አስቴር Chapter 1

For English

Read አስቴር Chapter 1 Online

Read አስቴር Chapter 1 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of አስቴር in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of አስቴር and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

አስቴር 1

ምዕራፍ 1

1. በአርጤክስስም ዘመን እንዲህ ሆነ፤ ይህም አርጤክስስ ከህንድ ጀምሮ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ በመቶ ሀያ ሰባት አገሮች ላይ ነገሠ።

2. ፤ በዚያም ዘመን ንጉሡ አርጤክስስ በሱሳ ግንብ በነበረው በመንግሥቱ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ሳለ፥

3. ፤ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ለባለምዋሎቹና ለአገልጋዮቹ ሁሉ ግብዣ አደረገ፤ የፋርስና የሜዶን ታላላቆች ሁሉ፥ የየአገሩ አዛውንትና ሹማምት፥ በፊቱ ነበሩ፤

4. ፤ የከበረውንም የመንግሥቱን ሀብት፥ የታላቁንም የግርማዊነቱን ክብር መቶ ሰማንያ ቀን ያህል አሳያቸው።

5. ፤ ይህም ቀን በተፈጸመ ጊዜ በሱሳ ግንብ ውስጥ ለተገኙት ሕዝብ ሁሉ ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ንጉሡ በንጉሡ ቤት አታክልት ውስጥ ባለው አደባባይ ሰባት ቀን ግብዣ አደረገ።

6. ፤ ነጭ፥ አረንጓዴ፥ ሰማያዊም መጋረጆች ከጥሩ በፍታና ከሐምራዊ ግምጃ በተሠራ ገመድ፥ በብር ቀለበትና በዕብነ በረድ አዕማድ ላይ ተዘርግተው ነበር፤ አልጋዎቹም ከወርቅና ከብር ተሠርተው በቀይና በነጭ በብጫና በጥቁር ዕብነ በረድ ወለል ላይ ነበሩ።

7. ፤ መጠጡም በልዩ ልዩ በወርቅ ዕቃ ይታደል ነበር፤ የንጉሡም የወይን ጠጅ እንደ ንጉሡ ለጋስነት መጠን እጅግ ብዙ ነበረ።

8. ፤ ንጉሡም እንደ ሰው ሁሉ ፈቃድ ያደርጉ ዘንድ ለቤቱ አዛዦች ሁሉ አዝዞ ነበርና መጠጡ እንደ ወግ አልነበረም።

9. ፤ ንግሥቲቱም አስጢን በንጉሡ በአርጤክስስ ቤተ መንግሥት ለሴቶች ግብዣ አደረገች።

10.

11. ፤ በሰባተኛውም ቀን ንጉሡ አርጤክስስ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ደስ ባለው ጊዜ፥ ንግሥቲቱ አስጢን መልከ መልካም ነበረችና ውበትዋ ለአሕዛብና ለአለቆች እንዲታይ የመንግሥቱን ዘውድ ጭነው ወደ ንጉሡ ፊት ያመጡአት ዘንድ በፊቱ የሚያገለግሉትን ሰባቱን ጃንደረቦች ምሁማንን፥ ባዛንን፥ ሐርቦናን፥ ገበታን፥ ዘቶልታን፥ ዜታርን፥ ከርከስን አዘዛቸው።

12. ፤ ነገር ግን ንግሥቲቱ አስጢን በጃንደረቦቹ እጅ በላከው በንጉሡ ትእዛዝ ትመጣ ዘንድ እንቢ አለች፤ ንጉሡም እጅግ ተቈጣ፥ በቍጣውም ተናደደ።

13. ፤ ሕግንና ፍርድን በሚያውቁ ሁሉ ፊት የንጉሡ ወግ እንዲህ ነበረና ንጉሡ የዘመኑን ነገር የሚያውቁትን ጥበበኞችን፥

14. ፤ በመንግሥቱም ቀዳሚዎች ሆነው የሚቀመጡ የንጉሡ ባለምዋሎች ሰባቱ የፋርስና የሜዶን መሳፍንት አርቄስዮስ፥ ሼታር፥ አድማታ፥ ተርሺሽ፥ ሜሬስ፥ ማሌሴዓር፥ ምሙካን በአጠገቡ ሳሉ።

