ሚክያስ Chapter 5

For English

Read ሚክያስ Chapter 5 Online

Read ሚክያስ Chapter 5 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሚክያስ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ሚክያስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ሚክያስ 5

ምዕራፍ 5

1. የጭፍሮች ሴት ልጅ ሆይ፥ ጭፍሮችሽን አሁን ሰብስቢ፤ ከብቦ አስጨንቆናል፤ የእስራኤልን ፈራጅ ጕንጩን በበትር ይመታሉ።

2. ፤ አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።

3. ፤ ስለዚህ ወላጂቱ እስከምትወልድበት ጊዜ ድረስ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፤ የቀሩትም ወንድሞቹ ወደ እስራኤል ልጆች ይመለሳሉ።

4. ፤ እርሱም ይቆማል፥ በእግዚአብሔርም ኃይል በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ግርማ መንጋውን ይጠብቃል፤ እነርሱም ይኖራሉ፤ እርሱ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ይሆናልና።

5. ፤ ይህም ለሰላም ይሆናል፤ አሦራዊውም ወደ አገራችን በገባ ጊዜ፥ ምድራችንንም በረገጠ ጊዜ ሰባት እረኞችና ስምንት አለቆች እናስነሣበታለን።

6. ፤ የአሦርንም አገር በሰይፍ፥ የናምሩድንም አገር በመግቢያው ውስጥ ያፈርሳሉ፤ አሦራዊውም ወደ አገራችን በገባ ጊዜ፥ ዳርቾቻችንንም በረገጠ ጊዜ እርሱ ይታደገናል።

7. ፤ የያዕቆብም ቅሬታ በብዙ አሕዛብ መካከል ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፥ በሣር ላይ እንደሚወድ ካፊያ፤ ሰውንም እንደማይጠብቅ፥ የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ይሆናል።

8. ፤ በዱር አራዊትም መካከል እንዳለ አንበሳ፥ በበጎች መንጋም መካከል አልፎ እንደሚረግጥ፥ የሚታደግም ሳይኖር እንደሚነጥቅ እንደ አንበሳ ደቦል፥ እንዲሁ የያዕቆብ ቅሬታ በአሕዛብና በብዙ ወገኖች መካከል ይሆናል።

9. ፤ እጅህ በጠላቶችህ ላይ ከፍ ከፍ ትበል፥ ጠላቶችህም ሁሉ ይጥፉ።

10. ፤ በዚያም ቀን ፈረሶችህን ከመካከልህ አጠፋለሁ፥ ሰረገሎችህንም እሰብራለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤

11. ፤ የምድርህንም ከተሞች አጠፋለሁ፥ ምሽጎችህንም ሁሉ አፈርሳለሁ፤

12. ፤ መተትንም ከእጅህ አጠፋለሁ፥ ምዋርተኞችም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆኑልህም፤

13. ፤ የተቀረጹትን ምስሎችህንና ሐውልቶችህን ከመካከልህ አጠፋለሁ፥ ለእጅህም ሥራ ከእንግዲህ ወዲህ አትሰግድም፤

14. ፤ የማምለኪያ ዐፀዶችህንም ከመካከልህ እነቅላለሁ፥ ከተሞችህንም አፈርሳለሁ።

15. ፤ ባልሰሙም አሕዛብ ላይ በቍጣና በመዓት እበቀላለሁ።

About ሚክያስ Chapter 5

Read ሚክያስ Chapter 5 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሚክያስ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ሚክያስ
Chapter: 5
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ሚክያስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ሚክያስ Chapter 5 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ሚክያስ Chapter 5?

ሚክያስ Chapter 5 is part of the Book of ሚክያስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ሚክያስ Chapter 5 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ሚክያስ

  1. ሚክያስ Chapter 2
  2. ሚክያስ Chapter 7
  3. ሚክያስ Chapter 6
  4. ሚክያስ Chapter 4
  5. ሚክያስ Chapter 3
  6. ሚክያስ Chapter 1

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. 2 ዜና መዋዕል Chapter 11
  2. 2 ነገሥት Chapter 11
  3. ኤርምያስ Chapter 2
  4. ዘኍልቍ Chapter 27
  5. ኢዮብ Chapter 11
  6. ዘጸአት Chapter 1
  7. ኢሳይያስ Chapter 61

Related Chapters & Readings

  1. ያዕቆብ Chapter 2
  2. ዘፍጥረት Chapter 25
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 10
  4. ኢሳይያስ Chapter 66
  5. 1 ነገሥት Chapter 14
  6. ዮሐንስ Chapter 15
  7. 1 ዜና መዋዕል Chapter 18
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *