ኢሳይያስ Chapter 46

For English

Read ኢሳይያስ Chapter 46 Online

Read ኢሳይያስ Chapter 46 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢሳይያስ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኢሳይያስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ኢሳይያስ 46

ምዕራፍ 46

1. ቤል ተዋረደ፥ ናባው ተሰባበረ፤ ጣዖቶቻቸው በእንስሳና በከብት ላይ ተጭነዋል፤ ሸክሞቻችሁ ለደካማ እንስሳ ከባድ ጭነት ሆነዋል።

2. ፤ ተጐነበሱ በአንድነትም ተዋረዱ፤ ሸክሙን ለማዳን አልቻሉም፥ ራሳቸው ግን ተማረኩ።

3. ፤ እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ የእስራኤልም ቤት ቅሬታ ሁሉ፥ ከሆድ ያነሣኋችሁ ከማኅፀንም የተሸከምኋችሁ፥ ስሙኝ።

4. ፤ እስከ ሽምግልና ድረስ እኔ ነኝ፥ እስከ ሽበትም ድረስ እሸከማችኋለሁ፤ እኔ ሠርቻለሁ እኔም አነሣለሁ፤ እኔ እሸከማለሁ እኔም አድናለሁ።

5. ፤ በማን ትመስሉኛላችሁ? ከማንስ ጋር ታስተካክሉኛላችሁ? እንመሳሰል ዘንድ ከማን ጋር ታስተያዩኛላችሁ?

6. ፤ ወርቁን ከኮረጆ የሚያፈስሱ ብሩንም በሚዛን የሚመዝኑ እነርሱ አንጥረኛውን ይቀጥራሉ፥ እርሱም አምላክ አድርጎ ይሠራ ዋል፤ ለዚያም ይጐነበሱለታል ይሰግዱለትማል።

7. ፤ በጫንቃቸው ላይ አንሥተው ይሸከሙታል በስፍራውም ያደርጉታል፥ በዚያም ይቆማል፥ ከስፍራውም ፈቀቅ አይልም፤ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮኽ አይሰማውም ከመከራውም አያድነውም።

8. ፤ ይህን አስቡና አልቅሱ፤ ተላላፊዎች ሆይ፥ ንስሐ ግቡ፥ ልባችሁንም መልሱ።

9. ፤ እኔ አምላክ ነኝና፥ ሌላም የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስቡ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።

10. ፤ በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እነግራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ እላለሁ።

11. ፤ ከምሥራቅ ነጣቂ ወፍን፥ ከሩቅም አገር ምክሬን የሚያደርገውን ሰው እጠራዋለሁ። ተናግሬአለሁ፤ እፈጽማለሁ፤ አስቤአለሁ አደርግማለሁ።

12. ፤ እናንተ ከጽድቅ የራቃችሁ እልከኞች፥ ስሙኝ፤

13. ፤ ጽድቄን አቀርባለሁ፥ አይርቅም መድኃኒቴም አይዘገይም፤ ከጽዮን ለክብር እንዲሆን መድኃኒትን ለእስራኤል ሰጥቻለሁ።

About ኢሳይያስ Chapter 46

Read ኢሳይያስ Chapter 46 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢሳይያስ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ኢሳይያስ
Chapter: 46
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኢሳይያስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ኢሳይያስ Chapter 46 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ኢሳይያስ Chapter 46?

ኢሳይያስ Chapter 46 is part of the Book of ኢሳይያስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ኢሳይያስ Chapter 46 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ብሉይ ኪዳን

  1. አሞጽ Chapter 4
  2. አሞጽ Chapter 1
  3. አሞጽ Chapter 3
  4. አሞጽ Chapter 6
  5. አሞጽ Chapter 2
  6. አሞጽ Chapter 7
  7. አሞጽ Chapter 5

Explore More from ኢሳይያስ

  1. ኢሳይያስ Chapter 9
  2. ኢሳይያስ Chapter 51
  3. ኢሳይያስ Chapter 61
  4. ኢሳይያስ Chapter 15
  5. ኢሳይያስ Chapter 6
  6. ኢሳይያስ Chapter 20
  7. ኢሳይያስ Chapter 41

Related Chapters & Readings

  1. የሐዋርያት ሥራ Chapter 7
  2. የሐዋርያት ሥራ Chapter 10
  3. ኤፌሶን Chapter 4
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 22
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 73
  6. 1 ዜና መዋዕል Chapter 22
  7. ዘፍጥረት Chapter 41
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *