ሮሜ Chapter 10

For English

Read ሮሜ Chapter 10 Online

Read ሮሜ Chapter 10 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሮሜ in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ሮሜ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ሮሜ 10

ምዕራፍ 10

1. ወንድሞች ሆይ፥ የልቤ በጎ ፈቃድና ስለ እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ልመናዬ እንዲድኑ ነው።

2. በእውቀት አይቅኑ እንጂ ለእግዚአብሔር እንዲቀኑ እመሰክርላቸዋለሁና።

3. የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም።

4. የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።

5. ሙሴ ከሕግ የሆነውን ጽድቅ የሚያደርገው ሰው በእርሱ በሕይወት እንዲኖር ጽፎአልና።

6. ከእምነት የሆነ ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል። በልብህ። ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤

7. ወይም። በልብህ። ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው።

8. ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው።

9. ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤

10. ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።

11. መጽሐፍ። በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና።

12. በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤

13. የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።

14. እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ?

15. መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ?

16. ነገር ግን ሁሉ ለምሥራቹ ቃል አልታዘዙም። ኢሳይያስ። ጌታ ሆይ፥ ምስክርነታችንን ማን አመነ? ብሎአልና።

17. እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።

18. ዳሩ ግን። ባይሰሙ ነው ወይ? እላለሁ። በእውነት። ድምፃቸው በምድር ሁሉ ላይ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ።

19. ነገር ግን። እስራኤል ባያውቁ ነው ወይ? እላለሁ። ሙሴ አስቀድሞ። እኔ ሕዝብ በማይሆነው አስቀናችኋለሁ በማያስተውልም ሕዝብ አስቆጣችኋለሁ

20. ብሎአል። ኢሳይያስም ደፍሮ። ላልፈለጉኝ ተገኘሁ፥ ላልጠየቁኝም ተገለጥሁ አለ።

21. ስለ እስራኤል ግን። ቀኑን ሁሉ ወደማይታዘዝና ወደሚቃወም ሕዝብ እጆቼን ዘረጋሁ ይላል።

About ሮሜ Chapter 10

Read ሮሜ Chapter 10 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሮሜ in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ሮሜ
Chapter: 10
Testament: New Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ሮሜ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ሮሜ Chapter 10 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ሮሜ Chapter 10?

ሮሜ Chapter 10 is part of the Book of ሮሜ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ሮሜ Chapter 10 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ሮሜ

  1. ሮሜ Chapter 7
  2. ሮሜ Chapter 6
  3. ሮሜ Chapter 16
  4. ሮሜ Chapter 13
  5. ሮሜ Chapter 8
  6. ሮሜ Chapter 2
  7. ሮሜ Chapter 15

Explore More from አዲስ ኪዳን

  1. 1 ተሰሎንቄ Chapter 5
  2. ማቴዎስ Chapter 26
  3. 1 ጴጥሮስ Chapter 3
  4. ሉቃስ Chapter 22
  5. ራእይ Chapter 1
  6. 1 ቆሮንቶስ Chapter 1
  7. ራእይ Chapter 3

Related Chapters & Readings

  1. 1 ቆሮንቶስ Chapter 5
  2. ማቴዎስ Chapter 21
  3. ዘፍጥረት Chapter 15
  4. 2 ሳሙኤል Chapter 15
  5. ኤርምያስ Chapter 1
  6. መዝሙረ ዳዊት Chapter 81
  7. ሮሜ Chapter 9
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *