Read 1 ቆሮንቶስ Chapter 6 Online
Read 1 ቆሮንቶስ Chapter 6 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ቆሮንቶስ in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 1 ቆሮንቶስ and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
1 ቆሮንቶስ 6
ምዕራፍ 6
1. ከእናንተ አንዱ ከባልንጀራው ጋር ሙግት ቢኖረው በቅዱሳን ፊት በመፋረድ ፋንታ በዓመፀኞች ፊት ሊፋረድ ይደፍራልን?
2. ቅዱሳን በዓለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን? በዓለምስ ላይ ብትፈርዱ ከሁሉ ይልቅ ትንሽ ስለሚሆን ነገር ልትፈርዱ አትበቁምን?
3. የትዳር ጉዳይ ይቅርና በመላእክት እንኳ እንድንፈርድ አታውቁምን?
4. እንግዲህ ስለ ትዳር ጉዳይ የፍርድ ቤት ቢያስፈልጋችሁ በቤተ ክርስቲያን የተናቁትን ሰዎች ፈራጆች አድርጋችሁ ታስቀምጣላችሁን?
5. አሳፍራችሁ ዘንድ ይህን እላለሁ። እንደዚህ ነውን? በወንድሞች መካከል ሽማግሌ ሊሆን የሚችል አንድ አስተዋይ ሰው በእናንተ ዘንድ አይገኝምን?
6. ነገር ግን ወንድም ወንድሙን ይከሳል፥ ይህም በማያምኑ ፊት ይደረጋልን?
7. እንግዲህ ፈጽሞ የእርስ በርስ ሙግት እንዳለባችሁ በእናንተ ጉድለት ነው። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ አይሻልምን?
8. ነገር ግን እናንተ ትበድላላችሁ ታታልሉማላችሁ፥ ያውም ወንድሞቻችሁን።
9. ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ
10. ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
11. ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል።
12. ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም።
13. መብል ለሆድ ነው፥ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሥጋ ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሥጋ ነው፤
14. እግዚአብሔርም ጌታንም አስነሣ እኛንም በኃይሉ ያስነሣናል።
15. ሥጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች እንደ ሆነ አታውቁምን? እንግዲህ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ የጋለሞታ ብልቶች ላድርጋቸውን? አይገባም።
16. ወይስ ከጋለሞታ ጋር የሚተባበር አንድ ሥጋ እንዲሆን አታውቁምን? ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ ተብሎአልና።
17. ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው።
18. ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል።
19. –
20. ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።
About 1 ቆሮንቶስ Chapter 6
Read 1 ቆሮንቶስ Chapter 6 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ቆሮንቶስ in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: 1 ቆሮንቶስ
Chapter: 6
Testament: New Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 1 ቆሮንቶስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading 1 ቆሮንቶስ Chapter 6 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is 1 ቆሮንቶስ Chapter 6?
1 ቆሮንቶስ Chapter 6 is part of the Book of 1 ቆሮንቶስ in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete 1 ቆሮንቶስ Chapter 6 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from 1-ቆሮንቶስ
- 1 ቆሮንቶስ Chapter 1
- 1 ቆሮንቶስ Chapter 2
- 1 ቆሮንቶስ Chapter 14
- 1 ቆሮንቶስ Chapter 11
- 1 ቆሮንቶስ Chapter 13
- 1 ቆሮንቶስ Chapter 12
- 1 ቆሮንቶስ Chapter 10
Explore More from አዲስ ኪዳን
- ሉቃስ Chapter 7
- ቲቶ Chapter 2
- ዕብራውያን Chapter 4
- የሐዋርያት ሥራ Chapter 13
- ዕብራውያን Chapter 7
- ሮሜ Chapter 16
- 2 ቆሮንቶስ Chapter 1