1 ዜና መዋዕል Chapter 10

For English

Read 1 ዜና መዋዕል Chapter 10 Online

Read 1 ዜና መዋዕል Chapter 10 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ዜና መዋዕል in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 1 ዜና መዋዕል and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

A+ A A-

1 ዜና መዋዕል 10

ምዕራፍ 10

1. ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ተዋጉ፤ የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፥ ተወግተውም በጊልቦአ ተራራ ላይ ወደቁ።

2. ፤ ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን በእግር በእግራቸው ተከትለው አባረሩአቸው፤ ፍልስጥኤማውያንም የሳኦልን ልጆች ዮናታንንና አሚናዳብን ሜልኪሳንም ገደሉ።

3. ፤ ሰልፍም በሳኦል ላይ ጠነከረ፥ ቀስተኞችም አገኙት፤ ከቀስተኞችም የተነሣ ተጨነቀ።

4. ፤ ሳኦልም ጋሻ ጃግሬውን። እነዚህ ቈላፋን መጥተው እንዳይዘብቱብኝ ሰይፍህን መዝዘህ ውጋኝ አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ነበርና እንቢ አለ። ሳኦልም ሰይፉን ወስዶ በላዩ ወደቀ።

5. ፤ ጋሻ ጃግሬውም ሳኦል እንደ ሞተ ባየ ጊዜ እርሱ ደግሞ በሰይፉ ላይ ወድቆ ሞተ።

6. ፤ ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ የቤቱም ሰዎች ሁሉ በአንድ ላይ ሞቱ።

7. ፤ በሸለቆውም የነበሩት የእስራኤል ሰዎች ሁሉ እንደ ሸሹ፥ ሳኦልና ልጆቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ለቅቀው ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው።

8. ፤ በነጋውም ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦልንና ልጆቹን በጊልቦአ ተራራ ላይ ወድቀው አገኙአቸው።

9. ፤ ገፈፉትም፥ ራሱንና መሣሪያውንም አንሥተው ለጣኦቶቻቸውና ለሕዝቡ የምሥራች ይወስዱ ዘንድ ወደ ፍልስጥኤማውያን አገር ዙሪያ ሰደዱ።

10. ፤ መሣሪያውንም በአምላኮቻቸው ቤት ውስጥ አኖሩ፤ ራሱንም በዳጎን ቤት ውስጥ ቸነከሩት።

11. ፤ የኢያቢስ ገለዓድም ሰዎች ሁሉ ፍልስጥኤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን ሁሉ በሰሙ ጊዜ፥

12. ፤ ጽኑአን ሰዎች ሁሉ ተነሥተው የሳኦልን ሬሳ የልጆቹንም ሬሳ ወሰዱ፥ ወደ ኢያቢስም አመጡአቸው፤ በኢያቢስም ካለው ከትልቁ ዛፍ በታች አጥንቶቻቸውን ቀበሩ፥ ሰባት ቀንም ጾሙ።

13. ፤ እንዲሁ ሳኦል በእግዚአብሔር ላይ ስላደረገው ኃጢአት፥ የእግዚአብሔርንም ቃል ስላልጠበቀ ሞተ። ደግሞም መናፍስት ጠሪ

14. ፤ ስለ ጠየቀ እግዚአብሔርንም ስላልጠየቀ፥ ስለዚህ ገደለው፥ መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት አሳለፈው።

About 1 ዜና መዋዕል Chapter 10

Read 1 ዜና መዋዕል Chapter 10 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ዜና መዋዕል in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 1 ዜና መዋዕል
Chapter: 10
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 1 ዜና መዋዕል. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 1 ዜና መዋዕል Chapter 10 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 1 ዜና መዋዕል Chapter 10?

1 ዜና መዋዕል Chapter 10 is part of the Book of 1 ዜና መዋዕል in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 1 ዜና መዋዕል Chapter 10 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 1-ዜና-መዋዕል

  1. 1 ዜና መዋዕል Chapter 2
  2. 1 ዜና መዋዕል Chapter 13
  3. 1 ዜና መዋዕል Chapter 25
  4. 1 ዜና መዋዕል Chapter 15
  5. 1 ዜና መዋዕል Chapter 12
  6. 1 ዜና መዋዕል Chapter 7
  7. 1 ዜና መዋዕል Chapter 3

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ኤርምያስ Chapter 14
  2. ኢዮብ Chapter 1
  3. ዘሌዋውያን Chapter 6
  4. ሚክያስ Chapter 2
  5. ዘዳግም Chapter 25
  6. ዘኍልቍ Chapter 3
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 51

Related Chapters & Readings

  1. ማርቆስ Chapter 13
  2. ዕብራውያን Chapter 7
  3. ዘኍልቍ Chapter 35
  4. ኤርምያስ Chapter 44
  5. ዘካርያስ Chapter 9
  6. መዝሙረ ዳዊት Chapter 58
  7. 2 ነገሥት Chapter 7
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *