ሚክያስ Chapter 6

For English

Read ሚክያስ Chapter 6 Online

Read ሚክያስ Chapter 6 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሚክያስ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ሚክያስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ሚክያስ 6

ምዕራፍ 6

1. አሁን። ተነሣ፥ በተራሮችም ፊት ተፋረድ፥ ኮረብቶችም ቃልህን ይስሙ ብሎ እግዚአብሔር የሚለውን ስሙ።

2. ፤ ተራሮች ሆይ፥ ጠንካሮች የምድር መሠረቶችም ሆይ፥ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ክርክር አለውና፥ ከእስራኤልም ጋር ይፋረዳልና የእግዚአብሔርን ክርክር ስሙ።

3. ፤ ሕዝቤ ሆይ፥ ምን አድርጌሃለሁ? በምንስ አድክሜሃለሁ? መስክርብኝ።

4. ፤ ከግብጽ ምድር አውጥቼሃለሁ፥ ከባርነት ቤትም ተቤዥቼሃለሁ፤ በፊትህም ሙሴንና አሮንን ማርያምንም ልኬልህ ነበር።

5. ፤ ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፥ የቢዖርም ልጅ በለዓም የመለሰለትን አሁን አስብ፤ የእግዚአብሔርንም የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድ ከሰጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ አስብ።

6. ፤ ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣና በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ? የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንዱን ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልምጣን?

7. ፤ እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጎች ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን? ወይስ የበኵር ልጄን ስለ በደሌ፥ የሆዴንም ፍሬ ስለ ነፍሴ ኃጢአት እሰጣለሁን?

8. ፤ ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?

9. ፤ የእግዚአብሔር ድምፅ ከተማይቱን ይጠራታል፤ ስምህን መፍራት ጥበብ ነው፤ የመቅሠፍትን በትር፥ እርሱንም ያዘጋጀ ማን እንደ ሆነ ስሙ።

10. ፤ በውኑ በኃጢአተኛ ቤት የኃጢአት መዝገብ፥ የተጸየፈም ውሽተኛ መስፈሪያ ገና አለ ይሆን?

11. ፤ በአባይ ሚዛንና በከረጢት ባለ በተንኰል መመዘኛ ንጹሕ እሆናለሁን?

12. ፤ ባለ ጠጎችዋን ግፍ ሞልቶባቸዋል፤ በእርስዋም የሚኖሩ በሐሰት ተናግረዋል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ተንኰለኛ ነው።

13. ፤ ስለዚህ እኔ ደግሞ በክፉ ቍስል መታሁህ፤ ስለ ኃጢአትህም አፈርስሁህ።

14. ፤ ትበላለህ፥ ነገር ግን አትጠግብም፥ ችጋርህም በመካከልህ ይሆናል፤ ትወስዳለህ፥ ነገር ግን አታድንም፤ የምታድነውንም ለሰይፍ እሰጣለሁ።

15. ፤ ትዘራለህ፥ ነገር ግን አታጭድም፤ ወይራውንም ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን ዘይቱን አትቀባም፤ ወይኑንም ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን የወይን ጠጁን አትጠጣም።

16. ፤ አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፤ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።

About ሚክያስ Chapter 6

Read ሚክያስ Chapter 6 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሚክያስ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ሚክያስ
Chapter: 6
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ሚክያስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ሚክያስ Chapter 6 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ሚክያስ Chapter 6?

ሚክያስ Chapter 6 is part of the Book of ሚክያስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ሚክያስ Chapter 6 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ሚክያስ

  1. ሚክያስ Chapter 2
  2. ሚክያስ Chapter 7
  3. ሚክያስ Chapter 4
  4. ሚክያስ Chapter 5
  5. ሚክያስ Chapter 3
  6. ሚክያስ Chapter 1

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ዘሌዋውያን Chapter 14
  2. ኢዮብ Chapter 20
  3. 1 ነገሥት Chapter 16
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 88
  5. ዘኍልቍ Chapter 29
  6. ዘዳግም Chapter 6
  7. 1 ዜና መዋዕል Chapter 9

Related Chapters & Readings

  1. 2 ሳሙኤል Chapter 6
  2. የሐዋርያት ሥራ Chapter 6
  3. ሩት Chapter 3
  4. ዘዳግም Chapter 33
  5. መክብብ Chapter 6
  6. 2 ሳሙኤል Chapter 11
  7. ዘፍጥረት Chapter 38
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *