Read መክብብ Chapter 10 Online
Read መክብብ Chapter 10 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መክብብ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መክብብ and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
መክብብ 10
ምዕራፍ 10
1. የሞቱ ዝንቦች የተቀመመውን የዘይት ሽቱ ያገሙታል፤ እንዲሁም ትንሽ ስንፍና ጥበብንና ክብርን ያጠፋል።
2. ፤ የጠቢብ ልብ በስተ ቀኙ ነው፥ የሰነፍ ልብ ግን በስተ ግራው ነው።
3. ፤ ደግሞም ሰነፍ በመንገድ ሲመላለስ እርሱ ልብ ይጐድለዋል፥ የሚያስበውም ሁሉ ስንፍና ነው።
4. ፤ ትዕግሥት ታላቁን ኃጢአት ጸጥ ያደርጋልና የገዢ ቍጣ የተነሣብህ እንደ ሆነ ስፍራህን አትልቀቅ።
5. ፤ ከፀሐይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፥ እርሱም ከገዢ የሚወጣ ስሕተት ነው፤
6. ፤ ሰነፍ በታላቅ ማዕርግ ተሾመ፥ ባለጠጎች ግን በተዋረደ ስፍራ ተቀመጡ።
7. ፤ ባሪያዎች በፈረስ ላይ ሲቀመጡ መሳፍንትም እንደ ባሪያዎች በምድር ላይ ሲሄዱ አየሁ።
8. ፤ ጕድጓድን የሚምስ ይወድቅበታል፥ ቅጥርንም የሚያፈርስን እባብ ትነድፈዋለች።
9. ፤ ድንጋይን የሚፈነቅል ይታመምበታል፥ እንጨትንም የሚፈልጥ ይጐዳበታል።
10. ፤ ብረት ቢደነዝዝ ሰውም ባይስለው ኃይልን ሊያበዛ ይገባዋል፤ ጥበብ ግን ሥራውን ለማከናወን ትጠቅመዋለች።
11. ፤ ደጋሚ ሳይደግምባት እባብ ብትነድፍ ለደጋሚው ትርፍ የለውም።
12. ፤ የጠቢብ ሰው የአፉ ቃል ሞገስ ናት፤ የሰነፍ ከንፈሮች ግን ራሱን ይውጡታል።
13. ፤ የአፉ ቃል መጀመሪያ ስንፍና ነው፥ የንግግሩ ፍጻሜም ክፉ እብደት ነው።
14. ፤ ሰነፍ ቃሉን ያበዛል፤ ሰው ግን የሚሆነውን አያውቅም፤ ከእርሱስ በኋላ የሚሆነውን ማን ይነግረዋል?
15. ፤ የሰነፍ ሥራ ያደክመዋል ወደ ከተማ መሄድ አያውቅምና።
16. ፤ ንጉሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ማልደው የሚበሉ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ ወዮልሽ!
17. ፤ ንጉሥሽ የከበረ ልጅ የሆነ፥ ለብርታት እንጂ ለስካር ያይደለ በጊዜ የሚበሉ መኳንንት ያሉሽ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ የተመሰገንሽ ነሽ።
18. ፤ ተግባር በመፍታት ጣራው ይዘብጣል፥ በእጅም መታከት ቤት ያፈስሳል።
19. ፤ እንጀራን ለሳቅ የወይን ጠጅንም ለሕይወት ደስታ ያደርጉታል፥ ሁሉም ለገንዘብ ይገዛል።
20. ፤ የሰማይ ወፍ ቃሉን ይወስደዋልና፥ ባለ ክንፎችም ነገሩን ይናገራሉና በልብህ አሳብ እንኳ ቢሆን ንጉሥን አትስደብ፥ በመኝታ ቤትህም ባለጠጋን አትስደብ።
About መክብብ Chapter 10
Read መክብብ Chapter 10 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መክብብ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: መክብብ
Chapter: 10
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መክብብ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading መክብብ Chapter 10 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is መክብብ Chapter 10?
መክብብ Chapter 10 is part of the Book of መክብብ in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete መክብብ Chapter 10 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from መክብብ
- መክብብ Chapter 6
- መክብብ Chapter 5
- መክብብ Chapter 12
- መክብብ Chapter 11
- መክብብ Chapter 9
- መክብብ Chapter 8
- መክብብ Chapter 3
Explore More from ብሉይ ኪዳን
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 116
- ሕዝቅኤል Chapter 43
- ዘሌዋውያን Chapter 16
- ዘዳግም Chapter 8
- ኢዮብ Chapter 28
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 67
- ኢያሱ Chapter 4