2 ዜና መዋዕል Chapter 34

For English

Read 2 ዜና መዋዕል Chapter 34 Online

Read 2 ዜና መዋዕል Chapter 34 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ዜና መዋዕል in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 2 ዜና መዋዕል and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

2 ዜና መዋዕል 34

ምዕራፍ 34

1. ኢዮስያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የስምንት ዓመት ልጅ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ አንድ ዓመት ነገሠ።

2. ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ቅን ነገር አደረገ፥ በአባቱም በዳዊት መንገድ ሄደ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላለም።

3. ፤ በነገሠም በስምንተኛው ዓመት ገና ብላቴና ሳለ የአባቱን የዳዊትን አምላክ ይፈልግ ጀመር፤ በአሥራ ሁለተኛውም ዓመት ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ከኮረብታው መስገጃዎችና ከማምለኪያ ዐፀዶቹ፥ ከተቀረጹትና ቀልጠው ከተሠሩት ምስሎች ያነጻ ጀመር።

4. ፤ የበኣሊምንም መሠዊያዎች በፊቱ አፈረሱ፤ በላዩም የነበሩትን የፀሐዩን ምስሎች የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ቈረጠ፤ የተቀረጹትንና ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎች ሰባበረ፥ አደቀቃቸውም፥ ይሠዉላቸው በነበሩት ሰዎች መቃብርም ላይ በተናቸው።

5. ፤ የካህናቶቻቸውንም አጥንት በመሠዊያቸው ላይ አቃጠለ፤ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን አንጻ።

6. ፤ የምናሴንና የኤፍሬምንም የስምዖንና የንፍታሌምንም ከተሞች፥ በዙሪያቸውም ያለውን ቦታ እንዲሁ አነጻ።

7. ፤ መሠዊያዎቹንም አፈረሰ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቹንና የተቀረጹትን ምስሎች አደቀቀ፥ በእስራኤልም አገር ሁሉ የፀሐይን ምስሎች ሁሉ ቈራረጠ፥ ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሰ።

8. ፤ በነገሠም በአሥራ ስምንተኛው ዓመት ምድሪቱንና የእግዚአብሔርን ቤት ካነጻ በኋላ፥ የኤዜልያስ ልጅ ሳፋን፥ የከተማይቱም አለቃ መዕሤያ፥ ታሪክ ጸሐፊም የኢዮአካዝ ልጅ ኢዮአክ የእግዚአብሔርን የአምላኩን ቤት ይጠግኑ ዘንድ ሰደዳቸው።

9. ፤ ወደ ታላቁም ካህን ወደ ኬልቅያስ መጡ፤ ሌዋውያኑም በረኞች ከምናሴና ከኤፍሬም ከቀረውም ከእስራኤል ሁሉ፥ ከይሁዳና ከብንያም ሁሉ በኢየሩሳሌምም ከሚኖሩት የሰበሰቡትን፥ ወደ እግዚእብሔር ቤት የቀረበውን ገንዘብ ሰጡት።

10. ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት በሚሠሩት ላይ ለተሾሙት ሰጡ፤ እነርሱም ይጠግኑና ያድሱ ዘንድ፥ የእግዚአብሔርን ቤት ለሚሠሩ ሠራተኞች ሰጡ።

11. ፤ የይሁዳ ነገሥታት ላፈረሱት ቤት ሰረገሎች ያደርጉ ዘንድ፥ ለማጋጠሚያም እንጨት የተጠረበውንም ድንጋይ ይገዙ ዘንድ ለአናጢዎችና ለጠራቢዎች ሰጡ።

12. ፤ ሰዎቹም ሥራውን በመታመን አደረጉ፤ በእነርሱም ላይ የተሾሙት፥ ሥራውንም የሚያሠሩት ሌዋውያን ከሜራሪ ልጆች ኢኤትና አብድዩ፥ ከቀዓትም ልጆች ዘካርያስና ሜሱላም ነበሩ። ከሌዋውያንም ወገን በዜማ ዕቃ አዋቂዎች የነበሩ ሁሉ

13. ፤ በተሸካሚዎችና ልዩ ልዩ ሥራ በሚሠሩ ላይ ተሾመው ነበር፤ ጸሐፊዎቹና አለቆቹም በረኞቹም ከሌዋውያን ወገን ነበሩ።

14. ፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት የቀረበውን ገንዘብ ባመጡ ጊዜ ካህኑ ኬልቅያስም በሙሴ እጅ የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ አገኘ።

15. ፤ ኬልቅያስም ጸሐፊውን ሳፋንን። የሕጉን መጽሐፍ በእግዚአብሔር ቤት አግኝቼአለሁ ብሎ ተናገረው። ኬልቅያስም መጽሐፉን ለሳፋን ሰጠው።

16. ፤ ሳፋንም መጽሐፉን ወደ ንጉሡ አመጣ፤ ለንጉሡም። ባሪያዎችህ የተሰጣቸውን ትእዛዝ ሁሉ ያደርጋሉ፤

17. ፤ በእግዚአብሔርም ቤት የተገኘውን ገንዘብ አፈሰሱ፥ በሥራውም ላይ ለተሾሙትና ለሠራተኞቹ ሰጡ ብሎ አወራለት።

18. ፤ ጸሐፊውም ሳፋን ለንጉሡ። ካህኑ ኬልቅያስ መጽሐፍ ሰጠኝ ብሎ ነገረው። ሳፋንም በንጉሡ ፊት አነበበው።

19. ፤ ንጉሡም የሕጉን ቃል በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀደደ።

20. ፤ ንጉሡም ኬልቅያስን፥ የሳፋንንም ልጅ አኪቃምን፥ የሚክያስንም ልጅ ዓብዶንን፥ ጸሐፊውንም ሳፋንን፥ የንጉሡንም ብላቴና ዓሳያን።

