱ እንደ እኔ ሰው አይደለም።

33. ፤ እጁን በሁለታችን ላይ የሚያኖር ዳኛ በመካከላችን ምነው በተገኘ!

34. ፤ በትሩን ከእኔ ላይ ያርቅ፥ ግርማውም አያስፈራኝ፤

35. ፤ እናገርም ነበር፥ አልፈራውምም ነበር፤ በራሴ እንዲህ አይደለሁምና።

About ኢዮብ Chapter 9

Read ኢዮብ Chapter 9 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ኢዮብ
Chapter: 9
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኢዮብ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ኢዮብ Chapter 9 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ኢዮብ Chapter 9?

ኢዮብ Chapter 9 is part of the Book of ኢዮብ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ኢዮብ Chapter 9 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ብሉይ ኪዳን

  1. አሞጽ Chapter 4
  2. አሞጽ Chapter 1
  3. አሞጽ Chapter 3
  4. አሞጽ Chapter 6
  5. አሞጽ Chapter 2
  6. አሞጽ Chapter 7
  7. አሞጽ Chapter 5

Explore More from ኢዮብ

  1. ኢዮብ Chapter 21
  2. ኢዮብ Chapter 1
  3. ኢዮብ Chapter 3
  4. ኢዮብ Chapter 24
  5. ኢዮብ Chapter 5
  6. ኢዮብ Chapter 29
  7. ኢዮብ Chapter 12

Related Chapters & Readings

  1. ዘኍልቍ Chapter 29
  2. ኢዮብ Chapter 8
  3. 1 ዜና መዋዕል Chapter 7
  4. 2 ተሰሎንቄ Chapter 1
  5. 2 ዜና መዋዕል Chapter 15
  6. ዘፍጥረት Chapter 27
  7. ዕብራውያን Chapter 5
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *