1 ቆሮንቶስ Chapter 3

For English

Read 1 ቆሮንቶስ Chapter 3 Online

Read 1 ቆሮንቶስ Chapter 3 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ቆሮንቶስ in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 1 ቆሮንቶስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

1 ቆሮንቶስ 3

ምዕራፍ 3

1. እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም።

2. ገና ጽኑ መብል ለመብላት አትችሉም ነበርና ወተት ጋትኋችሁ፤

3. ገና ሥጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ ገና አትችሉም። ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን?

4. አንዱ። እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ ሁለተኛውም። እኔ የአጵሎስ ነኝ ቢል ሰዎች ብቻ መሆናችሁ አይደለምን?

5. አጵሎስ እንግዲህ ምንድር ነው? ጳውሎስስ ምንድር ነው? በእነርሱ እጅ ያመናችሁ አገልጋዮች ናቸው፤ ለእያንዳንዳቸውም ጌታ እንደ ሰጣቸው ያገለግላሉ።

6. እኔ ተከልሁ አጵሎስም አጠጣ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር፤

7. እንግዲያስ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ የሚተክል ቢሆን ወይም የሚያጠጣ ቢሆን አንዳች አይደለም።

8. የሚተክልና የሚያጠጣ አንድ ናቸው፥ ነገር ግን እያንዳንዱ እንደ ራሱ ድካም መጠን የራሱን ደመወዝ ይቀበላል።

9. የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ፤ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና።

10. የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን መሠረትሁ፥ ሌላውም በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ።

11. ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

12. ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ፥ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤

13. በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፥ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል።

14. ማንም በእርሱ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ደመወዙን ይቀበላል፤

15. የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፥ እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል።

16. የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?

17. ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።

18. ማንም ራሱን አያታልል፤ ከእናንተ ማንም በዚች ዓለም ጥበበኛ የሆነ ቢመስለው ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ሞኝ ይሁን።

19. –

20. የዚህች ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነውና። እርሱ ጥበበኞችን በተንኰላቸው የሚይዝ፤ ደግሞም። ጌታ የጥበበኞችን አሳብ ከንቱ እንደ ሆነ ያውቃል ተብሎ ተጽፎአልና።

21. ስለዚህም ማንም በሰው አይመካ። ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና፤

22. ጳውሎስ ቢሆን አጵሎስም ቢሆን ኬፋም ቢሆን ዓለምም ቢሆን ሕይወትም ቢሆን ሞትም ቢሆን ያለውም ቢሆን የሚመጣውም ቢሆን፥

23. ሁሉ የእናንተ ነው፥ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው።

About 1 ቆሮንቶስ Chapter 3

Read 1 ቆሮንቶስ Chapter 3 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ቆሮንቶስ in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 1 ቆሮንቶስ
Chapter: 3
Testament: New Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 1 ቆሮንቶስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 1 ቆሮንቶስ Chapter 3 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 1 ቆሮንቶስ Chapter 3?

1 ቆሮንቶስ Chapter 3 is part of the Book of 1 ቆሮንቶስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 1 ቆሮንቶስ Chapter 3 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 1-ቆሮንቶስ

  1. 1 ቆሮንቶስ Chapter 5
  2. 1 ቆሮንቶስ Chapter 1
  3. 1 ቆሮንቶስ Chapter 8
  4. 1 ቆሮንቶስ Chapter 2
  5. 1 ቆሮንቶስ Chapter 14
  6. 1 ቆሮንቶስ Chapter 13
  7. 1 ቆሮንቶስ Chapter 4

Explore More from አዲስ ኪዳን

  1. 1 ተሰሎንቄ Chapter 1
  2. ማቴዎስ Chapter 27
  3. ማቴዎስ Chapter 24
  4. ሮሜ Chapter 11
  5. ዕብራውያን Chapter 8
  6. ዕብራውያን Chapter 3
  7. 1 ጢሞቴዎስ Chapter 3

Related Chapters & Readings

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 66
  2. ዘኍልቍ Chapter 29
  3. መሳፍንት Chapter 13
  4. ሕዝቅኤል Chapter 30
  5. ዘኍልቍ Chapter 22
  6. ምሳሌ Chapter 7
  7. ሕዝቅኤል Chapter 26
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *