2 ሳሙኤል Chapter 9

For English

Read 2 ሳሙኤል Chapter 9 Online

Read 2 ሳሙኤል Chapter 9 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ሳሙኤል in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 2 ሳሙኤል and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

2 ሳሙኤል 9

ምዕራፍ 9

1. ዳዊትም። ስለ ዮናታን ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳኦል ቤት አንድ ሰው ቀርቶአልን? አለ።

2. ፤ ከሳኦልም ቤት ሲባ የሚባል አንድ ባሪያ ነበረ፥ ወደ ዳዊትም ጠሩት፤ ንጉሡም። አንተ ሲባ ነህን? አለው። እርሱም። እኔ ባሪያህ ነኝ አለ።

3. ፤ ንጉሡም። የእግዚአብሔርን ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳኦል ቤት አንድ ሰው አልቀረምን? አለ። ሲባም ንጉሡን። እግሩ ሽባ የሆነ አንድ የዮናታን ልጅ አለ አለው።

4. ፤ ንጉሡም። ወዴት ነው? አለው፤ ሲባም ንጉሡን። እነሆ፥ እርሱ በሎዶባር በዓሚኤል ልጅ በማኪር ቤት አለ አለው።

5. ፤ ንጉሡም ዳዊት ልኮ ከሎዶባር ከዓሚኤል ልጅ ከማኪር ቤት አስመጣው።

6. ፤ የሳኦልም ልጅ የዮናታን ልጅ ሜምፊቦስቴ ወደ ዳዊት መጣ፥ በግምባሩም ወድቆ እጅ ነሣ፤ ዳዊትም። ሜምፊቦስቴ ሆይ፥ አለ፤ እርሱም። እነሆኝ ባሪያህ አለ።

7. ፤ ዳዊትም። ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ቸርነት ፈጽሜ አደርግልሃለሁና አትፍራ፤ የአባትህንም የሳኦልን ምድር ሁሉ እመልስልሃለሁ፥ አንተም ሁልጊዜ ከገበታዬ እንጀራ ትበላለህ አለው።

8. ፤ እርሱም። የሞተ ውሻ ወደምመስል ወደ እኔ የተመለከትህ እኔ ባሪያህ ምንድር ነኝ? ብሎ እጅ ነሣ።

9. ፤ ንጉሡም የሳኦልን ባሪያ ሲባን ጠርቶ። ለሳኦልና ለቤቱ ሁሉ የነበረውን ሁሉ ለጌታህ ልጅ ሰጥቻለሁ።

10. ፤ አንተና ልጆችህ ሎሌዎችህም ምድሩን እረሱለት፤ ለጌታህም ልጅ እንጀራ ይሆነው ዘንድ ፍሬውን አግባ፤ የጌታህ ልጅ ሜምፊቦስቴ ግን ሁልጊዜ ከገበታዬ ይበላል አለው። ለሲባም አሥራ አምስት ልጆችና ሀያ ባሪያዎች ነበሩት።

11. ፤ ሲባም ንጉሡን። ጌታዬ ንጉሡ ባሪያውን እንዳዘዘ እንዲሁ ባሪያህ ያደርጋል አለው። ሜምፊቦስቴም ከንጉሡ ልጆች እንደ አንዱ ከዳዊት ገበታ ይበላ ነበር።

12. ፤ ለሜምፊቦስቴም ሚካ የተባለ ታናሽ ልጅ ነበረው። በሲባም ቤት ያሉ ሁሉ ለሜምፊቦስቴ ያገለግሉ ነበር።

13. ፤ ሜምፊቦስቴም ከንጉሥ ገበታ ሁልጊዜ እየበላ በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ነበር፤ ሁለት እግሩም ሽባ ነበረ።

About 2 ሳሙኤል Chapter 9

Read 2 ሳሙኤል Chapter 9 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ሳሙኤል in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 2 ሳሙኤል
Chapter: 9
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 2 ሳሙኤል. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 2 ሳሙኤል Chapter 9 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 2 ሳሙኤል Chapter 9?

2 ሳሙኤል Chapter 9 is part of the Book of 2 ሳሙኤል in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 2 ሳሙኤል Chapter 9 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 2-ሳሙኤል

  1. 2 ሳሙኤል Chapter 1
  2. 2 ሳሙኤል Chapter 13
  3. 2 ሳሙኤል Chapter 2
  4. 2 ሳሙኤል Chapter 21
  5. 2 ሳሙኤል Chapter 16
  6. 2 ሳሙኤል Chapter 3
  7. 2 ሳሙኤል Chapter 12

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ኢዮብ Chapter 24
  2. ዘካርያስ Chapter 5
  3. ናሆም Chapter 2
  4. ነህምያ Chapter 6
  5. ዘጸአት Chapter 4
  6. ዘሌዋውያን Chapter 13
  7. ምሳሌ Chapter 14

Related Chapters & Readings

  1. 2 ነገሥት Chapter 24
  2. መክብብ Chapter 5
  3. ማቴዎስ Chapter 17
  4. ዘፍጥረት Chapter 38
  5. 1 ነገሥት Chapter 11
  6. ዳንኤል Chapter 8
  7. ማቴዎስ Chapter 12
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *