1 ጴጥሮስ Chapter 5

For English

Read 1 ጴጥሮስ Chapter 5 Online

Read 1 ጴጥሮስ Chapter 5 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ጴጥሮስ in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 1 ጴጥሮስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

1 ጴጥሮስ 5

ምዕራፍ 5

1. እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤

2. በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤

3. ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤

4. የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።

5. እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።

6. እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤

7. እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።

8. በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤

9. በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።

10. በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁምል ያበረታችሁማል።

11. ለእርሱ ክብርና ኃይል እስከዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።

12. እየመከርኋችሁና የምትቆሙባት ጸጋ እውነትኛ የእግዚአብሔር ጸጋ እንድትሆን እየመሰከርሁላችሁ፥ የታመነ ወንድም እንደ ሆነ በቈጠርሁት በስልዋኖስ እጅ በአጭሩ ጽፌላችኋለሁ።

13. ከእናንተ ጋር ተመርጣ በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

14. በፍቅር አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። በክርስቶስ ላላችሁ ለሁላችሁ ሰላም ይሁን። አሜን።

About 1 ጴጥሮስ Chapter 5

Read 1 ጴጥሮስ Chapter 5 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ጴጥሮስ in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 1 ጴጥሮስ
Chapter: 5
Testament: New Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 1 ጴጥሮስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 1 ጴጥሮስ Chapter 5 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 1 ጴጥሮስ Chapter 5?

1 ጴጥሮስ Chapter 5 is part of the Book of 1 ጴጥሮስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 1 ጴጥሮስ Chapter 5 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 1-ጴጥሮስ

  1. 1 ጴጥሮስ Chapter 1
  2. 1 ጴጥሮስ Chapter 3
  3. 1 ጴጥሮስ Chapter 2
  4. 1 ጴጥሮስ Chapter 4

Explore More from አዲስ ኪዳን

  1. ሉቃስ Chapter 23
  2. የሐዋርያት ሥራ Chapter 15
  3. ማርቆስ Chapter 2
  4. ማቴዎስ Chapter 25
  5. ራእይ Chapter 10
  6. 1 ቆሮንቶስ Chapter 1
  7. የሐዋርያት ሥራ Chapter 19

Related Chapters & Readings

  1. ሆሴዕ Chapter 14
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 40
  3. ኤርምያስ Chapter 25
  4. ምሳሌ Chapter 12
  5. መሳፍንት Chapter 20
  6. 1 ሳሙኤል Chapter 14
  7. 2 ዜና መዋዕል Chapter 35
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *