ሮሜ Chapter 3

For English

Read ሮሜ Chapter 3 Online

Read ሮሜ Chapter 3 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሮሜ in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ሮሜ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

A+ A A-

ሮሜ 3

ምዕራፍ 3

1. እንግዲህ የአይሁዳዊ ብልጫው ምንድር ነው? ወይስ የመገረዝ ጥቅሙ ምንድር ነው? በሁሉ ነገር ብዙ ነው።

2. አስቀድሞ የእግዚአብሔር ቃላት አደራ ተሰጡአቸው። ታዲያ ምንድር ነው?

3. የማያምኑ ቢኖሩ አለማመናቸው የእግዚአብሔርን ታማኝነት ያስቀራልን?

4. እንዲህ አይሁን፤ በቃልህ ትጸድቅ ዘንድ ወደ ፍርድ በገባህም ጊዜ ትረታ ዘንድ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ሰው ሁሉ ውሸተኛ ከሆነ እግዚአብሔር እውነተኛ ይሁን።

5. ነገር ግን ዓመፃችን የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚያስረዳ ከሆነ ምን እንላለን? ቍጣን የሚያመጣ እግዚአብሔር ዓመፀኛ ነውን? እንደ ሰው ልማድ እላለሁ።

6. እንዲህ አይሁን፤ እንዲህ ቢሆን እግዚአብሔር በዓለም እንዴት ይፈርዳል?

7. በእኔ ውሸት ግን የእግዚአብሔር እውነት ለክብሩ ከላቀ ስለምን በእኔ ደግሞ እንደ ኃጢአተኛ ገና ይፈርድብኛል?

8. ስለ ምንስ መልካም እንዲመጣ ክፉ አናደርግም? እንዲሁ ይሰድቡናልና አንዳንዱም እንዲሁ እንድንል ይናገራሉና። የእነርሱም ፍርድ ቅን ነው።

9. እንግዲህ ምን ይሁን? ከእነርሱ እንበልጣለንን? ከቶ አይደለም፤ አይሁድም የግሪክ ሰዎችም ሁሉ ከኃጢአት በታች እንደ ሆኑ አስቀድመን ከሰናቸዋልና፤

10. እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ።

11. ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ፤ አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፤ ሁሉ ተሳስተዋል፥

12. በአንድነትም የማይጠቅሙ ሆነዋል፤ ቸርነት የሚያደርግ የለም፥ አንድ ስንኳ የለም።

13. ጕሮሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፥ በመላሳቸውም ሸንግለዋል፤ የእባብ መርዝ ከከንፈሮቻቸው በታች አለ፤

14. አፋቸውም እርግማንና መራርነት ሞልቶበታል፤

15. እግሮቻቸው ደምን ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው፤

16. ጥፋትና ጉስቁልና በመንገዳቸው ይገኛል፥

17.

18. የሰላምንም መንገድ አያውቁም። በዓይኖቻቸው ፊት እግዚአብሔርን መፍራት የለም።

19. አፍም ሁሉ ይዘጋ ዘንድ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንዲናገር እናውቃለን፤

20. ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና።

21. አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥

22. እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤

23. ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤

24. በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።

25. እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፥

26. ራሱም ጻድቅ እንዲሆን በኢየሱስም የሚያምነውን እንዲያጸድቅ አሁን በዚህ ዘመን ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው።

27. ትምክህት እንግዲህ ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል። በየትኛው ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፥ በእምነት ሕግ ነው እንጂ።

28. ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና።

29.

30. ወይስ እግዚአብሔር የአይሁድ ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ ደግሞ አምላክ አይደለምን? አዎን፥ የተገረዘን ስለ እምነት ያልተገረዘንም በእምነት የሚያጸድቅ አምላክ አንድ ስለ ሆነ የአሕዛብ ደግሞ አምላክ ነው።

31. እንግዲህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? አይደለም፤ ሕግን እናጸናለን እንጂ።

About ሮሜ Chapter 3

Read ሮሜ Chapter 3 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሮሜ in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ሮሜ
Chapter: 3
Testament: New Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ሮሜ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ሮሜ Chapter 3 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ሮሜ Chapter 3?

ሮሜ Chapter 3 is part of the Book of ሮሜ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ሮሜ Chapter 3 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ሮሜ

  1. ሮሜ Chapter 13
  2. ሮሜ Chapter 7
  3. ሮሜ Chapter 6
  4. ሮሜ Chapter 16
  5. ሮሜ Chapter 8
  6. ሮሜ Chapter 2
  7. ሮሜ Chapter 10

Explore More from አዲስ ኪዳን

  1. 1 ጢሞቴዎስ Chapter 1
  2. ሉቃስ Chapter 11
  3. ማቴዎስ Chapter 13
  4. 1 ጢሞቴዎስ Chapter 4
  5. ሉቃስ Chapter 22
  6. ቆላስይስ Chapter 1
  7. ማቴዎስ Chapter 18

Related Chapters & Readings

  1. 1 ዮሐንስ Chapter 1
  2. ሕዝቅኤል Chapter 29
  3. ዳንኤል Chapter 11
  4. ዘኍልቍ Chapter 10
  5. የሐዋርያት ሥራ Chapter 27
  6. መዝሙረ ዳዊት Chapter 136
  7. ኢሳይያስ Chapter 61
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *