Read 1 ሳሙኤል Chapter 15 Online
Read 1 ሳሙኤል Chapter 15 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ሳሙኤል in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 1 ሳሙኤል and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
1 ሳሙኤል 15
ምዕራፍ 15
1. ሳሙኤልም ሳኦልን አለው። በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን እቀባህ ዘንድ እግዚአብሔር ላከኝ፥ አሁንም የእግዚአብሔርን ድምፅ ስማ።
2. ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ አማሌቅ በመንገድ እየተቃወመ ያደረገበትን እበቀላለሁ።
3. ፤ አሁንም ሄደህ አማሌቅን ምታ፥ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፥ አትማራቸውም፤ ወንዱንና ሴቱን ብላቴናውንና ሕፃኑን በሬውንና በጉን ግመሉንና አህያውን ግደል።
4. ፤ ሳኦልም ሕዝቡን ጠርቶ በጌልገላ ቈጠራቸው፤ ሁለት መቶ ሺህ እግረኞች፥ ከይሁዳም አሥር ሺህ ሰዎች ነበሩ።
5. ፤ ሳኦልም ወደ አማሌቅ ከተማ ወጣ፥ በሸለቆውም ውስጥ ተደበቀ።
6. ፤ ሳኦል ቄናውያንን። ተነሥታችሁ ሂዱ፤ ከግብጽ በወጡ ጊዜ ለእስራኤል ልጆች ቸርነት አድርጋችኋልና ከአማሌቅ ጋር እንዳላጠፋችሁ ከመካከላቸው ውረዱ አላቸው፤ ቄናውያንም ከአማሌቃውያን መካከል ሄዱ።
7. ፤ ሳኦልም አማሌቃውያንን ከኤውላጥ ጀምሮ በግብጽ ፊት እስካለችው እስከ ሱር ድረስ መታቸው።
8. ፤ የአማሌቅንም ንጉሥ አጋግን በሕይወቱ ማረከው፥ ሕዝቡንም ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው።
9. ፤ ነገር ግን ሳኦልና ሕዝቡ ለአጋግ፥ ለተመረጡትም በጎችና በሬዎች ለሰቡትም ጥጆችና ጠቦቶች፥ ለመልካሞቹም ሁሉ ራሩላቸው፥ ፈጽሞ ሊያጠፉአቸውም አልወደዱም፤ ነገር ግን ምናምንቴንና የተናቀውን ሁሉ ፈጽመው አጠፉት።
10. ፤
11. ፤ የእግዚአብሔርም ቃል። ሳኦል እኔ ከመከተል ተመልሶአልና፥ ትእዛዜንም አልፈጸመምና ስላነገሥሁት ተጸጸትሁ ብሎ ወደ ሳሙኤል መጣ። ሳሙኤልም ተቈጣ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።
12. ፤ ሳሙኤልም በነጋው ሳኦልን ለመገናኘት ማለደ። ሳኦልም ወደ ቀርሜሎስ መጣ፤ እነሆም፥ የመታሰቢያ ዓምድ ባቆመ ጊዜ ዞሮ አለፈ፥ ወደ ጌልገላም ወረደ የሚል ወሬ ለሳሙኤል ደረሰለት።
13. ፤ ሳሙኤልም ወደ ሳኦል መጣ፤ ሳኦልም። አንተ ለእግዚአብሔር የተባረክህ ሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ፈጽሜአለሁ አለው።
14. ፤ ሳሙኤልም። ይህ በጆሮዬ የምሰማው የበጎች ጩኸትና የበሬዎች ግሣት ምንድር ነው? አለ።
15. ፤ ሳኦልም። ሕዝቡ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ይሠዉአቸው ዘንድ መልካሞቹን በጎችና በሬዎች አድነዋቸዋልና ከአማሌቃውያን አምጥተዋቸዋል፤ የቀሩትንም ፈጽመን አጠፋን አለው።
16. ፤ ሳሙኤልም ሳኦልን። ቆይ፥ እግዚአብሔር ዛሬ ሌሊት የነገረኝን ልንገርህ አለው፤ እርሱም። ተናገር አለው።
17. ፤ ሳሙኤልም አለ። በዓይንህ ምንም ታናሽ ብትሆን ለእስራኤል ነገዶች አለቃ አልሆንህምን? እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባህ።
18. ፤ እግዚአብሔርም። ሄደህ ኃጢአተኞቹን አማሌቃውያንን ፈጽመህ አጥፋቸው፥ እስኪጠፉም ድረስ ውጋቸው ብሎ በመንገድ ላከህ።
19. ፤ ለምርኮ ሳስተህ ለምን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማህም? ለምንስ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረግህ?
20. ፤ ሳኦልም ሳሙኤልን። የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቻለሁ፥ እግዚአብሔርም በላከኝ መንገድ ሄጃለሁ፤ የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን አምጥቻለሁ፥ አማሌቃውያንንም ፈጽሜ አጥፍቻለሁ።
21. ፤ ሕዝቡ ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በጌልገላ ይሠዉ ዘንድ ከእርሙ የተመረጡትን በጎችንና በሬዎችን ከምርኮው ወሰዱ አለው።
22. ፤ ሳሙኤልም። በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።
23. ፤ ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነው፤ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ አለ።
24. ፤ ሳኦልም ሳሙኤልን። ሕዝቡን ስለ ፈራሁ፥ ቃላቸውንም ስለ ሰማሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝና የአንተን ቃል በመተላለፍ በድያለሁ።
25. ፤ አሁንም፥ እባክህ፥ ኃጢአቴን ይቅር በለኝ፥ ለእግዚአብሔርም እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመለስ አለው።
26. ፤ ሳሙኤልም ሳኦልን። የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና፥ እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃልና ከአንተ ጋር አልመለስም አለው።
27. ፤ ሳሙኤልም ሊሄድ ዘወር ባለ ጊዜ ሳኦል የልብሱን ጫፍ ያዘ፥ ተቀደደም።
28. ፤ ሳሙኤልም። እግዚአብሔር የእስራኤልን መንግሥት ዛሬ ከአንተ ቀደዳት፥ ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጣት፤
29. ፤ የእስራኤል ኃይል እንደ ሰው የሚጸጸት አይደለምና አይዋሽም አይጸጸትምም አለው።
30. ፤ እርሱም። በድያለሁ፤ አሁን ግን በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊትና በእስራኤል ፊት፥ እባክህ፥ አክብረኝ፤ ለአምላክህም ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመለስ አለው።
31. ፤ ሳሙኤልም ከሳኦል በኋላ ተመለሰ፤ ሳኦልም ለእግዚአብሔር ሰገደ።
32. ፤ ሳሙኤልም። የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ አለ። አጋግም እየተንቀጠቀጠ ወደ እርሱ መጣ። አጋግም። በውኑ ሞት እንደዚህ መራራ ነውን? አለ።
33. ፤ ሳሙኤልም። ሰይፍህ ሴቶችን ልጆች አልባ እንዳደረገቻቸው እንዲሁ እናትህ በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች አለ፤ ሳሙኤልም አጋግን በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ ቈራረጠው።
34. ፤ ሳሙኤልም ወደ አርማቴም ሄደ፤
35. ፤ ሳኦልም ወደ ቤቱ ወደ ጊብዓ ወጣ። ሳሙኤልም እስከ ሞተበት ቀን ድረስ ሳኦልን ለማየት ዳግመኛ አልሄደም፥ ሳሙኤልም ለሳኦል አለቀሰ፤ እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ሳኦልን ስላነገሠ ተጸጸተ።
About 1 ሳሙኤል Chapter 15
Read 1 ሳሙኤል Chapter 15 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ሳሙኤል in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: 1 ሳሙኤል
Chapter: 15
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 1 ሳሙኤል. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading 1 ሳሙኤል Chapter 15 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is 1 ሳሙኤል Chapter 15?
1 ሳሙኤል Chapter 15 is part of the Book of 1 ሳሙኤል in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete 1 ሳሙኤል Chapter 15 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from 1 ሳሙኤል
- 1 ሳሙኤል Chapter 9
- 1 ሳሙኤል Chapter 30
- 1 ሳሙኤል Chapter 22
- 1 ሳሙኤል Chapter 20
- 1 ሳሙኤል Chapter 13
- 1 ሳሙኤል Chapter 29
- 1 ሳሙኤል Chapter 16
Explore More from ብሉይ ኪዳን
- ኤርምያስ Chapter 49
- ዘፍጥረት Chapter 18
- 2 ዜና መዋዕል Chapter 18
- ዘፍጥረት Chapter 27
- ኢሳይያስ Chapter 42
- ኢሳይያስ Chapter 51
- 2 ነገሥት Chapter 2