1 ሳሙኤል Chapter 29

For English

Read 1 ሳሙኤል Chapter 29 Online

Read 1 ሳሙኤል Chapter 29 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ሳሙኤል in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 1 ሳሙኤል and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

1 ሳሙኤል 29

ምዕራፍ 29

1. ፍልስጥኤማውያንም ጭፍሮቻቸውን ሁሉ ወደ አፌቅ ሰበሰቡ፤ እስራኤላውያንም በኢይዝራኤል ባለው ውኃ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ።

2. ፤ የፍልስጥኤማውያንም አለቆች በመቶ በመቶ በሺህ በሺህ እየሆኑ ያልፉ ነበር፤ ዳዊትና ሰዎቹም ከአንኩስ ጋር በኋለኛው ጭፍራ በኩል ያልፉ ነበር።

3. ፤ የፍልስጥኤማውያንም አለቆች። እነዚህ ዕብራውያን በዚህ ምን ያደርጋሉ? አሉ፤ አንኩስም የፍልስጥኤማውያንን አለቆች። ይህ የእስራኤል ንጉሥ የሳኦል ባሪያ ዳዊት አይደለምን? እርሱም በእነዚህ ቀኖች በእነዚህ ዓመታት ከእኔ ጋር ነበረ፥ ወደ እኔም ከተጠጋበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ምንም አላገኘሁበትም አላቸው።

4. ፤ የፍልስጥኤማውያን አለቆች ግን ተቆጥተው። ይህ ሰው ባስቀመጥኸው ስፍራ ይቀመጥ ዘንድ ይመለስ፤ በሰልፉ ውስጥ ጠላት እንዳይሆነን ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይውረድ፤ ከጌታው ጋር በምን ይታረቃል? የእነዚህን ሰዎች ራስ በመቍረጥ አይደለምን?

5. ፤ ወይስ ሴቶች። ሳኦል ሺህ ገደለ፥ ዳዊት እልፍ ገደለ ብለው በዘፈን የዘመሩለት ይህ ዳዊት አይደለምን? አሉት።

6. ፤ አንኩስም ዳዊትን ጠርቶ። ሕያው እግዚአብሔርን! አንተ ቅን ነህ፥ ከእኔም ጋር በጭፍራው በኩል መውጣትህና መግባትህ በፊቴ መልካም ነው፤ ወደ እኔም ከመጣህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ አንዳች ክፋት አላገኘሁብህም፤ ነገር ግን በአለቆች ዘንድ አልተወደድህም።

7. ፤ አሁንም ተመልሰህ በደኅና ሂድ፥ በፍልስጥኤማውያንም አለቆች ዓይን ክፋት አታድርግ አለው።

8. ፤ ዳዊትም አንኩስን። ምን አድርጌአለሁ? ሄጄስ ከጌታዬ ከንጉሡ ጠላቶች ጋር እንዳልዋጋ፥ በፊትህ ከተቀመጥሁ ጀምሬ እስከ ዛሬ ድረስ በእኔ በባሪያህ ምን አግኝተህብኛል? አለው።

9. ፤ አንኩስም መልሶ ዳዊትን። እንደ አምላክ መልእክተኛ በዓይኔ ፊት መልካም እንደ ሆንህ አውቃለሁ፤ ነገር ግን የፍልስጥኤማውያን አለቆች። ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይወጣም አሉ።

10. ፤ አሁንም አንተ ከአንተም ጋር የመጡ የጌታህ ባሪያዎች ማልዳችሁ ተነሡ፤ ሲነጋም ተነሥታችሁ ሂዱ አለው።

11. ፤ ዳዊትና ሰዎቹም ማልደው ይሄዱ ዘንድ፥ ወደ ፍልስጥኤማውያንም አገር ይመለሱ ዘንድ ተነሡ። ፍልስጥኤማውያንም ወደ ኢይዝራኤል ወጡ።

About 1 ሳሙኤል Chapter 29

Read 1 ሳሙኤል Chapter 29 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ሳሙኤል in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 1 ሳሙኤል
Chapter: 29
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 1 ሳሙኤል. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 1 ሳሙኤል Chapter 29 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 1 ሳሙኤል Chapter 29?

1 ሳሙኤል Chapter 29 is part of the Book of 1 ሳሙኤል in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 1 ሳሙኤል Chapter 29 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 1 ሳሙኤል

  1. 1 ሳሙኤል Chapter 3
  2. 1 ሳሙኤል Chapter 30
  3. 1 ሳሙኤል Chapter 22
  4. 1 ሳሙኤል Chapter 9
  5. 1 ሳሙኤል Chapter 20
  6. 1 ሳሙኤል Chapter 13
  7. 1 ሳሙኤል Chapter 2

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 104
  2. ኢዮብ Chapter 16
  3. ኤርምያስ Chapter 26
  4. ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 4
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 32
  6. መሳፍንት Chapter 20
  7. 1 ነገሥት Chapter 4

Related Chapters & Readings

  1. የሐዋርያት ሥራ Chapter 1
  2. ሕዝቅኤል Chapter 11
  3. አሞጽ Chapter 6
  4. ዘኍልቍ Chapter 11
  5. 1 ጴጥሮስ Chapter 3
  6. የሐዋርያት ሥራ Chapter 12
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 7
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *