1 ቆሮንቶስ Chapter 16

For English

Read 1 ቆሮንቶስ Chapter 16 Online

Read 1 ቆሮንቶስ Chapter 16 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ቆሮንቶስ in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 1 ቆሮንቶስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

1 ቆሮንቶስ 16

ምዕራፍ 16

1. ለቅዱሳንም ገንዘብን ስለ ማዋጣት፥ ለገላትያ አብያተ ክርስቲያናት እንደ ደነገግሁት እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ።

2. እኔ ስመጣ ይህ የገንዘብ ማዋጣት ያን ጊዜ እንዳይሆን፥ ከእናንተ እያንዳንዱ በየሳምንቱ በፊተኛው ቀን እንደ ቀናው መጠን እያስቀረ በቤቱ ያስቀምጥ።

3. ስመጣም ማናቸውም ቢሆኑ የታመኑ የሚመስሉአችሁ ሰዎች ቸርነታችሁን ወደ ኢየሩሳሌም ያደርሱ ዘንድ ደብዳቤ ሰጥቼ እልካቸዋለሁ፤

4. እኔ ደግሞ ልሄድ የሚገባኝ ብሆን ከእኔ ጋር አብረው ይሄዳሉ።

5. በመቄዶንያም ሳልፍ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በመቄዶንያ አድርጌ አልፋለሁና፤

6. እናንተም ወደምሄድበት ወደ ማናቸውም ስፍራ በጉዞዬ እንድትረዱኝ ምናልባት በእናንተ ዘንድ እቆይ ወይም እከርም ይሆናል።

7. አሁን እግረ መንገዴን ሳልፍ ልጎበኛችሁ አልወድምና፤ ጌታ ቢፈቅደው የሆነውን ዘመን በእናንተ ዘንድ ልሰነብት ተስፋ አደርጋለሁና።

8. በኤፌሶን ግን እስከ በዓለ ኀምሳ ድረስ እሰነብታለሁ።

9. ሥራ የሞላበት ትልቅ በር ተከፍቶልኛልና ተቃዋሚዎችም ብዙ ናቸው።

10. ጢሞቴዎስም የመጣ እንደ ሆነ በእናንተ ዘንድ ያለ ፍርሃት እንዲኖር ተጠንቀቁ፤ እንደ እኔ ደግሞ የጌታን ሥራ ይሠራልና፤ እንግዲህ ማንም አይናቀው።

11. ነገር ግን ከወንድሞቹ ጋር እጠብቀዋለሁና ወደ እኔ ይመጣ ዘንድ በሰላም በጉዞው እርዱት።

12. ስለ ወንድማችን ስለ አጵሎስ ግን ከወንድሞቹ ጋር ወደ እናንተ ሊሄድ እጅግ አድርጌ ለምኜው ነበር፤ ዛሬም ለመምጣት ከቶ ፈቃድ አልነበረውም፥ ሲመቸው ግን ይመጣል።

13. ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ።

14. በእናንተ ዘንድ ሁሉ በፍቅር ይሁን።

15. ወንድሞች ሆይ፥ የእስጢፋኖስ ቤተ ሰዎች የአካይያ በኩራት እንደ ሆኑ ቅዱሳንንም ለማገልገል ራሳቸውን እንደ ሰጡ ታውቃላችሁ፤

16. እንደ እነርሱ ላሉትና አብሮ ለሚሠራ ለሚደክምም ሁሉ እናንተም እንድትገዙ እለምናችኋለሁ።

17. በእስጢፋኖስና በፈርዶናጥስ በአካይቆስም መምጣት ደስ ይለኛል፥ እናንተ ስለሌላችሁ የጎደለኝን ፈጽመዋልና፤ መንፈሴንና መንፈሳችሁን አሳርፈዋልና።

18. እንግዲህ እንደነዚህ ያሉትን እወቁአቸው።

19. የእስያ አብያተ ክርስቲያናት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አቂላና ጵርስቅላ በቤታቸው ካለች ቤተ ክርስቲያን ጋር በጌታ እጅግ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

20. ወንድሞች ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ።

21. እኔ ጳውሎስ ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ ጽፌአለሁ።

22. ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታችን ሆይ፥ ና።

23. የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።

24. ፍቅሬ በክርስቶስ ኢየሱስ ከሁላችሁ ጋር ነው። አሜን።

About 1 ቆሮንቶስ Chapter 16

Read 1 ቆሮንቶስ Chapter 16 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ቆሮንቶስ in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 1 ቆሮንቶስ
Chapter: 16
Testament: New Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 1 ቆሮንቶስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 1 ቆሮንቶስ Chapter 16 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 1 ቆሮንቶስ Chapter 16?

1 ቆሮንቶስ Chapter 16 is part of the Book of 1 ቆሮንቶስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 1 ቆሮንቶስ Chapter 16 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 1-ቆሮንቶስ

  1. 1 ቆሮንቶስ Chapter 1
  2. 1 ቆሮንቶስ Chapter 2
  3. 1 ቆሮንቶስ Chapter 14
  4. 1 ቆሮንቶስ Chapter 11
  5. 1 ቆሮንቶስ Chapter 13
  6. 1 ቆሮንቶስ Chapter 9
  7. 1 ቆሮንቶስ Chapter 6

Explore More from አዲስ ኪዳን

  1. ዕብራውያን Chapter 12
  2. ማርቆስ Chapter 2
  3. ራእይ Chapter 9
  4. 1 ቆሮንቶስ Chapter 3
  5. ያዕቆብ Chapter 1
  6. የሐዋርያት ሥራ Chapter 10
  7. ማርቆስ Chapter 10

Related Chapters & Readings

  1. 2 ዜና መዋዕል Chapter 35
  2. 1 ነገሥት Chapter 8
  3. ዮሐንስ Chapter 16
  4. መክብብ Chapter 2
  5. የሐዋርያት ሥራ Chapter 4
  6. 2 ተሰሎንቄ Chapter 3
  7. ሆሴዕ Chapter 5
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *