Read ኢሳይያስ Chapter 29 Online
Read ኢሳይያስ Chapter 29 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢሳይያስ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኢሳይያስ and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
ኢሳይያስ 29
ምዕራፍ 29
1. ዳዊት ለሰፈረባት ከተማ ለአርኤል ወዮላት! ዓመት በዓመት ላይ ጨምሩ፥ በዓላትም ይመለሱ።
2. ፤ አርኤልንም አስጨንቃለሁ፥ ልቅሶና ዋይታም ይሆንባታል፤ እንደ አርኤልም ትሆንልኛለች።
3. ፤ በዙሪያሽም እሰፍራለሁ፥ በቅጥርም ከብቤ አስጨንቅሻለሁ፥ አምባም በላይሽ አቆማለሁ።
4. ፤ ትዋረጂማለሽ፥ በመሬትም ላይ ሆነሽ ትናገሪያለሽ፥ ቃልሽም ዝቅ ብሎ ከአፈር ይወጣል፤ ድምፅሽም ከመሬት እንደሚወጣ እንደ መናፍስት ጠሪ ድምፅ ይሆናል፥ ቃልሽም ከአፈር ወጥቶ ይጮኻል።
5. ፤ ነገር ግን የጠላቶችሽ ብዛት እንደ ደቀቀ ትቢያ፥ የጨካኞችም ብዛት እንደሚያልፍ ገለባ ይሆናል።
6. ፤ ድንገትም ፈጥኖ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በነጐድጓድ፥ በምድርም መናወጥ፥ በታላቅም ድምፅ፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በምትበላም በእሳት ነበልባል ይጐበኛታል።
7. ፤ በአርኤልም ላይ የሚዋጉ፥ እርስዋንና ምሽግዋንም የሚወጉ የሚያስጨንቋትም፥ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት እንደ ሕልምና እንደ ሌሊት ራእይ ይሆናል።
8. ፤ ተርቦም እንደሚያልም ሰው ይሆናል፤ በሕልሙም፥ እነሆ፥ ይበላል፥ ነገር ግን ይነቃል ሰውነቱም ባዶ ነው፤ ተጠምቶም እንደሚያልም ሰው ይሆናል፤ በሕልሙም፥ እነሆ፥ ይጠጣል፥ ነገር ግን ይነቃል፥ እነሆም፥ ይዝላል ሰውነቱም አምሮት አለው፤ እንዲሁ የጽዮንን ተራራ የሚወጉ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት ይሆናል።
9. ፤ ተደነቁ ደንግጡም፤ ተጨፈኑም ዕውሮችም ሁኑ፤ በወይን ጠጅ አይሁን እንጂ ሰከሩ፤ በሚያሰክር መጠጥ አይሁን እንጂ ተንገደገዱ።
10. ፤ እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል ዓይኖቻችሁን ነቢያትንም ጨፍኖባችኋል ራሶቻችሁን ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል።
11. ፤ ራእዩም ሁሉ እንደ ታተመ መጽሐፍ ቃል ሆኖባችኋል፤ ማንበብንም ለሚያውቅ። ይህን አንብብ ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ። ታትሞአልና አልችልም ይላቸዋል፤
12. ፤ ደግሞም መጽሐፉን ማንበብን ለማያውቅ። ይህን አንብብ ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ። ማንበብ አላውቅም ይላቸዋል።
13. ፤ ጌታም። ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባልና፥ በከንፈርቹም ያከብረኛልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፥ በሰዎች ሥርዓትና ትምህርት ብቻ ይፈራኛልና
14. ፤ ስለዚህ፥ እነሆ፥ ድንቅ ነገርን በዚህ ሕዝብ መካከል፥ ድንቅ ነገርን ተአምራትንም፥ እንደ ገና አደርጋለሁ፤ የጥበበኞችም ጥበብ ትጠፋለች፥ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትሰወራለች።
15. ፤ ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ፥ ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው። ማን ያየናል? ወይስ ማን ያውቀናል? ለሚሉ ወዮላቸው!
16. ፤ ይህ የእናንተ ጠማምነት ነው፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃ የምትቈጠሩ አይደላችሁምን? በውኑ ሥራ ሠሪውን። አልሠራኸኝም ይለዋልን? ወይስ የተደረገው አድራጊውን። አታስተውልም ይለዋልን?
17. ፤ ሊባኖስ እንደ ፍሬያማ እርሻ ሊለወጥ ፍሬያማውም እርሻ እንደ ዱር ሊቈጠር ጥቂት ዘመን የቀረ አይደለምን?
18. ፤ በዚያም ቀን ደንቆሮች የመጽሐፍን ቃል ይሰማሉ፥ የዕውሮችም ዓይኖች ከጭጋግና ከጨለማ ተለይተው ያያሉ።
19. ፤ የዋሃን ደስታቸውን በእግዚአብሔር ያበዛሉ፥ በሰዎች መካከል ያሉ ችግረኞችም ሐሤትን በእስራኤል ቅዱስ ያደርጋሉ።
20. ፤ ጨካኙ ሰው አልቆአልና፥ ፌዘኛውም ጠፍቶአልና፥ ለኃጢአትም የደፈጡ ሁሉ ይቈረጣሉና፤
21. ፤ እነዚህም ሰውን በነገር በደለኛ የሚያደርጉ፥ በበርም ለሚገሥጸው አሽክላ የሚያኖሩ፥ ጻድቁንም በከንቱ ነገር የሚያስቱ ናቸው።
22. ፤ ስለዚህ አብርሃምን የተቤዠ እግዚአብሔር ስለ ያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል። ያዕቆብ አሁን አያፍርም፥ ፊቱም አሁን አይለወጥም።
23. ፤ ነገር ግን የእጄን ሥራ ልጆቹን በመካከሉ ባያቸው ጊዜ ስሜን ይቀድሳሉ፤ የያዕቆብንም ቅዱስ ይቀድሳሉ፥ የእስራኤልንም አምላክ ይፈራሉ።
24. ፤ በመንፈስም የሳቱ ማስተዋልን ያውቃሉ፥ የሚያጕረመርሙም ትምህርትን ይቀበላሉ።
About ኢሳይያስ Chapter 29
Read ኢሳይያስ Chapter 29 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢሳይያስ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: ኢሳይያስ
Chapter: 29
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኢሳይያስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading ኢሳይያስ Chapter 29 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is ኢሳይያስ Chapter 29?
ኢሳይያስ Chapter 29 is part of the Book of ኢሳይያስ in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete ኢሳይያስ Chapter 29 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from ብሉይ ኪዳን
Explore More from ኢሳይያስ
- ኢሳይያስ Chapter 12
- ኢሳይያስ Chapter 19
- ኢሳይያስ Chapter 30
- ኢሳይያስ Chapter 61
- ኢሳይያስ Chapter 50
- ኢሳይያስ Chapter 27
- ኢሳይያስ Chapter 39