Read ኢዮብ Chapter 8 Online
Read ኢዮብ Chapter 8 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኢዮብ and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
ኢዮብ 8
ምዕራፍ 8
1. ሹሐዊውም በልዳዶስ መለሰ እንዲህም አለ።
2. ፤ እስከ መቼ ይህን ትናገራለህ? የአፍህስ ቃል እስከ መቼ እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆናል?
3. ፤ በውኑ እግዚአብሔር ፍርድን ያጣምማልን? ሁሉንም የሚችል አምላክ ጽድቅን ያጣምማልን?
4. ፤ ልጆችህ በድለውት እንደ ሆነ፥ እርሱ በበደላቸው እጅ ጥሎአቸዋል።
5. ፤ እግዚአብሔርን ብትገሠግሥ፥ ሁሉንም የሚችለውን አምላክ ብትለምን፥
6. ፤ ንጹሕና ቅን ብትሆን፥ በእውነት አሁን ስለ አንተ ይነቃል፥ የጽድቅህንም መኖሪያ ያከናውንልሃል።
7. ፤ ጅማሬህ ታናሽ ቢሆንም እንኳ ፍጻሜህ እጅግ ይበዛል።
8. ፤
9. ፤ ዘመናችን በምድር ላይ እንደ ጥላ ነውና እኛ የትናንት ብቻ ነን፤ ምንም አናውቅም፤ ስለዚህ የቀደመውን ትውልድ ጠይቅ፥ አባቶቻቸውም ለመረመሩት ነገር ትጋ፤
10. ፤ እነርሱ የሚያስተምሩህና የሚነግሩህ፥ ቃልንም ከልባቸው የሚያወጡ አይደሉምን?
11. ፤ በውኑ ደንገል ረግረግ በሌለበት መሬት ይበቅላልን? ወይስ ቄጠማ ውኃ በሌለበት ቦታ ይለመልማልን?
12. ፤ ገና ሲለመልም ሳይቈረጥም፥ ከአትክልት ሁሉ በፊት ይደርቃል።
13. ፤ እግዚአብሔርን የሚረሱ ሁሉ ፍጻሜአቸው እንዲሁ ነው፤ የዝንጉም ሰው ተስፋ ይጠፋል።
14. ፤ ተስፋው ይቈረጣል፥ እምነቱም እንደ ሸረሪት ቤት ይሆናል።
15. ፤ ቤቱን ይደግፈዋል፥ አይቆምለትም፤ ይይዘውማል፥ አይጸናለትም።
16. ፤ ፀሐይም ሳይተኵስ ይለመልማል፥ ጫፉም በአታክልቱ ቦታ ይወጣል።
17. ፤ በድንጋይ ክምር ላይ ሥሩ ይጠመጠማል፤ የድንጋዮቹን ቦታ ይመለከታል።
18. ፤ ከቦታው ቢጠፋ። አላየሁህም ብሎ ይክደዋል።
19. ፤ እነሆ፥ የመንገዱ ደስታ እንዲህ ነው፤ ሌሎችም ከመሬት ይበቅላሉ።
20. ፤ እነሆ፥ እግዚአብሔር ፍጹሙን ሰው አይጥለውም፥ የኃጢአተኞችንም እጅ አያበረታም።
21. ፤ አፍህን እንደ ገና ሳቅ ይሞላል፥ ከንፈሮችህንም እልልታ ይሞላል።
22. ፤ የሚጠሉህ እፍረት ይለብሳሉ፤ የኃጢአተኞችም ድንኳን አይገኝም።
About ኢዮብ Chapter 8
Read ኢዮብ Chapter 8 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: ኢዮብ
Chapter: 8
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኢዮብ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading ኢዮብ Chapter 8 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is ኢዮብ Chapter 8?
ኢዮብ Chapter 8 is part of the Book of ኢዮብ in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete ኢዮብ Chapter 8 online for free with easy chapter navigation.