ቆላስይስ Chapter 3

For English

Read ቆላስይስ Chapter 3 Online

Read ቆላስይስ Chapter 3 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ቆላስይስ in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ቆላስይስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ቆላስይስ 3

ምዕራፍ 3

1. እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ።

2. በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም።

3. ሞታችኋልና፥ ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና።

4. ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ።

5. እንግዲህ በምድር ያሉቱን ብልቶቻችሁን ግደሉ፥ እነዚህም ዝሙትና ርኵሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣኦትንም ማምለክ የሆነ መጎምጀት ነው።

6. በእነዚህም ጠንቅ የእግዚአብሔር ቍጣ በማይታዘዙ ልጆች ላይ ይመጣል።

7. እናንተም ደግሞ ትኖሩባቸው በነበራችሁ ጊዜ፥ በፊት በእነዚህ ተመላለሳችሁ።

8. አሁን ግን እናንተ ደግሞ ቍጣንና ንዴትን ክፋትንም፥ ከአፋችሁም ስድብን የሚያሳፍርንም ንግግር እነዚህን ሁሉ አስወግዱ።

9. እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ፥ አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር ገፋችሁታልና፥

10. የፈጠረውንም ምሳሌ እንዲመስል እውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል።

11. በዚያም የግሪክ ሰው አይሁዳዊም የተገረዘም ያልተገረዘም አረማዊም እስኩቴስም ባሪያም ጨዋ ሰውም መሆን አልተቻለም፥ ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉ ነው፥ በሁሉም ነው።

12. እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ፥ ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትህትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ።

13. እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ። ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ።

14. በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነውን ፍቅርን ልበሱት።

15. በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ። የምታመሰግኑም ሁኑ።

16. የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ። በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገሥጹ። በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።

17. እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።

18. ሚስቶች ሆይ፥ በጌታ እንደሚገባ ለባሎቻችሁ ተገዙ።

19. ባሎች ሆይ፥ ሚስቶቻችሁን ውደዱ መራራም አትሁኑባቸው።

20. ልጆች ሆይ፥ ይህ ለጌታ ደስ የሚያሰኝ ነውና በሁሉ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ።

21. አባቶች ሆይ፥ ልባቸው እንዳይዝል ልጆቻችሁን አታበሳጩአቸው።

22. ባሪያዎች ሆይ፥ በቅን ልብ ጌታን እየፈራችሁ እንጂ፥ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ ሳትሆኑ፥ በሥጋ ጌቶቻችሁ ለሆኑ በሁሉ ታዘዙ።

23. ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥

24. ከጌታ የርስትን ብድራት እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና። የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና።

25. የሚበድልም የበደለውን በብድራት ይቀበላል፥ ለሰው ፊትም አድልዎ የለም።

About ቆላስይስ Chapter 3

Read ቆላስይስ Chapter 3 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ቆላስይስ in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ቆላስይስ
Chapter: 3
Testament: New Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ቆላስይስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ቆላስይስ Chapter 3 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ቆላስይስ Chapter 3?

ቆላስይስ Chapter 3 is part of the Book of ቆላስይስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ቆላስይስ Chapter 3 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ቆላስይስ

  1. ቆላስይስ Chapter 1
  2. ቆላስይስ Chapter 4
  3. ቆላስይስ Chapter 2

Explore More from አዲስ ኪዳን

  1. 1 ጢሞቴዎስ Chapter 3
  2. ማርቆስ Chapter 5
  3. ማቴዎስ Chapter 19
  4. ማቴዎስ Chapter 24
  5. ገላትያ Chapter 2
  6. ፊልጵስዩስ Chapter 3
  7. ሮሜ Chapter 4

Related Chapters & Readings

  1. 2 ዜና መዋዕል Chapter 34
  2. 2 ሳሙኤል Chapter 4
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 104
  4. ዕብራውያን Chapter 11
  5. ኢዮብ Chapter 41
  6. አስቴር Chapter 10
  7. ኢሳይያስ Chapter 58
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *