Read ምሳሌ Chapter 14 Online
Read ምሳሌ Chapter 14 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ምሳሌ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ምሳሌ and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
ምሳሌ 14
ምዕራፍ 14
1. ብልሃተኛ ሴት ቤትዋን ትሠራለች፤ ሰነፍ ሴት ግን በእጅዋ ታፈርሰዋለች።
2. በቅን የሚሄድ ሰው እግዚአብሔርን ይፈራል፤ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይንቀዋል።
3. በሰነፍ አፍ የትዕቢት በትር አለ፤ የጠቢባን ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች።
4. በሬ በሌለበት ስፍራ እህል አይገኝም፤ ብዙ ሲሳይ ግን በበሬዎች ኃይል ነው።
5. የታመነ ምስክር አይዋሽም፤ የሐሰት ምስክር ግን በሐሰት ይናገራል።
6. ፌዘኛ ሰው ጥበብን ይፈልጋል አያገኛትም፤ ለአስተዋይ ግን እውቀትን ማግኘት አያስቸግረውም።
7. ከሰነፍ ሰው ፊት ራቅ፥ በእርሱ ዘንድ የእውቀትን ከንፈር አታገኝምና።
8. የብልህ ሰው ጥበብ መንገዱን ያስተውል ዘንድ ነው፤ የሰነፎች ስንፍና ግን ሽንገላ ነው።
9. ሰነፉ በኃጢአት ያፌዛል፤ በቅኖች መካከል ግን ቸርነት አለች።
10. የራሱን ኀዘን ልብ ያውቃል፤ ከደስታውም ጋር ሌላ ሰው አይገናኝም።
11. የኅጥኣን ቤት ይፈርሳል፤ የቅኖች ማደሪያ ግን ያብባል።
12. ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች ፍጻሜዋ ግን የሞት መንገድ ነው።
13. በሳቅ ደግሞ ልብ ያዝናል፥ የደስታም ፍጻሜ ልቅሶ ነው።
14. ልቡን ከጽድቅ የሚመልስ ሰው ከመንገዱ ፍሬ ይጠግባል፥ ጻድቅም ሰው ደግሞ በራሱ።
15. የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል፤ ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል።
16. ጠቢብ ሰው ይፈራል ከክፉም ይሸሻል፤ ሰነፍ ግን ራሱን ታምኖ ይኰራል።
17. ቍጡ ሰው በስንፍና ይሠራል፤ አስተዋይ ግን ይታገሣል።
18. አላዋቂዎች ሰዎች ስንፍናን ይወርሳሉ፤ ብልሆች ግን እውቀትን እንደ ዘውድ ይጭናሉ።
19. ኃጢአተኞች በደጎች ፊት ይጐነበሳሉ፥ ኀጥኣንም በጻድቃን በር።
20. ድሀ በባልንጀራው ዘንድ የተጠላ ነው የባለጠጋ ወዳጆች ግን ብዙዎች ናቸው።
21. ባልንጀራውን የሚንቅ ይበድላል ለድሀ ግን የሚራራ ምስጉ ነው።
22. ክፉ የሚያደርጉ ይስታሉ፤ ምሕረትና እውነት ግን መልካምን ለሚያደርጉ ናቸው።
23. በድካም ሁሉ ልምላሜ ይገኛል፤ ብዙ ነገር በሚናገር ከንፈር ግን ድህነት ብቻ አለ።
24. የጠቢባን ዘውድ ባለጠግነታቸው ነው፤ የሰነፎች ስንፍና ግን ስንፍና ነው።
25. እውነተኛ ምስክር ነፍሶችን ያድናል፤ በሐሰት የሚናገር ግን ሸንጋይ ነው።
26. እግዚአብሔርን ለሚፈራ ጠንካራ መታመን አለው፥ ለልጆቹም መጠጊያ ይኖራል።
27. ሰው ከሞት ወጥመድ ያመልጥ ዘድን እግዚአብሔርን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው።
28. የንጉሥ ክብር በሕዝብ ብዛት ነው፤ በሰው ጥቂትነት ግን የገዥ ጥፋት አለ።
29. ለትግሥተኛ ሰው ብዙ ማስተዋል አለው፤ ቍጡ ግን ስንፍናውን ከፍ ከፍ ያደርጋል።
30. ትሑት ልብ የሥጋ ሕይወት ነው፤ ቅንዓት ግን አጥንትን ያነቅዛል።
31. ድሀን የሚያስጨንቅ ፈጣሪውን ይሰድባል፤ ለድሀ ምሕረትን የሚያደርግ ግን ያከብረዋል።
32. ኀጥእ በክፋቱ ይደፋል፤ ጻድቅ ግን በእውነቱ ይታመናል።
33. በአዋቂ ልብ ጥበብ ትቀመጣለች፤ በሰነፎች ውስጥ ግን አትታወቅም።
34. ጽድቅ ሕዝብን ከፍ ከፍ ታደርጋለች፤ ኃጢአት ግን ሕዝብን ታስነውራለች።
35. አስተዋይ አገልጋይ በንጉሥ ዘንድ ይወደዳል፤ በሚያሳፍር ላይ ግን ቍጣው ይሆናል።
About ምሳሌ Chapter 14
Read ምሳሌ Chapter 14 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ምሳሌ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: ምሳሌ
Chapter: 14
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ምሳሌ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading ምሳሌ Chapter 14 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is ምሳሌ Chapter 14?
ምሳሌ Chapter 14 is part of the Book of ምሳሌ in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete ምሳሌ Chapter 14 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from ምሳሌ
Explore More from ብሉይ ኪዳን
- ናሆም Chapter 3
- ዘጸአት Chapter 33
- ኢሳይያስ Chapter 58
- ምሳሌ Chapter 28
- ዘጸአት Chapter 29
- መክብብ Chapter 3
- ሕዝቅኤል Chapter 14