Read ሆሴዕ Chapter 11 Online
Read ሆሴዕ Chapter 11 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሆሴዕ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ሆሴዕ and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
ሆሴዕ 11
ምዕራፍ 11
1. እስራኤል ሕፃን በነበረ ጊዜ ወደድሁት፥ ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት።
2. ፤ አብዝቼ ብጠራቸው አጥብቀው ከፊቴ ራቁ፤ ለበኣሊምም ይሠዉ ነበር፥ ለተቀረጹ ምስሎችም ያጥኑ ነበር።
3. ፤ እኔም ኤፍሬምን ክንዱን ይዤ በእግሩ እንዲሄድ መራሁት፤ እኔም እፈውሳቸው እንደ ነበርሁ አላወቁም።
4. ፤ በሰው ገመድ በፍቅርም እስራት ሳብኋቸው፤ ለእነርሱም ቀምበርን ከጫንቃቸው ላይ እንደሚያነሣ ሆንሁ፥ ድርቆሽም ጣልሁላቸው።
5. ፤ ወደ እኔ ይመለሱ ዘንድ አልወደዱምና ወደ ግብጽ ምድር ይመለሳሉ፥ አሦርም ንጉሣቸው ይሆናል።
6. ፤ ከመከሩትም ምክር የተነሣ ሰይፍ በከተሞቻቸው ላይ ይወድቃል፥ ከበርቴዎችንም ያጠፋል።
7. ፤ ሕዝቤም ከእኔ ይመለሱ ዘንድ ወደዱ፤ ወደ ላይም ቢጠሩአቸው ማንም ከፍ ከፍ ያደርጋቸው ዘንድ አይችልም።
8. ፤ ኤፍሬም ሆይ፥ እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ፥ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴትስ እንደ አዳማ እጥልሃለሁ? እንዴትስ እንደ ሲባዮ አደርግሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተናውጣለች፥ ምሕረቴም ተነሣሥታለች።
9. ፤ እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥ በመካከልህም ቅዱሱ ነኝና የቁጣዬን መቅሠፍት አላደርግም፥ ኤፍሬምንም አጠፋ ዘንድ አልመለስም፤ በመዓትም አልመጣም።
10. ፤ እግዚአብሔርን ይከተላሉ፥ እርሱም እንደ አንበሳ ያገሣል፤ ባገሣም ጊዜ ልጆች እየተንቀጠቀጡ ከምዕራብ ይመጣሉ።
11. ፤ እንደ ወፍም ከግብጽ፥ እንደ ርግብም ከአሦር ምድር እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ፤ በቤታቸውም አኖራቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
About ሆሴዕ Chapter 11
Read ሆሴዕ Chapter 11 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሆሴዕ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: ሆሴዕ
Chapter: 11
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ሆሴዕ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading ሆሴዕ Chapter 11 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is ሆሴዕ Chapter 11?
ሆሴዕ Chapter 11 is part of the Book of ሆሴዕ in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete ሆሴዕ Chapter 11 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from ሆሴዕ
Explore More from ብሉይ ኪዳን
- ዘኍልቍ Chapter 20
- ኢሳይያስ Chapter 45
- ምሳሌ Chapter 3
- ሕዝቅኤል Chapter 39
- 2 ዜና መዋዕል Chapter 8
- ኢሳይያስ Chapter 52
- አስቴር Chapter 3