21. ፤ በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ አባቶቻችን የእግዚአብሔርን ቃል ስላልጠበቁ፥ በላያችን የነደደ የእግዚአብሔር ቍጣ እጅግ ነውና ሄዳችሁ ስለ ተገኘው የመጽሐፍ ቃል ለእኔ በእስራኤልና በይሁዳም ለቀሩት እግዚአብሔርን ጠይቁ ብሎ አዘዛቸው።

22. ፤ ኬልቅያስና እነዚያ ንጉሥ ያዘዛቸው ወደ ልብስ ጠባቂው ወደ ሐስራ ልጅ ወደ ቲቁዋ ልጅ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢይቱ ወደ ሕልዳና ሄዱ፤ እርስዋም በኢየሩሳሌም በከተማይቱ በሁለተኛው ክፍል ተቀምጣ ነበር፤ ይህንም ነገር ነገሩአት።

23. ፤ እርስዋም አለቻቸው። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ወደ እኔ ለላካችሁ ሰው እንዲህ ብላችሁ ንገሩት።

24. ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ በይሁዳ ንጉሥ ፊት በተነበበው መጽሐፍ የተጻፉትን ቃላት ሁሉ፥ ማለት ክፉ ነገርን፥ በዚህ ስፍራና በሚኖሩበት ላይ አመጣለሁ።

25. ፤ በእጃቸው ሥራ ሁሉ ሊያስቈጡኝ ትተውኛልና፥ ለሌሎችም አማልክት ዐጥነዋልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ይነድዳል፥ አይጠፋምም።

26. ፤ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ለላካችሁ ለይሁዳ ንጉሥ እንዲህ በሉት። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ስለ ሰማኸው ቃል ልብህ ገር ሆኖአልና፥

27. ፤ በፊቴም ራስህን አዋርደሃልና፥ በዚህም ስፍራና በሚኖሩበት ላይ ቃሌን በሰማህ ጊዜ ራስህን አዋርደሃልና፥ ልብስህንም ቀድደህ በፊቴ አለቅሰሃልና እኔ ደግሞ ሰምቼአለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

28. ፤ እነሆ፥ ወደ አባቶችህ እሰበስብሃለሁ፥ በሰላምም ወደ መቃብርህ ትሰበሰባለህ፤ በዚህም ስፍራና በሚኖሩበት ላይ የማመጣውን ክፉ ነገር ሁሉ ዓይኖችህ አያዩም። ይህንም ለንጉሥ አወሩለት።

29. ፤ ንጉሡም ላከ፥ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምንም ሽማግሌዎች ሁሉ ሰበሰበ።

30. ፤ ንጉሡም የይሁዳም ሰዎች ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩና ካህናቱ፥ ሌዋውያኑም፥ ሕዝቡም ሁሉ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጡ፤ በእግዚአብሔርም ቤት የተገኘውን የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ቃል ሁሉ በጆሮአቸው አነበበ።

31. ፤ ንጉሡም በስፍራው ቆሞ እግዚአብሔርን ተከትሎ እንዲሄድ፥ ትእዛዙንና ምስክሩን ሥርዓቱንም በፍጹም ልቡና በፍጹም ነፍሱ እንዲጠብቅ፥ በዚህም መጽሐፍ የተጻፈውን የቃል ኪዳን ቃል እንዲያደርግ በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረገ።

32. ፤ በኢየሩሳሌምና በብንያምም የተገኙትን ሁሉ በዚህ ነገር አማለ፤ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩት የአባቶቻቸው አምላክ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን እንዳዘዘ አደረጉ።

33. ፤ ኢዮስያስም ከእስራኤል ልጆች ምድር ሁሉ ርኩሱን ሁሉ አስወገደ፥ በእስራኤልም የተገኙትን ሁሉ አምላካቸውን እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ አደረገ። በዘመኑ ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ከመከተል አልራቁም።

About 2 ዜና መዋዕል Chapter 34

Read 2 ዜና መዋዕል Chapter 34 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ዜና መዋዕል in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 2 ዜና መዋዕል
Chapter: 34
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 2 ዜና መዋዕል. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 2 ዜና መዋዕል Chapter 34 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 2 ዜና መዋዕል Chapter 34?

2 ዜና መዋዕል Chapter 34 is part of the Book of 2 ዜና መዋዕል in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 2 ዜና መዋዕል Chapter 34 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 2 ዜና-መዋዕል

  1. 2 ዜና መዋዕል Chapter 14
  2. 2 ዜና መዋዕል Chapter 19
  3. 2 ዜና መዋዕል Chapter 36
  4. 2 ዜና መዋዕል Chapter 24
  5. 2 ዜና መዋዕል Chapter 16
  6. 2 ዜና መዋዕል Chapter 13
  7. 2 ዜና መዋዕል Chapter 31

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 39
  2. ኢሳይያስ Chapter 39
  3. 2 ዜና መዋዕል Chapter 27
  4. ዘጸአት Chapter 10
  5. ኢዮብ Chapter 33
  6. ዘካርያስ Chapter 7
  7. ዳንኤል Chapter 11

Related Chapters & Readings

  1. ኢያሱ Chapter 1
  2. ነህምያ Chapter 1
  3. 2 ዜና መዋዕል Chapter 29
  4. ዘፍጥረት Chapter 19
  5. ዕዝራ Chapter 7
  6. ዕብራውያን Chapter 4
  7. ሕዝቅኤል Chapter 25
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *