Read 2 ነገሥት Chapter 1 Online
Read 2 ነገሥት Chapter 1 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ነገሥት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 2 ነገሥት and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
2 ነገሥት 1
ምዕራፍ 1
1. አክዓብም ከሞተ በኋላ ሞዓብ በእስራኤል ላይ ዐመፀ።
2. ፤ አካዝያስም በሰማርያ በሰገነቱ ላይ ሳለ ከዓይነ ርግቡ ወድቆ ታመመ፤ እርሱም። ሂዱ ከዚህም ደዌ እድን እንደ ሆነ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ጠይቁ ብሎ መልእክተኞችን ላከ።
3. ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ቴስብያዊውን ኤልያስን። ተነሣ፥ የሰማርያን ንጉሥ መልእክተኞች ለመገናኘት ውጣና። የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ትጠይቁ ዘንድ የምትሄዱት በእስራኤል ዘንድ አምላክ ስለሌለ ነውን?
4. ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ትሞታለህ እንጂ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም በላቸው አለው። ኤልያስም ሄደ።
5. ፤ መልእክተኞችም ወደ አካዝያስ ተመለሱ፥ እርሱም። ለምን ተመለሳችሁ? አላቸው።
6. ፤ እነርሱም። አንድ ሰው ሊገናኘን መጣና። ሂዱ፥ ወደ ላካችሁም ንጉሥ ተመልሳችሁ። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ትጠይቅ ዘንድ የላከህ በእስራኤል ዘንድ አምላክ ስለሌለ ነውን? ስለዚህ ትሞታለህ እንጂ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም በሉት አለን አሉት።
7. ፤ እርሱም። ሊገናኛችሁ የወጣው፥ ይህንስ ቃል የነገራችሁ ሰው መልኩ ምን ይመስላል? አላቸው።
8. ፤ እነርሱም። ሰውዮው ጠጕራም ነው፥ በወገቡም ጠፍር ታጥቆ ነበር አሉት። እርሱም። ቴስብያዊው ኤልያስ ነው አለ።
9. ፤ ንጉሡም የአምሳ አለቃውን ከአምሳ ሰዎች ጋር ሰደደ፥ ወደ እርሱም ወጣ፤ እነሆም፥ በተራራ ራስ ላይ ተቀምጦ ነበር። እርሱም። የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ንጉሡ። ውረድ ይልሃል አለው።
10. ፤ ኤልያስም መልሶ የአምሳ አለቃውን። እኔስ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰማይ ትውረድ፥ አንተንም፥ አምሳውንም ሰዎችህን ትብላ አለው። እሳትም ከሰማይ ወርዳ እርሱንና አምሳውን ሰዎቹን በላች።
11. ፤ ደግሞም ሌላ የአምሳ አለቃ ከአምሳ ሰዎች ጋር ላከበት፤ እርሱም። የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ንጉሡ። ፈጥነህ ውረድ ይላል ብሎ ተናገረ።
12. ፤ ኤልያስም። እኔስ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰማይ ትውረድ፥ አንተንም አምሳውንም ሰዎችህን ትብላ አለው። የእግዚአብሔርም እሳት ከሰማይ ወርዳ እርሱንና አምሳውን ሰዎቹን በላች።
13. ፤ ደግሞም ሦስተኛ የአምሳ አለቃ ከአምሳ ሰዎች ጋር ሰደደ፤ ሦስተኛውም የአምሳ አለቃ ወጥቶ በኤልያስ ፊት በጕልበቱ ተንበረከከና። የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ነፍሴና የእነዚህ የአምሳው ባሪያዎችህ ነፍስ በፊትህ የከበረች ትሁን።
14. ፤ እነሆ፥ እሳት ከሰማይ ወርዳ የፊተኞቹን ሁለቱን የአምሳ አለቆችና አምሳ አምሳውን ሰዎቻቸውን በላች፤ አሁን ግን ነፍሴ በፊትህ የከበረች ትሁን ብሎ ለመነው።
15. ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ኤልያስን። ከእርሱ ጋር ውረድ፥ አትፍራውም አለው። ተነሥቶም ከእርሱ ጋር ወደ ንጉሡ ወረደ።
16. ፤ ኤልያስም። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ትጠይቅ ዘንድ መልእክተኞችን ልከሃልና ትሞታለህ እንጂ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም አለው።
17. ፤ ኤልያስም እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ሞተ። ልጅም አልነበረውምና በይሁዳ ንጉሥ በኢዮሣፍጥ ልጅ በኢዮራም በሁለተኛው ዓመት ወንድሙ ኢዮራም በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
18. ፤ አካዝያስ ያደረገው የቀረው ነገር በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
About 2 ነገሥት Chapter 1
Read 2 ነገሥት Chapter 1 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ነገሥት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: 2 ነገሥት
Chapter: 1
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 2 ነገሥት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading 2 ነገሥት Chapter 1 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is 2 ነገሥት Chapter 1?
2 ነገሥት Chapter 1 is part of the Book of 2 ነገሥት in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete 2 ነገሥት Chapter 1 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from 2-ነገሥት
- 2 ነገሥት Chapter 12
- 2 ነገሥት Chapter 2
- 2 ነገሥት Chapter 13
- 2 ነገሥት Chapter 6
- 2 ነገሥት Chapter 3
- 2 ነገሥት Chapter 20
- 2 ነገሥት Chapter 15
Explore More from ብሉይ ኪዳን
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 82
- 1 ሳሙኤል Chapter 20
- ኢዮብ Chapter 11
- ኢዮብ Chapter 40
- ሕዝቅኤል Chapter 20
- ዘኍልቍ Chapter 21
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 27