Read 2 ነገሥት Chapter 16 Online
Read 2 ነገሥት Chapter 16 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ነገሥት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 2 ነገሥት and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
2 ነገሥት 16
ምዕራፍ 16
1. በሮሜልዩ ልጅ በፋቁሔ በአሥራ ሰባተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአታም ልጅ አካዝ ነገሠ።
2. ፤ አካዝ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ ዓመት ጕልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ፤ እንደ አባቱም እንደ ዳዊት በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አላደረገም።
3. ፤ ነገር ግን በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤ ደግሞም እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት እንዳሳደዳቸው እንደ አሕዛብ ርኵሰት ልጁን በእሳት አሳለፈው።
4. ፤ በመስገጃዎችና በኮረብቶቹ ላይ በለመለመውም ዛፍ ሁሉ በታች ይሠዋና ያጥን ነበር።
5. ፤ የዚያን ጊዜም የሶርያ ንጉሥ ረአሶንና የእስራኤል ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ሊዋጉ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ አካዝንም ከበቡት፥ ሊያሸንፉት ግን አልቻሉም።
6. ፤ በዚያም ዘመን የሶርያ ንጉሥ ረአሶን ኤላትን ወደ ሶርያ መለሰ፥ አይሁድንም ከኤላት አሳደደ፤ ኤዶማውያንም ወደ ኤላት መጥተው እስከ ዛሬ ድረስ በእርስዋ ተቀምጠዋል።
7. ፤ አካዝም። እኔ ባሪያህና ልጅህ ነኝ፤ መጥተህ ከተነሡብን ከሶርያ ንጉሥና ከእስራኤል ንጉሥ እጅ አድነኝ ብሎ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ቴልጌልቴልፌልሶር መልእክተኞችን ላከ።
8. ፤ አካዝም በእግዚአብሔር ቤትና በንጉሡ ቤት መዛግብት የተገኘውን ብርና ወርቅ ወስዶ ወደ አሦር ንጉሥ ገጸ በረከት አድርጎ ሰደደው።
9. ፤ የአሦርም ንጉሥ ሰማው፤ የአሦርም ንጉሥ በደማስቆ ላይ ወጣባት ወሰዳትም፥ ሕዝብዋንም ወደ ቂር አፈለሳቸው፥ ረአሶንንም ገደለ።
10. ፤ ንጉሡም አካዝ የአሦርን ንጉሠ ቴልጌልቴልፌልሶርን ሊገናኘው ወደ ደማስቆ ሄደ፤ በደማስቆ የነበረውን መሠዊያ አየ፤ ንጉሡም አካዝ የመሠዊያውን ምሳሌና የአሠራሩን መልክ ወደ ካህኑ ወደ ኦርያ ላከው።
11. ፤ ካህኑም ኦርያ መሠዊያ ሠራ፤ ንጉሡ አካዝ ከደማስቆ ልኮ እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ ካህኑ ኦርያ ንጉሡ አካዝ ከደማስቆ እስኪመጣ ድረስ ሠራው።
12. ፤ ንጉሡም ከደማስቆ በመጣ ጊዜ መሠዊያውን አየ፤ ንጉሡም ወደ መሠዊያው ቀርቦ በእርሱ ላይ ወጣ።
13. ፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን አሳረገ፥ የመጠጡንም ቍርባን አፈሰሰ፥ የደኅንነቱንም መሥዋዕት ደም ረጨ።
14. ፤ በእግዚአብሔርም ፊት የነበረውን የናሱን መሠዊያ ከመቅደሱ ፊት ከመሠዊያውና ከእግዚአብሔር ቤት መካከል ፈቀቅ አድርጎ በመሠውያው አጠገብ በሰሜን በኩል አኖረው።
15. ፤ ንጉሡም አካዝ። የሚቃጠለውን የጥዋት መሥዋዕት፥ የማታውንም የእህሉን ቍርባን፥ የንጉሡንም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን፥ ለአገሩም ሕዝብ የሚሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን የመጠጡንም ቍርባን በታላቁ መሠዊያ ላይ አቅርብ፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ደም ሁሉ የሌላ መሥዋዕቱንም ደም ሁሉ ርጭበት፤ የናሱ መሠዊያ ግን እኔ እጠይቅበት ዘንድ ይሁን ብሎ ካህኑን ኦርያን አዘዘው።
16. ፤ ካህኑ ኦርያ ንጉሡ አካዝ እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ አደረገ።
17. ፤ ንጉሡም አካዝ የመቀመጫዎችን ክፈፍ ቈረጠ፥ ከእነርሱም የመታጠቢያውን ሰኖች ወሰደ፤ ኵሬውንም ከበታቹ ከነበሩት ከናሱ በሬዎች አወረደው፥ በጠፍጣፋውም ድንጋይ ላይ አኖረው።
18. ፤ በእግዚአብሔርም ቤት የዙፋኑን መሠረት ሠራ፤ ስለ አሦርም ንጉሥ በውጭ ያለውን የንጉሡን መንገድ ወደ እግዚአብሔር ቤት አዞረው።
19. ፤ የቀረውም አካዝ ያደረገው ነገር በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
20. ፤ አካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በዳዊትም ከተማ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ፤ ልጁም ሕዝቅያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
About 2 ነገሥት Chapter 16
Read 2 ነገሥት Chapter 16 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ነገሥት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: 2 ነገሥት
Chapter: 16
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 2 ነገሥት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading 2 ነገሥት Chapter 16 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is 2 ነገሥት Chapter 16?
2 ነገሥት Chapter 16 is part of the Book of 2 ነገሥት in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete 2 ነገሥት Chapter 16 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from 2-ነገሥት
- 2 ነገሥት Chapter 12
- 2 ነገሥት Chapter 2
- 2 ነገሥት Chapter 13
- 2 ነገሥት Chapter 3
- 2 ነገሥት Chapter 1
- 2 ነገሥት Chapter 20
- 2 ነገሥት Chapter 15
Explore More from ብሉይ ኪዳን
- ኢሳይያስ Chapter 18
- ሆሴዕ Chapter 4
- ኢሳይያስ Chapter 21
- ዘኍልቍ Chapter 23
- ሕዝቅኤል Chapter 19
- ሕዝቅኤል Chapter 40
- ኢያሱ Chapter 14