15. ፤ በጃንደረቦች እጅ የተላከባትን የንጉሡን የአርጤክስስን ትእዛዝ ስላላደረገች በንግሥቲቱ በአስጢን ላይ እንደ ሕጉ የምናደርገው ምንድር ነው? አላቸው።

16. ፤ ምሙካንም በንጉሡና በአዛውንቱ ፊት እንዲህ አለ። ንግሥቲቱ አስጢን አዛውንቱን ሁሉና በንጉሡ በአርጤክስስ አገር ያሉትን አሕዛብ ሁሉ በድላለች እንጂ ንጉሡን ብቻ የበደለች አይደለችም።

17. ፤ ይህ የንግሥቲቱ ነገር ወደ ሴቶች ሁሉ ይደርሳልና። ንጉሡ አርጤክስስ ንግሥቲቱ አስጢን ወደ እርሱ ትገባ ዘንድ አዘዘ፥ እርስዋ ግን አልገባችም ተብሎ በተነገረ ጊዜ ባሎቻቸው በዓይናቸው ዘንድ የተናቁ ይሆናሉ።

18. ፤ ዛሬም የንግሥቲቱን ነገር የሰሙት የፋርስና የሜዶን ወይዛዝር እንዲህና እንዲህ ብለው ለንጉሡ አዛውንት ሁሉ ይናገራሉ፥ ንቀትና ቍጣም ይበዛል።

19. ፤ ንጉሡም ቢፈቅድ፥ አስጢን ወደ ንጉሡ ወደ አርጤክስስ ፊት ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትገባ የንጉሡ ትእዛዝ ከእርሱ ይውጣ፥ እንዳይፈርስም በፋርስና በሜዶን ሕግ ይጻፍ፤ ንጉሡም ንግሥትነትዋን ከእርስዋ ለተሻለችው ለሌላይቱ ይስጥ።

20. ፤ የንጉሡም ትእዛዝ በሰፊው መንግሥቱ ሁሉ በተነገረ ጊዜ ሴቶች ሁሉ ባሎቻቸውን ታላቁንም ታናሹንም ያከብራሉ።

21. ፤ ይህም ምክር ንጉሡንና አዛውንቱን ደስ አሰኛቸው፤ ንጉሡም እንደ ምሙካን ቃል አደረገ።

22. ፤ ሰው ሁሉ በቤቱ አለቃ ይሁን፤ በሕዝቡም ቋንቋ ይናገር ብሎ ለአገሩ ሁሉ እንደ ጽሕፈቱ ለሕዝቡም ሁሉ እንደ ቋንቋው ደብዳቤዎችን ወደ ንጉሡ አገሮች ሁሉ ሰደደ።

About አስቴር Chapter 1

Read አስቴር Chapter 1 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of አስቴር in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: አስቴር
Chapter: 1
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading አስቴር. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading አስቴር Chapter 1 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is አስቴር Chapter 1?

አስቴር Chapter 1 is part of the Book of አስቴር in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete አስቴር Chapter 1 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ብሉይ ኪዳን

  1. አሞጽ Chapter 4
  2. አሞጽ Chapter 1
  3. አሞጽ Chapter 3
  4. አሞጽ Chapter 2
  5. አሞጽ Chapter 7
  6. አሞጽ Chapter 6
  7. አሞጽ Chapter 5

Explore More from አስቴር

  1. አስቴር Chapter 9
  2. አስቴር Chapter 6
  3. አስቴር Chapter 3
  4. አስቴር Chapter 4
  5. አስቴር Chapter 10
  6. አስቴር Chapter 2
  7. አስቴር Chapter 7

Related Chapters & Readings

  1. ዘዳግም Chapter 19
  2. ኢያሱ Chapter 24
  3. 1 ዜና መዋዕል Chapter 5
  4. ኢሳይያስ Chapter 36
  5. ዘጸአት Chapter 16
  6. 1 ቆሮንቶስ Chapter 6
  7. ራእይ Chapter 16
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *