ሚክያስ Chapter 4

For English

Read ሚክያስ Chapter 4 Online

Read ሚክያስ Chapter 4 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሚክያስ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ሚክያስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ሚክያስ 4

ምዕራፍ 4

1. በመጨረሻውም ዘመን የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አሕዛብም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ።

2. ፤ ከጽዮን ሕግ፥ ከኢየሩሳሌምም የእግዚአብሔር ቃል ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው። ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በፍለጋውም እንሄዳለን ይላሉ።

3. ፤ በብዙዎችም አሕዛብ መካከል ይፈርዳል፥ በሩቅም ባሉ በብርቱዎች አሕዛብ ላይ ይበይናል፤ ሰይፋቸውንም ማረሻ፥ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፤ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም ከእንግዲህም ወዲህ ሰልፍ አይማሩም።

4. ፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር አፍም ተናግሮአልና ሰው እያንዳንዱ ከወይኑና ከበለሱ በታች ይቀመጣል፥ የሚያስፈራውም የለም።

5. ፤ ሕዝብም ሁሉ እያንዳንዱ በየአምላኩ ስም ይሄዳል፥ እኛም በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ለዘላለም እንሄዳለን።

6. ፤ በዚያ ቀን አንካሳይቱን እሰበስባለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የባከነችውንና ያስጨነቅኋትንም አከማቻለሁ፤

7. ፤ አንካሳይቱንም ለቅሬታ፥ ወደ ሩቅም የተጣለችውን ለብርቱ ሕዝብ አደርጋታለሁ፤ ከዚያም ወዲያ እስከ ዘላለም ድረስ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ በእነርሱ ላይ ይነግሣል።

8. ፤ አንተም የመንጋ ግንብ ሆይ፥ የጽዮን ሴት ልጅ አምባ፥ ወደ አንተ ትመጣለች፤ የቀደመችው ግዛት፥ የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ትደርሳለች።

9. ፤ አሁንስ ለምን ትጮኺአለሽ? እንደምትወልድ ሴት ምጥ የደረሰብሽ፥ ንጉሥ ስለሌለሽ ነውን? ወይስ መካሪ ስለ ጠፋብሽ ነውን?

10. ፤ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እንደምትወልድ ሴት አምጠሽ ውለጂ፤ አሁን ከከተማ ትወጫለሽና፥ በሜዳም ትቀመጫለሽ፥ ወደ ባቢሎንም ትደርሻለሽ፤ በዚያም ያድንሻል፥ በዚያም እግዚአብሔር ከጠላቶችሽ እጅ ይቤዥሻል።

11. ፤ አሁንም። ርኩስ ትሁን፥ ዓይናችንም በጽዮን ላይ ይይ የሚሉ ብዙ አሕዛብ በአንቺ ላይ ተሰብስበዋል።

12. ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔርን አሳብ አያውቁም፥ ምክሩንም አያስተውሉም፤ እንደ ነዶ ወደ አውድማ አከማችቶአቸዋልና።

13. ፤ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ቀንድሽን ብረት፥ ጥፍርሽንም ናስ አደርጋለሁና ተነሺ አሂጂ፤ ብዙ አሕዛብንም ታደቅቂአለሽ፤ ትርፋቸውንም ለእግዚአብሔር፥ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ ትቀድሻለሽ።

About ሚክያስ Chapter 4

Read ሚክያስ Chapter 4 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሚክያስ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ሚክያስ
Chapter: 4
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ሚክያስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ሚክያስ Chapter 4 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ሚክያስ Chapter 4?

ሚክያስ Chapter 4 is part of the Book of ሚክያስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ሚክያስ Chapter 4 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ሚክያስ

  1. ሚክያስ Chapter 6
  2. ሚክያስ Chapter 2
  3. ሚክያስ Chapter 7
  4. ሚክያስ Chapter 1
  5. ሚክያስ Chapter 5
  6. ሚክያስ Chapter 3

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ዘፍጥረት Chapter 27
  2. ኤርምያስ Chapter 17
  3. ሕዝቅኤል Chapter 32
  4. ዮናስ Chapter 4
  5. ሕዝቅኤል Chapter 18
  6. ዘሌዋውያን Chapter 26
  7. መሳፍንት Chapter 7

Related Chapters & Readings

  1. ዘዳግም Chapter 27
  2. ኤርምያስ Chapter 39
  3. 2 ሳሙኤል Chapter 12
  4. 2 ዜና መዋዕል Chapter 17
  5. 1 ዜና መዋዕል Chapter 1
  6. ዕንባቆም Chapter 2
  7. ኢሳይያስ Chapter 41
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *