ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 3

For English

Read ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 3 Online

Read ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 3 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሰቆቃወ ኤርምያስ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ሰቆቃወ ኤርምያስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

A+ A A-

ሰቆቃወ ኤርምያስ 3

ምዕራፍ 3

1. አሌፍ። በቍጣው በትር መከራ ያየ ሰው እኔ ነኝ።

2. ፤ ብርሃን ወደ ሌለበት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰደኝ።

3. ፤ ዘወትር ቀኑን ሁሉ እጁን በላዬ መለሰ።

4. ፤ ቤት። ሥጋዬንና ቁርበቴን አስረጀ፥ አጥንቴን ሰበረ።

5. ፤ ቅጥር ሠራብኝ በሐሞትና በድካምም ከበበኝ።

6. ፤ ቀድሞ ሞተው እንደ ነበሩ በጨለማ አኖረኝ።

7. ፤ ጋሜል። እንዳልወጣ በዙሪያዬ ቅጥር ሠራብኝ፤ ሰንሰለቴን አከበደ።

8. ፤ በጠራሁና በጮኽሁ ጊዜ ጸሎቴን ከለከለ።

9. ፤ መንገዴን በተጠረበ ድንጋይ ዘጋ፥ ጐዳናዬንም አጣመመ።

10. ፤ ዳሌጥ። እንደሚሸምቅ ድብ እንደ ተሸሸገም አንበሳ ሆነብኝ።

11. ፤ መንገዴን ለወጠ፥ ገነጣጠለኝም፤ ባድማ አደረገኝ።

12. ፤ ቀስቱን ገተረ ለፍላጻውም እንደ ጊጤ አደረገኝ።

13. ፤ ሄ። የሰገባውን ፍላጻዎች በኵላሊቴ ውስጥ ተከለ።

14. ፤ ለወገኔ ሁሉ ማላገጫ ቀኑንም ሁሉ መሳለቂያ ሆንሁ።

15. ፤ ምሬት ሞላብኝ በእሬትም አጠገበኝ።

16. ፤ ዋው። ጥርሴን በጭንጫ ሰበረ፥ በአመድም ከደነኝ።

17. ፤ ነፍሴን ከሰላም አራቅህ፤ በጎ ነገርን ረሳሁ።

18. ፤ እኔም። ኃይሌ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ያለው ተስፋዬ ጠፋ አልሁ።

19. ፤ ዛይ። መከራዬንና ችግሬን እሬትንና ሐሞትን አስብ።

20. ፤ ነፍሴ እያሰበችው በውስጤ ፈዘዘች።

21. ፤ ይህችን በልቤ አኖራለሁ፥ ስለዚህ እታገሣለሁ።

22. ፤ ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና።

23. ፤ ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው።

24. ፤ ነፍሴ። እግዚአብሔር እድል ፈንታዬ ነው፤ ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ አለች።

25. ፤ ጤት። እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ መልካም ነው።

26. ፤ ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው።

27. ፤ ሰው በታናሽነቱ ቀንበር ቢሸከም መልካም ነው።

28. ፤ ዮድ። እርሱ አሸክሞታልና ዝም ብሎ ለብቻው ይቀመጥ።

29. ፤ ተስፋ የሆነው እንደ ሆነ አፉን በአፈር ውስጥ ያኑር።

30. ፤ ጕንጩን ለሚመታው ይስጥ፥ ስድብንም ይጥገብ።

31. ፤ ካፍ። ጌታ ለዘላለም አይጥልምና፤

32. ፤ ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራልና፤

33. ፤ የሰውን ልጆች ከልቡ አያስጨንቅም፥ አያሳዝንምም።

34. ፤ ላሜድ። በምድር የተጋዙትን ሁሉ ከእግሩ በታች ይረግጣቸው ዘንድ፥

35. ፤ የሰውን ፍርድ በልዑል ፊት ይመልስ ዘንድ፥

36. ፤ የሰውን ፍርድ ያጣምም ዘንድ ጌታ እሺ አይልም።

37. ፤ ሜም። ጌታ ያላዘዘውን የሚልና የሚፈጽም ማን ነው?

38. ፤ ከልዑል አፍ ክፉና መልካም ነገር አይወጣምን?

39. ፤ ሕያው ሰው የሚያጕረመርም፥ ሰው ስለ ኃጢአቱ ቅጣት የሚያጕረመርም ስለ ምንድር ነው?

40. ፤ ኖን። መንገዳችንን እንመርምርና እንፈትን፥ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ።

41. ፤ ልባችንን ከእጃችን ጋር በሰማይ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር እናንሣ።

42. ፤ በድለናል ዐምፀናልም፥ አንተም ይቅር አላልህም።

43. ፤ ሳምኬት። በቍጣ ከደንኸን አሳደድኸንም፤ ገደልኸን፥ አልራራህም።

44. ፤ ጸሎት እንዳያልፍ ራስህን በደመና ከደንህ።

45. ፤ በአሕዛብ መካከል ጕድፍና ውዳቂ አደረግኸን።

46. ፤ ዔ። ጠላቶቻችን ሁሉ አፋቸውን ኣላቀቁብን።

47. ፤ ድንጋጤና ቍጣ፥ ጥፋትና ቅጥቃጤ ሆነብን።

48. ፤ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ ዓይኔ የውኃ ፈሳሽ አፈሰሰች።

49.

50. ፤ ፌ። እግዚአብሔር ከሰማይ እስኪጐበኝና እስኪመለከት ድረስ ዓይኔ ሳታቋርጥ ዝም ሳትል እንባ ታፈስሳለች።

51. ፤ ስለ ከተማዬ ቈነጃጅት ሁሉ ዓይኔ ነፍሴን አሳዘነች።

52. ፤ ጻዴ። በከንቱ ነገር ጠላቶች የሆኑኝ እንደ ወፍ ማደንን አደኑኝ።

53. ፤ ሕይወቴን በጕድጓድ አጠፉ፥ በላዬም ድንጋይ ጣሉ።

54. ፤ በራሴ ላይ ውኆች ተከነበሉ፤ እኔም። ጠፋሁ ብዬ ነበር።

55. ፤ ቆፍ። አቤቱ፥ በጠለቀ ጕድጓድ ውስጥ ሆኜ ስምህን ጠራሁ።

56. ፤ ድምፄን ሰማህ፤ ጆሮህን ከልመናዬ አትመልስ።

57. ፤ በጠራሁህ ቀን ቀርበህ። አትፍራ አልህ።

58. ፤ ሬስ። ጌታ ሆይ፥ ስለ ነፍሴ ተምዋግተህ ሕይወቴን ተቤዠህ።

59. ፤ አቤቱ፥ ጭንቀቴን አይተሃል፥ ፍርዴን ፍረድልኝ።

60. ፤ በቀላቸውን ሁሉና በእኔ ላይ ያለውን አሳባቸውን ሁሉ አየህ።

61. ፤ ሳን። አቤቱ፥ ስድባቸውንና በእኔ ላይ ያለውን አሳባቸውን ሁሉ፥

62. ፤ የተነሡብኝን ሰዎች ከንፈሮች ቀኑንም ሁሉ ያሰቡብኝን አሳባቸውን ሰማህ።

63. ፤ መቀመጣቸውንና መነሣታቸውን ተመልከት፤ እኔ መሳለቂያቸው ነኝ።

64. ፤ ታው። አቤቱ፥ እንደ እጃቸው ሥራ ፍዳቸውን ትከፍላቸዋለህ።

65. ፤ የልብ ዕውርነትንና እርግማንህን ትሰጣቸዋለህ።

66. ፤ አቤቱ፥ በቍጣ ታሳድዳቸዋለህ ከሰማይም በታች ታጠፋቸዋለህ።

About ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 3

Read ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 3 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሰቆቃወ ኤርምያስ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ሰቆቃወ ኤርምያስ
Chapter: 3
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ሰቆቃወ ኤርምያስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 3 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 3?

ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 3 is part of the Book of ሰቆቃወ ኤርምያስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 3 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ሰቆቃወ ኤርምያስ

  1. ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 4
  2. ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 1
  3. ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 5
  4. ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 2

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ሕዝቅኤል Chapter 33
  2. ምሳሌ Chapter 24
  3. ዘጸአት Chapter 37
  4. ኢዮብ Chapter 19
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 132
  6. ኢሳይያስ Chapter 60
  7. ኢሳይያስ Chapter 52

Related Chapters & Readings

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 68
  2. ዘፍጥረት Chapter 40
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 149
  4. ኤፌሶን Chapter 3
  5. ዘጸአት Chapter 4
  6. ዘሌዋውያን Chapter 16
  7. ዳንኤል Chapter 4
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *