Read 1 ዜና መዋዕል Chapter 18 Online
Read 1 ዜና መዋዕል Chapter 18 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ዜና መዋዕል in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 1 ዜና መዋዕል and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
1 ዜና መዋዕል 18
ምዕራፍ 18
1. ከዚህም በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን መታ፥ አዋረዳቸውም፥ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ጌትንና መንደሮችዋን ወሰደ።
2. ፤ ሞዓብን መታ፤ ሞዓባውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት።
3. ፤ ዳዊትም በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ የነበረውን ግዛት ለመያዝ በሄደ ጊዜ የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን እስከ ሃማት ድረስ መታ።
4. ፤ ዳዊትም ከእርሱ አንድ ሺህ ሰረገሎች፥ ሰባት ሺህም ፈረሰኞች፥ ሀያ ሺህም እግረኞች ወሰደ፤ ዳዊት ለመቶ ሰረገሎች የሚሆኑትን ብቻ አስቀርቶ የሰረገሎቹን ፈረሶች ቋንጃ ቆረጠ።
5. ፤ ከደማስቆም ሶርያውያን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ሊረዱ በመጡ ጊዜ ዳዊት ከሶርያውያን ሀያ ሁለት ሺህ ሰዎችን ገደለ።
6. ፤ ዳዊትም በደማስቆ ሶርያ ጭፍሮች አኖረ፤ ሶርያውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፥ ግብርም አመጡለት። እግዚአብሔርም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድል ይሰጠው ነበር።
7. ፤ ዳዊትም ለአድርአዛር ባሪያዎች የነበሩትን የወርቅ ጋሻዎች ወሰደ፥ ወደ ኢየሩሳሌምም ይዞአቸው መጣ።
8. ፤ ከአድርአዛርም ከተሞች ከጢብሐትና ከኩን ዳዊት እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ፤ ከዚህም ሰሎሞን የናሱን ኵሬና ዓምዶች የናሱንም ዕቃ ሠራ።
9. ፤ የሐማትም ንጉሥ ቶዑ ዳዊት የሱባን ንጉሥ የአድርአዛርን ጭፍራ ሁሉ እንደ መታ ሰማ።
10. ፤ ቶዑም ከአድርአዛር ጋር ሁል ጊዜ ይዋጋ ነበርና ዳዊት አድርአዛርን ወግቶ ስለመታው ደኅንነቱን ይጠይቅ ዘንድ ይመርቀውም ዘንድ ልጁን አዶራምን ወደ ዳዊት ላከው፤ እርሱም የወርቅና የብር የናስም ዕቃ ይዞ መጣ።
11. ፤ ንጉሡም ዳዊት ከአሕዛብ ሁሉ ከኤዶምና ከሞዓብ ከአሞንም ልጆች ከፍልስጥኤማውያንም ከአማሌቅም ከማረከው ብርና ወርቅ ጋር እነዚህን ደግሞ ለእግዚአብሔር ቀደሰ።
12. ፤ ደግሞ የጽሩያ ልጅ አቢሳ ከኤዶማውያን በጨው ሸለቆ ውስጥ አሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች ገደለ።
13. ፤ በኤዶምያስም ጭፍሮች አኖረ፥ ኤዶማውያንም ሁሉ ለዳዊት ገባሮች ሆኑ። እግዚአብሔርም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድል ይሰጠው ነበር።
14. ፤ ዳዊትም በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤ ለሕዝቡም ሁሉ ፍርድንና ጽድቅም አደረገላቸው።
15. ፤ የጽሩያ ልጅ ኢዮአብም የሠራዊት አለቃ ነበረ፤ የአሒሉድም ልጅ ኢዮሣፍጥ ታሪክ ጸሐፊ ነበረ።
16. ፤ የአኪጦብም ልጅ ሳዶቅ፥ የአቤሜሌክም ልጅ አብያታር ካህናት ነበሩ፤ ሱሳ ጸሐፊ ነበረ።
17. ፤ የዮዳሄ ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ ነበረ፤ የዳዊትም ልጆች በንጉሡ አጠገብ አለቆች ነበሩ።
About 1 ዜና መዋዕል Chapter 18
Read 1 ዜና መዋዕል Chapter 18 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ዜና መዋዕል in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: 1 ዜና መዋዕል
Chapter: 18
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 1 ዜና መዋዕል. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading 1 ዜና መዋዕል Chapter 18 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is 1 ዜና መዋዕል Chapter 18?
1 ዜና መዋዕል Chapter 18 is part of the Book of 1 ዜና መዋዕል in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete 1 ዜና መዋዕል Chapter 18 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from 1-ዜና-መዋዕል
- 1 ዜና መዋዕል Chapter 2
- 1 ዜና መዋዕል Chapter 15
- 1 ዜና መዋዕል Chapter 13
- 1 ዜና መዋዕል Chapter 27
- 1 ዜና መዋዕል Chapter 25
- 1 ዜና መዋዕል Chapter 12
- 1 ዜና መዋዕል Chapter 7
Explore More from ብሉይ ኪዳን
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 43
- ኢዮብ Chapter 42
- 2 ነገሥት Chapter 8
- 1 ነገሥት Chapter 12
- ዘፍጥረት Chapter 48
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 22
- ዘፍጥረት Chapter 26