Read 1 ዜና መዋዕል Chapter 24 Online
Read 1 ዜና መዋዕል Chapter 24 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ዜና መዋዕል in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 1 ዜና መዋዕል and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
1 ዜና መዋዕል 24
ምዕራፍ 24
1. የአሮንም ልጆች ሰሞን ይህ ነው። የአሮን ልጆች ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር ነበሩ።
2. ፤ ናዳብና አብዩድ ግን ልጆች ሳይወልዱ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፤ አልዓዛርና ኢታምርም ካህናት ሆኑ።
3. ፤ ዳዊትም ከአልዓዛር ልጆች ከሳዶቅ ጋር፥ ከኢታምርም ልጆች ከአቢሜሌክ ጋር ሆኖ እንደ አገልግሎታቸው ሥርዓት ከፍሎ መደባቸው።
4. ፤ የአልዓዛርም ልጆች አለቆች ከኢታምርም ልጆች አለቆች በልጠው ተገኙ፤ እንዲህም ተመደቡ፤ ከአልዓዛር ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች አሥራ ስድስት፥ ከኢታምርም ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ስምንት አለቆች ነበሩ።
5. ፤ ከአልዓዛርና ከኢታምርም ልጆች መካከል የመቅደሱና የእግዚአብሔር አለቆች ነበሩና እነዚህና እነዚያ እንዲህ በዕጣ ተመደቡ።
6. ፤ ከሌዋውያንም ወገን የነበረው የናትናኤል ልጅ ጸሐፊው ሸማያ በንጉሡና በአለቆቹ ፊት፥ በካህኑ በሳዶቅና በአብያታርም ልጅ በአቢሜሌክ ፊት፥ በካህናቱና በሌዋውያኑ አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት ጻፋቸው፤ አንዱንም የአባት ቤት ለአልዓዛር፥ አንዱንም ለኢታምር ጻፈ።
7. ፤ መጀመሪያውም ዕጣ ለዮአሪብ ወጣ፥ ሁለተኛው ለዮዳኤ፥
8. ፤ ሦስተኛው ለካሪም፥
9. ፤ አራተኛው ለሥዖሪም፥ አምስተኛው ለመልክያ፥
10. ፤ ስድስተኛው ለሚያሚን፥ ሰባተኛው ለአቆስ፥
11. ፤ ስምንተኛው ለአብያ፥ ዘጠኝኛው ለኢያሱ፥
12. ፤ አሥረኛው ለሴኬንያ፥ አሥራ አንደኛው ለኤልያሴብ፥ አሥራ ሁለተኛው ለያቂም፥
13. ፤ አሥራ ሦስተኛው ለኦፓ፥ አሥራ አራተኛው ለየሼብአብ፥
14. ፤ አሥራ አምስተኛው ለቢልጋ፥ አሥራ ስድስተኛው ለኢሜር፥
15. ፤ አሥራ ሰባተኛው ለኤዚር፥ አሥራ ስምንተኛው ለሃፊጼጽ፥
16. ፤ አሥራ ዘጠኝኛው ለፈታያ፥
17. ፤ ሀያኛው ለኤዜቄል፥ ሀያ አንደኛው ለያኪን፥ ሀያ ሁለተኛው ለጋሙል፥
18. ፤ ሀያ ሦስተኛው ለድላያ፥ ሀያ አራተኛው ለመዓዝያ።
19. ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ አባታቸው አሮን እንደ ሰጣቸው ሥርዓት ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚገቡበት የአገልግሎታቸው ሥርዓት ይህ ነበረ።
20. ፤ ከቀሩትም የሌዊ ልጆች፤ ከእንበረም ልጆች ሱባኤል፤ ከሱባኤል ልጆች ዬሕድያ፤
21. ፤
22. ፤ ከረዓብያ ልጆች አለቃው ይሺያ፤ ከይስዓራውያን ሰሎሚት፤ ከሰሎሚት ልጆች ያሐት፤
23. ፤ ከኬብሮንም ልጆች አለቃው ይሪያ፥ ሁለተኛው አማርያ፥ ሦስተኛው የሕዚኤል፥ አራተኛው ይቀምዓም፤
24. ፤ የዑዝኤል ልጅ ሚካ፤
25. ፤ የሚካ ልጅ ሻሚር፤ የሚካ ወንድም ይሺያ፤
26. ፤ ከይሺያ ልጆች ዘካርያስ፤ የሜራሪ ልጆች ሞሖሊ፥ ሙሲ፤ ከያዝያ ልጅ በኖ፤
27. ፤ የሜራሪ ልጆች፤ ከያዝያ በኖ፥ ሾሃም፥ ዘኩር፥ ዔብሪ፤
28. ፤ ከሞሖሊ አልዓዛር፥ እርሱም ልጆች አልነበሩት፤
29. ፤ ከቂስ፤ የቂስ ልጅ ይረሕምኤል፤ የሙሲም ልጆች፤ ሞሖሊ፥ ዔዳር፥ ኢያሪሙት።
30. ፤ እነዚህ እንደ አባቶቻቸው ቤቶች የሌዋውያን ልጆች ነበሩ።
31. ፤ እነዚህም ደግሞ በንጉሡ በዳዊትና በሳዶቅ በአቢሜሌክም በሌዋውያንና በካህናት አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት፥ ታላቁም እንደ ታናሹ፥ እንደ ወንድሞቻቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣጣሉ።
About 1 ዜና መዋዕል Chapter 24
Read 1 ዜና መዋዕል Chapter 24 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ዜና መዋዕል in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: 1 ዜና መዋዕል
Chapter: 24
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 1 ዜና መዋዕል. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading 1 ዜና መዋዕል Chapter 24 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is 1 ዜና መዋዕል Chapter 24?
1 ዜና መዋዕል Chapter 24 is part of the Book of 1 ዜና መዋዕል in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete 1 ዜና መዋዕል Chapter 24 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from 1-ዜና-መዋዕል
- 1 ዜና መዋዕል Chapter 2
- 1 ዜና መዋዕል Chapter 13
- 1 ዜና መዋዕል Chapter 3
- 1 ዜና መዋዕል Chapter 15
- 1 ዜና መዋዕል Chapter 29
- 1 ዜና መዋዕል Chapter 27
- 1 ዜና መዋዕል Chapter 25
Explore More from ብሉይ ኪዳን
- ኢያሱ Chapter 8
- 2 ሳሙኤል Chapter 15
- ኢያሱ Chapter 22
- ዘጸአት Chapter 29
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 34
- ኤርምያስ Chapter 11
- ኢዮብ Chapter 8