ሆሴዕ Chapter 4

For English

Read ሆሴዕ Chapter 4 Online

Read ሆሴዕ Chapter 4 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሆሴዕ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ሆሴዕ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

A+ A A-

ሆሴዕ 4

ምዕራፍ 4

1. እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እውነትና ምሕረት እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድር ስለሌለ እግዚአብሔር በምድሩ ላይ ከሚኖሩ ጋር ክርክር አለውና የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።

2. ፤ እርግማንና ሐሰት ግዳይና ስርቆት ምንዝርናም ወጥተዋል፤ ደምም ወደ ደም ደርሶአል።

3. ፤ ስለዚህ ምድሪቱ ታለቅሳለች፥ በእርስዋም የሚቀመጡ ሁሉ ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች ጋር ይደክማሉ፤ የባሕሩም ዓሦች ያልቃሉ።

4. ፤ ነገር ግን ሕዝብህ ከካህን ጋር እንደሚከራከሩ ናቸውና ማንም አይከራከር፥ ማንም አይዝለፍ።

5. ፤ በቀንም ትሰናከላለህ፥ ነቢዩም ከአንተ ጋር በሌሊት ይሰናከላል፤ እናትህንም አጠፋታለሁ።

6. ፤ ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።

7. ፤ እንደ ብዛታቸው መጠን ኃጢአት ሠሩብኝ፤ እኔም ክብራቸውን ወደ ነውር እለውጣለሁ።

8. ፤ የሕዝቤም ኃጢአት መብል ሆኖላቸዋል፥ ልባቸውንም ወደ በደላቸው አድርገዋል።

9. ፤ እንደ ሕዝቡም እንዲሁ ካህኑ ይሆናል፤ በመንገዳቸውም እበቀላቸዋለሁ፥ ሥራቸውንም እመልስባቸዋለሁ።

10. ፤ እግዚአብሔርንም መጠበቅ ትተዋልና ሲበሉ አይጠግቡም፥ ሲያመነዝሩም አይበዙም።

11. ፤ ግልሙትናና የወይን ጠጅ ስካርም አእምሮን ያጠፋል።

12. ፤ የግልሙትና መንፈስ ሕዝቤን አስቶአቸዋልና፥ እነርሱም ከአምላካቸው ርቀው አመንዝረዋልና በትራቸውን ይጠይቃሉ፥ ዘንጋቸውም ይመልስላቸዋል።

13. ፤ በተራሮችም ራስ ላይ ይሠዋሉ፤ ጥላውም መልካም ነውና ከኮምበልና ከልብን ከአሆማም ዛፍ በታች በኮረብቶች ላይ ያጥናሉ፤ ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁ ይገለሙታሉ፥ ሙሽሮቻችሁም ያመነዝራሉ።

14. ፤ ወንዶችም ደግሞ ከጋለሞቶች ጋር ይጫወታሉና፥ ከጋለሞቶችም ጋር ይሠዋሉና ሴቶች ልጆቻችሁ በገለሞቱ ጊዜ፥ ሙሽሮቻችሁም ባመነዘሩ ጊዜ አልቀጣቸውም፤ የማያስተውልም ሕዝብ ይገለበጣል።

15. ፤ እስራኤል ሆይ፥ አንተ ብታመነዝር ይሁዳ አይበድል፤ እናንተም ወደ ጌልገላ አትግቡ፥ ወደ ቤትአዌንም አትውጡ፥ ወይም። ሕያው እግዚአብሔርን! ብላችሁ አትማሉ።

16. ፤ እስራኤል እንደ እልከኛ ጊደር እንቢ ብሎአል፤ እግዚአብሔርስ በሰፊው ቦታ እንደ ጠቦት ያሰማራዋልን?

17. ፤ ኤፍሬም ከጣዖታት ጋር ተጋጠመ፤ ተወው።

18. ፤ ስካርን ፈጽመዋል፥ ግልሙትናንም አብዝተዋል፤ አለቆችዋም ነውርን እጅግ ወደዱ።

19. ፤ ነፋስ በክንፍዋ አስሮአታል፤ ከመሥዋዕታቸውም የተነሣ ያፍራሉ።

About ሆሴዕ Chapter 4

Read ሆሴዕ Chapter 4 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሆሴዕ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ሆሴዕ
Chapter: 4
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ሆሴዕ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ሆሴዕ Chapter 4 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ሆሴዕ Chapter 4?

ሆሴዕ Chapter 4 is part of the Book of ሆሴዕ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ሆሴዕ Chapter 4 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ሆሴዕ

  1. ሆሴዕ Chapter 3
  2. ሆሴዕ Chapter 8
  3. ሆሴዕ Chapter 7
  4. ሆሴዕ Chapter 1
  5. ሆሴዕ Chapter 14
  6. ሆሴዕ Chapter 9
  7. ሆሴዕ Chapter 5

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ዘፍጥረት Chapter 24
  2. ሚልክያስ Chapter 2
  3. ሕዝቅኤል Chapter 25
  4. ዕዝራ Chapter 9
  5. 2 ዜና መዋዕል Chapter 7
  6. ምሳሌ Chapter 30
  7. ዘጸአት Chapter 24

Related Chapters & Readings

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 16
  2. ዘዳግም Chapter 9
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 12
  4. ሆሴዕ Chapter 7
  5. ኢያሱ Chapter 3
  6. 1 ነገሥት Chapter 20
  7. አስቴር Chapter 2
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *