ኢዮብ Chapter 36

For English

Read ኢዮብ Chapter 36 Online

Read ኢዮብ Chapter 36 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኢዮብ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ኢዮብ 36

ምዕራፍ 36

1. ኤሊሁም ደግሞ መለሰ እንዲህም አለ።

2. ፤ ገና ስለ እግዚአብሔር የሚነገር አለኝና ጥቂት ቆየኝ፥ እኔም አስታውቅሃለሁ።

3. ፤ እውቀቴን ከሩቅ አመጣለሁ፥ ፈጣሪዬንም። ጻድቅ ነው እላለሁ።

4. ፤ ቃሌ በእውነት ያለ ሐሰት ነው፤ በእውቀትም ፍጹም የሆነ ከአንተ ጋር አለ።

5. ፤ እነሆ፥ እግዚአብሔር ኃያል ነው፥ ማንንም አይንቅም፤ እርሱም በማስተዋል ብርታት ኃያል ነው።

6. ፤ እርሱ የበደለኞችን ሕይወት አያድንም፤ ለችግረኞች ግን ፍርዱን ይሰጣል።

7. ፤ ዓይኑን ከጻድቃን ላይ አያርቅም፤ ለዘላለምም ከነገሥታት ጋር በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል፥ እነርሱም ከፍ ከፍ ይላሉ።

8. ፤ በሰንሰለት ቢታሰሩ፥ ወይም በችግር ገመድ ቢጠመዱ፥

9. ፤ ሥራቸውንና መተላለፋቸውን በትዕቢትም እንዳደረጉ ይናገራቸዋል።

10. ፤ ጆሮአቸውን ለተግሣጽ ይከፍተዋል፥ ከኃጢአትም ይመለሱ ዘንድ ያዝዛቸዋል።

11. ፤ ቢሰሙ ቢያገለግሉትም፥ ዕድሜአቸውን በልማት፥ ዘመናቸውንም በተድላ ይፈጽማሉ።

12. ፤ ባይሰሙ ግን በሰይፍ ይጠፋሉ፥ ያለ እውቀትም ይሞታሉ።

13. ፤ ዝንጉዎች ግን ቍጣን ያዘጋጃሉ፤ እርሱም ባሰራቸው ጊዜ አይጮኹም።

14. ፤ በሕፃንነታቸው ሳሉ ይሞታሉ፥ ሕይወታቸውም በሰዶማውያን መካከል ይጠፋል።

15. ፤ የተቸገረውን በችግሩ ያድነዋል፤ በመከራም ጆሮአቸውን ይገልጣል።

16. ፤ እንዲሁም አንተን ከመከራ ችግር ወደሌለበት ወደ ሰፊ ስፍራ በወሰደህ ነበር፥ በማዕድህ ላይ የተዘጋጀውም ስብ በሞላበት ነበር።

17. ፤ አንተ ግን በበደለኞች ፍርድ የተሞላህ ነህ፤ ስለዚህ ፍርድና ብይን ይይዝሃል።

18. ፤ ቍጣ ለስድብ አያታልልህ፤ የማማለጃም ብዛት ፈቀቅ አያድርግህ።

19. ፤ ባለጠግነትህ የኃይልህም ብርታት ሁሉ ያለ ችግር እንድትሆን ሊረዳህ ይችላልን?

20. ፤ ወገኖች ከስፍራቸው የሚወጡበትን ሌሊት አትመኝ።

21. ፤ ከመከራ ይልቅ ይህን መርጠሃልና ኃጢአትን እንዳትመለከት ተጠንቀቅ።

22. ፤ እነሆ፥ እግዚአብሔር በኃይሉ ከፍ ያለውን ነገር ያደርጋል፤ እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማን ነው?

23. ፤ መንገዱን ማን አዘዘለት? ወይስ። ኃጢአትን ሠርተሃል የሚለው ማን ነው?

24. ፤ ሰዎች የዘመሩትን ሥራውን ታከብር ዘንድ አስብ።

25. ፤ ሰዎች ሁሉ ተመልክተውታል፤ ሰውም ከሩቅ ያየዋል።

26. ፤ እነሆ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም። የዘመኑም ቍጥር አይመረመርም።

27. ፤ የውኃውን ነጠብጣብ ወደ ላይ ይስባል፥ ዝናብም ከጉም ይንጠባጠባል፤

28. ፤ ደመናት ያዘንባሉ፥ በሰዎችም ላይ በብዙ ያንጠባጥባሉ።

29. ፤ የደመናውንም መዘርጋት፥ የማደሪያውንም ነጐድጓድ የሚያስተውል ማን ነው?

30. ፤ እነሆ፥ በዙሪያው ብርሃኑን ይዘረጋል፤ የባሕሩንም ጥልቀት ይከድናል።

31. ፤ በእነዚህ በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል፤ ብዙም ምግብ ይሰጣል።

32. ፤ እጆቹን በብርሃን ይሰውራል፥ በጠላቱም ላይ ይወጣ ዘንድ ያዝዘዋል፤

33. ፤ የነጐድጓድ ድምፅ ስለ እርሱ ይናገራል፤ እንስሶችም ደግሞ ስለሚመጣው ውሽንፍር ይጮኻሉ።

About ኢዮብ Chapter 36

Read ኢዮብ Chapter 36 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ኢዮብ
Chapter: 36
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኢዮብ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ኢዮብ Chapter 36 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ኢዮብ Chapter 36?

ኢዮብ Chapter 36 is part of the Book of ኢዮብ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ኢዮብ Chapter 36 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ብሉይ ኪዳን

  1. አሞጽ Chapter 4
  2. አሞጽ Chapter 1
  3. አሞጽ Chapter 3
  4. አሞጽ Chapter 6
  5. አሞጽ Chapter 2
  6. አሞጽ Chapter 7
  7. አሞጽ Chapter 5

Explore More from ኢዮብ

  1. ኢዮብ Chapter 1
  2. ኢዮብ Chapter 3
  3. ኢዮብ Chapter 28
  4. ኢዮብ Chapter 8
  5. ኢዮብ Chapter 13
  6. ኢዮብ Chapter 6
  7. ኢዮብ Chapter 17

Related Chapters & Readings

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 117
  2. 1 ሳሙኤል Chapter 20
  3. ሩት Chapter 1
  4. 1 ዜና መዋዕል Chapter 5
  5. ዘካርያስ Chapter 12
  6. የሐዋርያት ሥራ Chapter 13
  7. ኤርምያስ Chapter 33
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *