ዕብራውያን Chapter 13

For English

Read ዕብራውያን Chapter 13 Online

Read ዕብራውያን Chapter 13 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ዕብራውያን in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ዕብራውያን and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ዕብራውያን 13

ምዕራፍ 13

1. ወንድማማች መዋደድ ይኑር።

2. የ እንግዶችን መቀበል አትርሱ፤ በዚህ አንዳንዶች ሳያውቁ መላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልና።

3. ከእነርሱ ጋር እንደ ታሰረ ሆናችሁ እስሮችን አስቡ፥ የተጨነቁትንም ራሳችሁ ደግሞ በሥጋ እንዳለ ሆናችሁ አስቡ።

4. መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።

5. አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ። አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤

6. ስለዚህ በድፍረት። ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል? እንላለን።

7. የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።

8. ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።

9. ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምህርት አትወሰዱ፤ ልባችሁ በጸጋ ቢጸና መልካም ነው እንጂ በመብል አይደለም፤ በዚህ የሚሠሩባት አልተጠቀሙምና።

10. መሠዊያ አለን፥ ከእርሱም ሊበሉ ድንኳኒቱን የሚያገለግሉ መብት የላቸውም።

11. ሊቀ ካህናት ስለ ኃጢአት ወደ ቅድስት የእንስሶችን ደም ያቀርባልና፤ ሥጋቸው ግን ከሰፈሩ ውጭ ይቃጠላል።

12. ስለዚህ ኢየሱስ ደግሞ በገዛ ደሙ ሕዝቡን እንዲቀድስ ከበር ውጭ መከራን ተቀበለ።

13. እንግዲህ ነቀፌታውን እየተሸከምን ወደ እርሱ ወደ ሰፈሩ ውጭ እንውጣ፤

14. በዚህ የምትኖር ከተማ የለችንምና፥ ነገር ግን ትመጣ ዘንድ ያላትን እንፈልጋለን።

15. እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት፥ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ በእርሱ እናቅርብለት።

16. ነገር ግን መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና።

17. ለዋኖቻችሁ ታዘዙና ተገዙ፤ እነርሱ ስሌትን እንደሚሰጡ አድርገው፥ ይህንኑ በደስታ እንጂ በኃዘን እንዳያደርጉት፥ ይህ የማይጠቅማችሁ ነበርና፥ ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ።

18. ጸልዩልን፤ በነገር ሁሉ በመልካም እንድንኖር ወደን፥ መልካም ሕሊና እንዳለን ተረድተናልና።

19. ይልቁንም ፈጥኜ እንድመለስላችሁ ይህን ታደርጉ ዘንድ አጥብቄ እለምናችኋለሁ።

20. በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ፥

21. በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።

22. ወንድሞች ሆይ፥ የምክርን ቃል እንድትታገሡ እመክራችኋለሁ፥ በጥቂት ቃል ጽፌላችኋለሁና።

23. ወንድማችን ጢሞቴዎስ እንደ ተፈታ እወቁ፥ ቶሎ ብሎም ቢመጣ ከእርሱ ጋር አያችኋለሁ።

24. ለዋኖቻችሁ ሁሉና ለቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከኢጣልያ የሆኑቱ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

25. ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።

About ዕብራውያን Chapter 13

Read ዕብራውያን Chapter 13 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ዕብራውያን in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ዕብራውያን
Chapter: 13
Testament: New Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ዕብራውያን. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ዕብራውያን Chapter 13 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ዕብራውያን Chapter 13?

ዕብራውያን Chapter 13 is part of the Book of ዕብራውያን in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ዕብራውያን Chapter 13 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from አዲስ ኪዳን

  1. 2 ቆሮንቶስ Chapter 7
  2. ሉቃስ Chapter 7
  3. 2 ቆሮንቶስ Chapter 1
  4. 2 ቆሮንቶስ Chapter 6
  5. 2 ቆሮንቶስ Chapter 5
  6. 2 ቆሮንቶስ Chapter 2
  7. ሉቃስ Chapter 24

Explore More from ዕብራውያን

  1. ዕብራውያን Chapter 10
  2. ዕብራውያን Chapter 5
  3. ዕብራውያን Chapter 2
  4. ዕብራውያን Chapter 8
  5. ዕብራውያን Chapter 6
  6. ዕብራውያን Chapter 11
  7. ዕብራውያን Chapter 1

Related Chapters & Readings

  1. ሕዝቅኤል Chapter 3
  2. 2 ዜና መዋዕል Chapter 35
  3. ዘጸአት Chapter 29
  4. ዕብራውያን Chapter 4
  5. ኢሳይያስ Chapter 34
  6. 2 ሳሙኤል Chapter 22
  7. ነህምያ Chapter 8
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *