ምሳሌ Chapter 19

For English

Read ምሳሌ Chapter 19 Online

Read ምሳሌ Chapter 19 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ምሳሌ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ምሳሌ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

A+ A A-

ምሳሌ 19

ምዕራፍ 19

1. በከንፈሩ ከሚወሳልት ሰነፍ ይልቅ ያለ ነውር የሚሄድ ድሀ ይሻላል።

2. ነፍስ እውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ እግሩንም የሚያፈጥን ከመንገድ ይስታል።

3. የሰው ስንፍና መንገዱን ታጣምምበታለች፤ ልቡም በእግዚአብሔር ላይ ይቈጣል።

4. ባለጠግነት ብዙ ወዳጆች ይጨምራል፤ የድሀ ወዳጅ ግን ከእርሱ ይርቃል።

5. ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም፥ በሐሰትም የሚናገር አያመልጥም።

6. ብዙ ሰዎች ለጋሱን ያቈላምጣሉ፥ ስጦታ ለሚሰጥም ሁሉ ወዳጅ ነው።

7. ድሀን ሰው ወንድሞቹ ሁሉ ይጠሉታል፤ ይልቁንም ወዳጆቹ ከእርሱ ይርቃሉ። እነርሱንም በቃል ቢከተላቸው አንዳች አይረቡትም።

8. ጥበብን የሚያገኝ ነፍሱን ይወድዳል፥ ማስተዋልንም የሚጠብቅ መልካም ነገርን ያገኛል።

9. ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም፤ በሐሰትም የሚናገር ይጠፋል።

10. ለሰነፍ ቅምጥልነት አይገባውም፥ ይልቁንም ባሪያ በአለቆች ላይ ይገዛ ዘንድ።

11. ሰውን ጠቢብ አእምሮው ከቍጣ ያዘገየዋል፥ ለበደለኛውም ይቅር ይል ዘንድ ክብር ይሆንለታል።

12. እንደ አንበሳ ግሣት የንጉሥ ቍጣ ነው፥ ሞገሱም በመስክ ላይ እንዳለ ጠል ነው።

13. ሰነፍ ልጅ ለአባቱ ኀዘን ነው፥ ጠበኛም ሚስት እንደማያቋርጥ ነጠብጣብ ናት።

14. ቤትና ባለጠግነት ከአባቶች ዘንድ ይወረሳሉ፤ አስተዋይ ሚስት ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ናት።

15. ተግባር መፍታት እንቅልፍን ታመጣለች፥ የታካችም ነፍስ ትራባለች።

16. ትእዛዝን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ መንገዱን ቸል የሚል ግን ይጠፋል።

17. ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል።

18. ተስፋ ገና ሳለች ልጅህን ገሥጽ፥ መሞቱንም አትሻ።

19. ንዴተኛ ሰው መቀጮ ይከፍላል፤ ብታድነውም ደግሞ ትጨምራለህ።

20. ምክርን ስማ፥ ተግሣጽንም ተቀበል በፍጻሜህ ጠቢብ ትሆን ዘንድ።

21. በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፤ የእግዚአብሔር ምክር ግን እርሱ ይጸናል።

22. የሰው ቸርነት የእርሱ ፍሬ ነው፤ ከሐሰተኛ ባለጠጋም እውነተኛ ድሀ ይሻላል።

23. እግዚአብሔርን መፍራት ወደ ሕይወት ይመራል፤ የሚፈራውም ጠግቦ ይኖራል፥ ክፉ ነገርም አያገኘውም።

24. ታካች ሰው እጁን በወጭቱ ያጠልቃታል፥ ወደ አፉ ስንኳ አይመልሳትም።

25. ፌዘኛ ብትገርፈው አላዋቂ ብልሃተኛ ይሆናል፤ አስተዋይን ሰው ብትገሥጸው እውቀትን ያገኛል።

26. አባቱን የሚያስከፋ እናቱንም የሚያሳድድ የሚያሳፍርና ጐስቋላ ልጅ ነው።

27. ልጅ ሆይ፥ ተግሣጽን ከሰማህ በኋላ ከእውቀት ቃል መሳሳትን ተው።

28. ወስላታ ምስክር በፍርድ ያፌዛል፥ የኀጥኣንም አፍ ክፋትን ይውጣል።

29. ለሚያፌዙ ሰዎች ፍርድ ተዘጋጅታለች፥ ለሰነፎችም ጀርባ በትር።

About ምሳሌ Chapter 19

Read ምሳሌ Chapter 19 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ምሳሌ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ምሳሌ
Chapter: 19
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ምሳሌ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ምሳሌ Chapter 19 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ምሳሌ Chapter 19?

ምሳሌ Chapter 19 is part of the Book of ምሳሌ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ምሳሌ Chapter 19 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ምሳሌ

  1. ምሳሌ Chapter 17
  2. ምሳሌ Chapter 15
  3. ምሳሌ Chapter 4
  4. ምሳሌ Chapter 3
  5. ምሳሌ Chapter 30
  6. ምሳሌ Chapter 26
  7. ምሳሌ Chapter 24

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. 1 ዜና መዋዕል Chapter 8
  2. አስቴር Chapter 8
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 118
  4. ምሳሌ Chapter 21
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 18
  6. 2 ዜና መዋዕል Chapter 9
  7. ዘኍልቍ Chapter 6

Related Chapters & Readings

  1. 2 ዜና መዋዕል Chapter 5
  2. 1 ሳሙኤል Chapter 15
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 47
  4. ማቴዎስ Chapter 2
  5. ማቴዎስ Chapter 9
  6. ዮሐንስ Chapter 9
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 104
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *