1 ዜና መዋዕል Chapter 6

For English

Read 1 ዜና መዋዕል Chapter 6 Online

Read 1 ዜና መዋዕል Chapter 6 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ዜና መዋዕል in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 1 ዜና መዋዕል and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

1 ዜና መዋዕል 6

ምዕራፍ 6

1. የሌዊ ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።

2. ፤ የቀዓትም ልጆች፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል።

3. ፤ የእንበረምም ልጆች፤ አሮን፥ ሙሴ፥ ማርያም። የአሮን ልጆች፤ ናዳብ፥ አብዮድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር።

4. ፤ አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቢሱን ወለደ፤

5. ፤ አቢሱም ቡቂን ወለደ፤ ቡቂም ኦዚን ወለደ፤

6. ፤ ኦዚም ዘራእያን ወለደ፤ ዘራእያም መራዮትን ወለደ፤

7. ፤ መራዮት አማርያን ወለደ፤

8. ፤ አማርያም አኪጦብን ወለደ፤ አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪማአስን ወለደ፤

9. ፤ አኪማአስም ዓዛርያስን ወለደ፤

10. ፤ ዓዛርያስም ዮሐናንን ወለደ፤ ዮሐናንም ዓዛርያስን ወለደ፤ እርሱም ሰሎሞን በኢየሩሳሌም በሠራው ቤት ካህን ነበረ፤

11. ፤ ዓዛርያስም አማርያን ወለደ፤ አማርያም አኪጦብን ወለደ፤

12. ፤ አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም ሰሎምን ወለደ፤

13. ፤ ሰሎምም ኬልቅያስን ወለደ፤ ኬልቅያስም ዓዛርያስን ወለደ፤

14. ፤ ዓዛርያስም ሠራያን ወለደ፤ ሠራያም ኢዮሴዴቅን ወለደ፤

15. ፤ እግዚአብሔርም ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን በናቡከደነፆር እጅ ባስማረከ ጊዜ ኢዮሴዴቅ ተማርኮ ሄደ።

16. ፤ የሌዊ ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።

17. ፤ የጌድሶንም ልጆች ስም ይህ ነው፤ ሎቤኒ ሰሜኢ።

18. ፤ የቀዓትም ልጆች፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል ነበሩ።

19. ፤ የሜራሪ ልጆች፤ ሞሖሊም፥ ሙሲ። የሌዋውያን ወገኖች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ናቸው።

20. ፤ ከጌድሶን፤ ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ኢኤት፥ ልጁ ዛማት፥

21. ፤ ልጁ ዮአክ፥ ልጁ አዶ፥ ልጁ ዛራ፥ ልጁ ያትራይ።

22. ፤ የቀዓት ልጆች፤ ልጁ አሚናዳብ፥

23. ፤ ልጁ ቆሬ፥ ልጁ አሴር፥ ልጁ ሕልቃና፥

24. ፤ ልጁ አቢሳፍ፥ ልጁ አሴር፥ ልጁ ኢኢት፥ ልጁ ኡሩኤል፥ ልጁ ዖዝያ፥ ልጁ ሳውል።

25. ፤ የሕልቃናም ልጆች፤ አማሢ፥ አኪሞት።

26. ፤ የሕልቃናም ልጆች፤ ልጁ ሱፊ፥

27. ፤ ልጁ ናሐት፥ ልጁ ኤልያብ፥ ልጁ ይሮሐም፥ ልጁ ሕልቃና።

28. ፤ የሳሙኤልም ልጆች፤ በኵሩ ኢዮኤል፥ ሁለተኛውም አብያ።

29. ፤ የሜራሪ ልጆች፤ ሞሖሊ፥ ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ሰሜኢ፥

30. ፤ ልጁ ዖዛ፥ ልጁ ሳምዓ፥ ልጁ ሐግያ፥ ልጁ ዓሣያ።

31. ፤ ዳዊትም ታቦቱ ዐርፎ ከተቀመጠ በኋላ በእግዚአብሔር ቤት ያቆማቸው የመዘምራን አለቆች እነዚህ ናቸው።

32. ፤ ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በመገናኛ ድንኳን ማደሪያ ፊት እያዜሙ ያገለግሉ ነበር፤ በየተራቸውም ያገለግሉ ነበር።

33. ፤ አገልጋዮቹና ልጆቹ እነዚህ ናቸው፤ ከቀዓት ልጆች ዘማሪው ኤማን ነበረ፤ እርሱም የኢዮኤል ልጅ፥

34. ፤ የሳሙኤል ልጅ፥ የሕልቃና ልጅ፥ የይሮሐም ልጅ፥ የኤሊኤል ልጅ፥ የቶዋ ልጅ፥

35. ፤ የሱፍ ልጅ፥ የሕልቃና ልጅ፥ የመሐት ልጅ፥

36. ፤ የአማሢ ልጅ፥ የሕልቃና ልጅ፥ የኢዮኤል ልጅ፥ የዓዛርያስ ልጅ፥ የሶፎንያስ ልጅ፥

37. ፤ የታሐት ልጅ፥ የአሴር ልጅ፥

38. ፤ የአብያሳፍ ልጅ፥ የቆሬ ልጅ፥ የይስዓር ልጅ፥ የቀዓት ልጅ፥ የሌዊ ልጅ፥ የእስራኤል ልጅ ነው።

39. ፤ በቀኙም የቆመ ወንድሙ አሳፍ ነበረ፤ አሳፍም የበራክያ ልጅ፥

40. ፤ የሳምዓ ልጅ፥ የሚካኤል ልጅ፥ የበዓሤያ ልጅ፥

41. ፤ የመልክያ ልጅ፥ የኤትኒ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥

42. ፤ የዓዳያ ልጅ፥ የኤታን ልጅ፥ የዛማት ልጅ፥

43. ፤ የሰሜኢ ልጅ፥ የኢኤት ልጅ፥ የጌድሶን ልጅ፥ የሌዊ ልጅ ነው።

44. ፤ በግራቸውም በኩል ወንድሞቻቸው የሜራሪ ልጆች ነበሩ፤ ኤታን የቂሳ ልጅ፥ የአብዲ ልጅ፥

45. ፤ የማሎክ ልጅ፥ የሐሸብያ ልጅ፥ የአሜስያስ ልጅ፥

46. ፤ የኬልቅያስ ልጅ፥ የአማሲ ልጅ፥

47. ፤ የባኒ ልጅ፥ የሴሜር ልጅ፥ የሞሖሊ ልጅ፥ የሙሲ ልጅ፥ የሜራሪ ልጅ፥ የሌዊ ልጅ።

48. ፤ ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ለእግዚአብሔር ቤት ማደሪያ አገልግሎት ሁሉ ተሰጡ።

49. ፤ አሮንና ልጆቹ ግን የእግዚአሔር ባሪያ ሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ለቅድስተ ቅዱሳን ሥራ ሁሉ ስለ እስራኤልም ያስተሰርይ ዘንድ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ይሠዉ ነበር፥ በዕጣኑም መሠዊያ ላይ ያጥኑ ነበር።

50. ፤ የአሮንም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ልጁ አልዓዛር፥

51. ፤ ልጁ ፊንሐስ፥ ልጁ አቢሱ፥ ልጁ ቡቂ፥

52. ፤ ልጁ ኦዚ፥ ልጁ ዘራእያ፥ ልጁ መራዮት፥

53. ፤ ልጁ አማርያ፥ ልጁ አኪጦብ፥ ልጁ ሳዶቅ፥ ልጁ አኪማአስ።

54. ፤ ማደሪያዎቻቸውም በየሰፈራቸው በየዳርቻቸው እነዚህ ናቸው፤ ለአሮን ልጆች ለቀዓት ወገኖች አንደኛው ዕጣ ነበረ።

55. ፤ ለእነርሱ በይሁዳ አገር ያለችውን ኬብሮንን፥ በእርስዋም ዙሪያ የነበረውን መሰምርያ ሰጡ፤

56. ፤ የከተማይቱን እርሻ ግን መንደሮችዋንም ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ሰጡ።

57. ፤ ለአሮንም ልጆች የመማፀኛውን ከተሞች፥ ኬብሮንን፥ ልብናንና መሰምርያዋን፥ ደግሞ የቲርን፥

58. ፤ ኤሽትሞዓንና መሰምርያዋን፥ ሖሎንንና መሰምርያዋን፥ ዳቤርንና መሰምርያዋን፥

59. ፤ ዓሳንንና መሰምርያዋን፥ ቤትሳሚስንና መሰምርያዋን፤

60. ፤ ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰምርያዋን፥ ጋሌማትንና መሰምርያዋን፥ ዓናቶትንና መሰምርያዋን ሰጡ። ከተሞቻተው ሁሉ በየወገናቸው አሥራ ሦስት ነበሩ።

61. ፤ ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከነገዱ ወገን ከምናሴ ነገድ እኵሌታ አሥር ከተሞች በዕጣ ተሰጡ።

62. ፤ ለጌድሶንም ልጆች በየወገናቸው ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ፥ አሥራ ሦስት ከተሞች ተሰጡ።

63. ፤ ለሜራሪ ልጆች በየወገናቸው ከሮቤል ነገድ፥ ከጋድም ነገድ፥ ከዛብሎንም ነገድ፥ አሥራ ሁለት ከተሞች በዕጣ ተሰጡ።

64. ፤ የእስራኤልም ልጆች ለሌዋውያን ከተሞችን ከመሰምርያዎቻቸው ጋር ሰጡ።

65. ፤ ከይሁዳም ልጆች ነገድ፥ ከስምዖንም ልጆች ነገድ፥ ከብንያምም ልጆች ነገድ፥ እነዚህን በስማቸው የተጠሩትን ከተሞች በዕጣ ሰጡ።

66. ፤ ከቀዓትም ልጆች ወገኖች ለአንዳንዶቹ ከኤፍሬም ነገድ ከተሞች ድርሻ ነበራቸው።

67. ፤ በተራራማው በኤፍሬም አገር ያሉትን የመማፀኛውን ከተሞች ሴኬምንና መሰምርያዋን፥ ደግሞም ጌዝርንና መሰምርያዋን፥ ዮቅምዓምንና መሰምርያዋን፥

68. ፤ ቤትሖሮንንና መሰምርያዋን፥

69. ፤ ኤሎንንና መሰምርያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰምርያዋን ሰጡአቸው።

70. ፤ ከምናሴም ነገድ እኵሌታ ዓኔርንና መሰምርያዋን፥ ቢልዓምንና መሰምርያዋን ከቀዓት ልጆች ወገን ለቀሩት ሰጡ።

71. ፤ ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኵሌታ ወገን በባሳን ያለችው ጎላንና መሰምርያዋ፥ አስታሮትና መሰምርያዋ፤

72. ፤ ከይሳኮርም ነገድ ቃዴስና መሰምርያዋ፥ ዳብራትና መሰምርያዋ፥

73. ፤ ራሞትና መሰምርያዋ፥ ዓኔምና መሰምርያዋ፤

74. ፤ ከአሴርም ነገድ መዓሳልና መሰምርያዋ፥ ዓብዶንና መሰምርያዋ፥

75. ፤ ሑቆቅና መሰምርያዋ፥ ረአብና መሰምርያዋ፤

76. ፤ ከንፍታሌምም ነገድ በገሊላ ያለችው ቃዴስና መሰምርያዋ፥ ሐሞንና መሰምርያዋ፥ ቂርያታይምና መሰምርያዋ ተሰጡ።

77. ፤ ከሌዋውያን ለቀሩት ለሜራሪ ልጆች ከዛብሎን ነገድ ሬሞንና መሰምርያዋ፥ ታቦርና መሰምርያዋ፤

78. ፤ ከሮቤልም ነገድ በኢያሪኮ አንጻር በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል በምድረ በዳ ያለችው ቦሶርና መሰምርያዋ፥

79. ፤ ያሳና መሰምርያዋ፥ ቅዴሞትና መሰምርያዋ፥ ሜፍዓትና መሰምርያዋ፤

80. ፤ ከጋድም ነገድ በገለዓድ ያለችው ሬማትና መሰምርያዋ፥ መሃናይምና መሰምርያዋ፥

81. ፤ ሐሴቦንና መሰምርያዋ፥ ኢያዜርና መሰምርያዋ ተሰጡ።

About 1 ዜና መዋዕል Chapter 6

Read 1 ዜና መዋዕል Chapter 6 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ዜና መዋዕል in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 1 ዜና መዋዕል
Chapter: 6
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 1 ዜና መዋዕል. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 1 ዜና መዋዕል Chapter 6 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 1 ዜና መዋዕል Chapter 6?

1 ዜና መዋዕል Chapter 6 is part of the Book of 1 ዜና መዋዕል in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 1 ዜና መዋዕል Chapter 6 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 1-ዜና-መዋዕል

  1. 1 ዜና መዋዕል Chapter 2
  2. 1 ዜና መዋዕል Chapter 15
  3. 1 ዜና መዋዕል Chapter 13
  4. 1 ዜና መዋዕል Chapter 27
  5. 1 ዜና መዋዕል Chapter 25
  6. 1 ዜና መዋዕል Chapter 12
  7. 1 ዜና መዋዕል Chapter 7

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ኢያሱ Chapter 12
  2. ዕዝራ Chapter 8
  3. አስቴር Chapter 3
  4. 1 ዜና መዋዕል Chapter 23
  5. ምሳሌ Chapter 22
  6. ምሳሌ Chapter 29
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 2

Related Chapters & Readings

  1. ሆሴዕ Chapter 10
  2. 2 ዮሐንስ Chapter 1
  3. ሕዝቅኤል Chapter 10
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 138
  5. ሕዝቅኤል Chapter 12
  6. ዘጸአት Chapter 7
  7. ሆሴዕ Chapter 9
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *