2 ዜና መዋዕል Chapter 17

For English

Read 2 ዜና መዋዕል Chapter 17 Online

Read 2 ዜና መዋዕል Chapter 17 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ዜና መዋዕል in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 2 ዜና መዋዕል and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

2 ዜና መዋዕል 17

ምዕራፍ 17

1. በእርሱም ፋንታ ልጁ ኢዮሳፍጥ ነገሠ፥ በእስራኤልም ላይ ጠነከረ።

2. ፤ በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ወታደሮችን አኖረ፥ በይሁዳም አገር አባቱም አሳ በወሰዳቸው በኤፍሬም ከተሞች ዘበኞችን አስቀመጠ።

3. ፤ እግዚአብሔርም ከኢዮሳፍጥ ጋር ነበረ፥ በፊተኛይቱ በአባቱ በዳዊት መንገድ ሄዶአልና፥ በኣሊምንም አልፈለገምና፤

4. ፤ ነገር ግን የአባቱን አምላክ ፈለገ፥ በትእዛዙም ሄደ፥ የእስራኤልንም ሥራ አልሠራም።

5. ፤ እግዚአብሔርም መንግሥቱን በእጁ አጸና፤ ይሁዳም ሁሉ እጅ መንሻ ለኢዮሳፍጥ አመጣ፤ እጅግም ብዙ ብልጥግናና ክብር ሆነለት።

6. ፤ ልቡም በእግዚአብሔር መንገድ ከፍ ከፍ አለ፤ የኮረብታውን መስገጃዎችና የማምለኪያ ዐፀዱንም ከይሁዳ አስወገደ።

7. ፤ በነገሠም በሦስተኛው ዓመት በይሁዳ ከተሞች ያስተምሩ ዘንድ መሳፍንቱን፥ ቤንኃይልን፥ አብድያስን፥ ዘካርያስን፥ ናትናኤልን፥ ሚክያስን፥ ሰደደ።

8. ፤ ከእነርሱም ጋር ሌዋውያንን ሸማያን፥ ነታንያን፥ ዝባድያን፥ አሣሄልን፥ ሰሚራሞትን፥ ዮናትንን፥ አዶንያስን፥ ጦብያን፥ ጦባዶንያን ሰደደ ከእነርሱም ጋር ካህናቱን ኤሊሳማንና ኢዮራምን ሰደደ።

9. ፤ እነርሱም የእግዚአብሔርን የሕጉን መጽሐፍ ይዘው በይሁዳ ያስተምሩ ነበር፤ ወደ ይሁዳም ከተሞች ሁሉ ሄደው ሕዝቡን ያስተምሩ ነበር።

10. ፤ በይሁዳም ዙሪያ በነበሩ መንግሥታት ሁሉ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ድንጋጤ ሆነ፥ ከኢዮሳፍጥም ጋር አልተዋጉም።

11. ፤ ከፍልስጥኤማውያን ለኢዮሳፍጥ እጅ መንሻና የብር ግብር ያመጡ ነበር፤ ዓረባውያንም ደግሞ ከመንጎቻቸው ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ በጎችና ሰባት ሺህ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ ፍየሎች ያመጡለት ነበር።

12. ፤ ኢዮሳፍጥም እየበረታና እጅግም እየከበረ ሄደ፤ በይሁዳም ግንቦችንና የጎተራ ከተሞችን ሠራ።

13. ፤ በይሁዳም ከተሞች ብዙ ሥራ ሠራ፥ በኢየሩሳሌምም ጽኑዓን ኃያላን ሰልፈኞች ነበሩት።

14. ፤ ቍጥራቸውም እንደ አባቶቻቸው ቤት ይህ ነበረ፤ ከይሁዳ ሻለቆች አለቃው ዓድና፥ ከእርሱም ጋር ሦስት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ፤

15. ፤ ከእርሱም በኋላ አለቃው ይሆሐናን፥ ከእርሱም ጋር ሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤

16. ፤ ከእርሱም በኋላ በፈቃዱ ራሱን ለእግዚአብሔር የቀደሰ የዝክሪ ልጅ ዓማስያ፥ ከእርሱም ጋር ሁለት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ።

17. ፤ ከብንያምም ጽኑዕ ኃያል የነበረው ኤሊዳሄ፥ ከእርሱም ጋር ቀስትና ጋሻ የሚይዙ ሁለት መቶ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤

18. ፤ ከእርሱም በኋላ ዮዛባት፥ ከእርሱም ጋር ለሰልፍ የተዘጋጁ መቶ ሰማኒያ ሺህ ሰዎች ነበሩ።

19. ፤ ንጉሡ በተመሸጉ በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ካኖራቸውም ሌላ እነዚህ ንጉሡን ያገለግሉ ነበር።

About 2 ዜና መዋዕል Chapter 17

Read 2 ዜና መዋዕል Chapter 17 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ዜና መዋዕል in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 2 ዜና መዋዕል
Chapter: 17
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 2 ዜና መዋዕል. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 2 ዜና መዋዕል Chapter 17 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 2 ዜና መዋዕል Chapter 17?

2 ዜና መዋዕል Chapter 17 is part of the Book of 2 ዜና መዋዕል in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 2 ዜና መዋዕል Chapter 17 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 2 ዜና-መዋዕል

  1. 2 ዜና መዋዕል Chapter 14
  2. 2 ዜና መዋዕል Chapter 36
  3. 2 ዜና መዋዕል Chapter 24
  4. 2 ዜና መዋዕል Chapter 19
  5. 2 ዜና መዋዕል Chapter 16
  6. 2 ዜና መዋዕል Chapter 13
  7. 2 ዜና መዋዕል Chapter 34

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ኢዮብ Chapter 42
  2. ዘካርያስ Chapter 11
  3. ዘኍልቍ Chapter 24
  4. 2 ነገሥት Chapter 6
  5. ኢያሱ Chapter 7
  6. አሞጽ Chapter 1
  7. ሚልክያስ Chapter 2

Related Chapters & Readings

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 82
  2. ዘፍጥረት Chapter 24
  3. 2 ዜና መዋዕል Chapter 36
  4. ኢሳይያስ Chapter 40
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 59
  6. ዘዳግም Chapter 22
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 64
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *