ያዕቆብ Chapter 1

For English

Read ያዕቆብ Chapter 1 Online

Read ያዕቆብ Chapter 1 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ያዕቆብ in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ያዕቆብ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

A+ A A-

ያዕቆብ 1

ምዕራፍ 1

1. የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን።

2.

3. ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት

4. ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም።

5. ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል።

6. ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና።

7.

8. ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው።

9.

10. የተዋረደው ወንድም ግን በከፍታው፥ ባለ ጠጋም በውርደቱ ይመካ፤ እንደ ሣር አበባ ያልፋልና።

11. ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥ ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል።

12. በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።

13. ማንም ሲፈተን። በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም።

14. ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።

15. ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።

16. የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ።

17. በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።

18. ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።

19. ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤

20. የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና።

21. ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።

22. ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።

23. ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤

24. ራሱን አይቶ ይሄዳልና፥ ወዲያውም እንደ ምን እንደ ሆነ ይረሳል።

25. ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል።

26. አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው።

27. ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።

About ያዕቆብ Chapter 1

Read ያዕቆብ Chapter 1 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ያዕቆብ in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ያዕቆብ
Chapter: 1
Testament: New Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ያዕቆብ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ያዕቆብ Chapter 1 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ያዕቆብ Chapter 1?

ያዕቆብ Chapter 1 is part of the Book of ያዕቆብ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ያዕቆብ Chapter 1 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from አዲስ ኪዳን

  1. 2 ቆሮንቶስ Chapter 1
  2. ሉቃስ Chapter 7
  3. 2 ቆሮንቶስ Chapter 7
  4. 2 ቆሮንቶስ Chapter 5
  5. 2 ቆሮንቶስ Chapter 2
  6. 2 ቆሮንቶስ Chapter 6
  7. 2 ቆሮንቶስ Chapter 3

Explore More from ያዕቆብ

  1. ያዕቆብ Chapter 4
  2. ያዕቆብ Chapter 2
  3. ያዕቆብ Chapter 3
  4. ያዕቆብ Chapter 5

Related Chapters & Readings

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 76
  2. 1 ቆሮንቶስ Chapter 3
  3. መኃልየ መኃልይ Chapter 2
  4. ኢሳይያስ Chapter 4
  5. ኢያሱ Chapter 2
  6. 2 ዜና መዋዕል Chapter 15
  7. 1 ሳሙኤል Chapter 6
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *