1 ነገሥት Chapter 5

For English

Read 1 ነገሥት Chapter 5 Online

Read 1 ነገሥት Chapter 5 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ነገሥት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 1 ነገሥት and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

1 ነገሥት 5

ምዕራፍ 5

1. የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዳዊት በዘመኑ ሁሉ ወዳጅ ስለ ነበረ፥ ሰሎሞን በአባቱ ፋንታ ንጉሥ ለመሆን እንደ ተቀባ ሰምቶ ባሪያዎቹን ወደ ሰሎሞን ሰደደ።

2. ፤ ሰሎሞንም ወደ ኪራም እንዲህ ብሎ ላከ።

3. ፤ እግዚአብሔር ከእግሩ በታች እስኪጥልለት ድረስ በዙሪያው ስለ ነበረ ሰልፍ አባቴ ዳዊት የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት እንዳልቻለ አንተ ታውቃለህ።

4. ፤ አሁንም አምላኬ እግዚአብሔር በዙሪያዬ ካሉት ዕረፍት ሰጥቶኛል፤ ጠላትም ክፉም ነገር የለብኝም።

5. ፤ እነሆም፥ እግዚአብሔር ለአባቴ ለዳዊት። በአንተ ፋንታ በዙፋንህ ላይ የማስቀምጠው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል ብሎ እንደ ነገረው፥ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤት እሠራ ዘንድ አስባለሁ።

6. ፤ አሁንም ከወገኔ እንደ ሲዶናውያን እንጨት መቈረጥ የሚያውቅ እንደሌለ ታውቃለህና የዝግባ ዛፍ ከሊባኖስ ይቈርጡልኝ ዘንድ ባሪያዎችህን እዘዝ፤ ባሪያዎቼም ከባሪያዎችህ ጋር ይሁኑ፤ የባሪያዎችህንም ዋጋ እንደ ተናገርኸው ሁሉ እሰጥሃለሁ።

7. ፤ ኪራምም የሰሎሞንን ቃል ሰምቶ እጅግ ደስ አለውና። በዚህ በታላቅ ሕዝብ ላይ ጥበበኛ ልጅ ለዳዊት የሰጠ እግዚአብሔር ዛሬ ይመስገን አለ።

8. ፤ ኪራምም። የላክህብኝን ሁሉ ሰማሁ፤ ስለ ዝግባውና ስለ ጥዱ እንጨት ፈቃድህን ሁሉ አደርጋለሁ።

9. ፤ ባሪያዎቼ ከሊባኖስ ወደ ባሕር ይጐትቱታል፤ እኔም በታንኳ አድርጌ በባሕር ላይ እያንሳፈፍሁ አንተ እስከ ወሰንኸው ስፍራ ድረስ አደርስልሃለሁ፥ በዚያም እፈታዋለሁ፥ አንተም ከዚያ ታስወስደዋለህ፤ አንተም ፈቃዴን ታደርጋለህ፤ ለቤቴም ቀለብ የሚሆነውን ትሰጠኛለህ ብሎ ወደ ሰሎሞን ላከ።

10. ፤ እንዲሁም ኪራም የዝግባውንና የጥዱን እንጨት እንደሚሻው ያህል ሁሉ ለሰሎሞን ይሰጠው ነበር።

11. ፤ ሰሎሞንም ለኪራም ስለ ቤቱ ቀለብ ሀያ ሺ የቆሮስ መስፈሪያ ስንዴ ሀያ ኮርም ጥሩ ዘይት ይሰጠው ነበር፤ ሰሎሞንም ለኪራም በየዓመቱ ይህን ይሰጥ ነበር።

12. ፤ እግዚአብሔርም እንደ ነገረው ለሰሎሞን ጥበብን ሰጠው፤ በኪራምና በሰሎሞንም መካከል ሰላም ነበረ፤ ሁለቱም ቃል ኪዳን ተጋቡ።

13. ፤ ሰሎሞንም ከእስራኤል ሁሉ ገባሮቹን መርጦ አወጣ፤ የገባሮቹም ቍጥር ሠላሳ ሺህ ሰዎች ነበረ።

14. ፤ በየወሩም እያከታተለ ወደ ሊባኖስ አሥር አሥር ሺህ ይሰድድ ነበር፤ አንድ ወርም በሊባኖስ ሁለት ወርም በቤታቸው ይቀመጡ ነበር። አዶኒራምም አስገባሪ ነበረ።

15. ፤ ሰሎሞንም ሰባ ሺህ ተሸካሚዎች፥ ሰማንያ ሺህም በተራራው ላይ የሚጠርቡ ጠራቢዎች ነበሩት።

16. ፤ ይኸውም በሠራተኛው ሕዝብ ላይ ከተሾሙት ከሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎች ሌላ ነው።

17. ፤ ንጉሡም ታላላቅ ምርጥ ምርጥ ድንጋዮችን ይቈፍሩና ይጠርቡ ዘንድ ለቤቱም መሠረት ይረበርቡት ዘንድ አዘዘ።

18. ፤ የሰሎሞንና የኪራምም አናጢዎች ጌባላውያንም ወቀሩአቸው፥ ቤቱንም ለመሥራት እንጨቱንና ድንጋዮቹን አዘጋጁ።

About 1 ነገሥት Chapter 5

Read 1 ነገሥት Chapter 5 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ነገሥት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 1 ነገሥት
Chapter: 5
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 1 ነገሥት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 1 ነገሥት Chapter 5 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 1 ነገሥት Chapter 5?

1 ነገሥት Chapter 5 is part of the Book of 1 ነገሥት in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 1 ነገሥት Chapter 5 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 1-ነገሥት

  1. 1 ነገሥት Chapter 3
  2. 1 ነገሥት Chapter 6
  3. 1 ነገሥት Chapter 4
  4. 1 ነገሥት Chapter 19
  5. 1 ነገሥት Chapter 18
  6. 1 ነገሥት Chapter 16
  7. 1 ነገሥት Chapter 14

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ዘጸአት Chapter 20
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 145
  3. ኢሳይያስ Chapter 36
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 69
  5. መክብብ Chapter 4
  6. 2 ዜና መዋዕል Chapter 5
  7. ዘጸአት Chapter 18

Related Chapters & Readings

  1. መሳፍንት Chapter 13
  2. 1 ዜና መዋዕል Chapter 1
  3. ኤርምያስ Chapter 41
  4. 2 ዜና መዋዕል Chapter 7
  5. 2 ዜና መዋዕል Chapter 3
  6. ሕዝቅኤል Chapter 17
  7. ሉቃስ Chapter 17
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *