ሚልክያስ Chapter 1

For English

Read ሚልክያስ Chapter 1 Online

Read ሚልክያስ Chapter 1 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሚልክያስ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ሚልክያስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ሚልክያስ 1

ምዕራፍ 1

1. በሚልክያስ እጅ ለእስራኤል የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው።

2. ፤ ወድጃችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እናንተ ግን። በምን ወደድኸን? ብላችኋል። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል እግዚአብሔር፤ ያዕቆብንም ወደድሁ፥ ዔሳውንም ጠላሁ፤

3. ፤ ተራሮቹንም በረሃ አደረግኋቸው፥ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮች አሳልፌ ሰጠኋቸው።

4. ፤ ኤዶምያስ። እኛ ፈርሰናል፥ ነገር ግን የፈረሰውን መልሰን እንሠራለን ቢል፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነርሱ ይሠራሉ፥ እኔ ግን አፈርሳለሁ፤ በሰዎችም ዘንድ። የበደል ዳርቻና እግዚአብሔር ለዘላለም የተቈጣው ሕዝብ ይባላል።

5. ፤ ዓይኖቻችሁም ያያሉ፥ እናንተም። እግዚአብሔር ከእስራኤል ዳርቻ ወዲያ ታላቅ ይሁን ትላላችሁ።

6. ፤ እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፤ እኔስ አባት ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተም። ስምህን ያቃለልን በምንድር ነው? ብላችኋል።

7. ፤ በመሠዊያዬ ላይ ርኩስ እንጀራ ታቀርባላችሁ። እናንተም። ያረከስንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። የእግዚአብሔር ገበታ የተነቀፈ ነው በማለታችሁ ነው።

8. ፤ ዕውር መሥዋዕትንም ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? አንካሳውንና የታመመውን ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? ያንን ለአለቃህ አቅርብ፤ በውኑ በአንተ ደስ ይለዋልን? ወይስ ፊትህን ይቀበላልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

9. ፤ አሁንም ጸጋን ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔርን ለምኑ፤ ይህ ከእጃችሁ የተሰጠ ሲሆን ከቶ ፊታችሁን ይቀበላልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

10. ፤ በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ ዘንድ ደጅ የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥ ቍርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

11. ፤ ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፤ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፤ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

12. ፤ እናንተ ግን። የእግዚአብሔር ገበታ ርኩስ ነው፤ ፍሬውና መብሉም የተናቀ ነው በማለታችሁ አስነቀፋችሁት።

13. ፤ እናንተ። እነሆ፥ ይህ ድካም ነው ብላችሁ ጢቅ አላችሁበት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ በቅሚያ የያዛችሁትንም አንካሳውንም የታመመውንም አቅርባችኋል፤ እንዲሁ ቍርባንን ታመጣላችሁ፤ በውኑ ከእጃችሁ ይህን ልቀበለውን? ይላል እግዚአብሔር።

14. ፤ እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ስሜም በአሕዛብ ዘንድ የተፈራ ነውና በመንጋው ውስጥ ተባት እያለው ለጌታ ተስሎ ነውረኛውን የሚሠዋ ሸንጋይ ሰው ርጉም ይሁን።

About ሚልክያስ Chapter 1

Read ሚልክያስ Chapter 1 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሚልክያስ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ሚልክያስ
Chapter: 1
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ሚልክያስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ሚልክያስ Chapter 1 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ሚልክያስ Chapter 1?

ሚልክያስ Chapter 1 is part of the Book of ሚልክያስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ሚልክያስ Chapter 1 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ሚልክያስ

  1. ሚልክያስ Chapter 4
  2. ሚልክያስ Chapter 2
  3. ሚልክያስ Chapter 3

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ኤርምያስ Chapter 44
  2. ዳንኤል Chapter 11
  3. 2 ነገሥት Chapter 1
  4. መሳፍንት Chapter 20
  5. 2 ነገሥት Chapter 19
  6. ዘፍጥረት Chapter 8
  7. ምሳሌ Chapter 15

Related Chapters & Readings

  1. ፊልሞና Chapter 1
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 29
  3. ዘዳግም Chapter 25
  4. ኢሳይያስ Chapter 5
  5. ሚክያስ Chapter 7
  6. 1 ቆሮንቶስ Chapter 2
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 94
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *