1 ሳሙኤል Chapter 26

For English

Read 1 ሳሙኤል Chapter 26 Online

Read 1 ሳሙኤል Chapter 26 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ሳሙኤል in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 1 ሳሙኤል and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

1 ሳሙኤል 26

ምዕራፍ 26

1. የዚፍ ሰዎችም ወደ ጊብዓ ወደ ሳኦል መጥተው። እነሆ፥ ዳዊት በየሴሞን ፊት ለፊት ባለው በኤኬላ ኮረብታ ላይ ተሸሽጎአል አሉት።

2. ፤ ሳኦልም ተነሥቶ ዳዊትን በዚፍ ምድረ በዳ ይሻ ዘንድ ከእስራኤል የተመረጡ ሦስት ሺህ ሰዎች ይዞ ወደ ዚፍ ምድረ በዳ ወረደ።

3. ፤ ሳኦልም በየሴሞን ፊት ለፊት ባለው በኤኬላ ኮረብታ ላይ በመንገዱ አጠገብ ሰፈረ። ዳዊትም በምድረ በዳ ውስጥ ተቀምጦ ነበር፥ ሳኦልም በስተ ኋላው ወደ ምድረ በዳ እንደ መጣ አየ።

4. ፤ ዳዊትም ሰላዮች ሰደደ፥ ሳኦልም ወደዚህ እንደ መጣ በእርግጥ አወቀ።

5. ፤ ዳዊትም ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ቦታ መጣ፤ ሳኦልና የሠራዊቱ አለቃ የኔር ልጅ አበኔርም የተኙበትን ስፍራ አየ፤ ሳኦልም በሰፈሩ ውስጥ ተኝቶ ነበር፤ ሕዝቡም በዙሪያው ሰፍሮ ነበር።

6. ፤ ዳዊትም ኬጢያዊውን አቢሜሌክንና የጽሩያን ልጅ የኢዮአብን ወንድም አቢሳን። ወደ ሳኦል ወደ ሰፈሩ ከእኔ ጋር የሚወርድ ማን ነው? ብሎ ጠየቃቸው፤ አቢሳም። እኔ ከአንተ ጋር እወርዳለሁ አለ።

7. ፤ ዳዊትና አቢሳም ወደ ሕዝቡ በሌሊት መጡ፤ እነሆም፥ ሳኦል ጦሩ በራሱ አጠገብ በምድር ተተክሎ በሰፈሩ ውስጥ ተኝቶ ነበር፤ አበኔርና ሕዝቡም በዙርያው ተኝተው ነበር።

8. ፤ አቢሳም ዳዊትን። ዛሬ እግዚአብሔር ጠላትህን በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶታል፤ አሁንም እኔ በጦር አንድ ጊዜ ከምድር ጋር ላጣብቀው፥ ሁለተኛም አያዳግምም አለው።

9. ፤ ዳዊትም አቢሳን። እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጁን የሚዘረጋ ንጹሕ አይሆንምና አትግደለው አለው።

10. ፤ ደግሞም ዳዊት። ሕያው እግዚአብሔርን! እግዚአብሔር ይመታዋል፥ ወይም ቀኑ ደርሶ ይሞታል፥ ወይም ወደ ሰልፍ ወርዶ ይገደላል፤

11. ፤ እኔ ግን እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን እዘረጋ ዘንድ እግዚአብሔር ከእኔ ያርቀው፤ አሁንም በራሱ አጠገብ ያለውን ጦርና የውኃውን መንቀል ይዘህ እንሂድ አለ።

12. ፤ ዳዊትም በሳኦል ራስ አጠገብ የነበረውን ጦርና የውኃውን መንቀል ወሰደ፤ ማንም ሳያይ ሳያውቅም ሄዱ፤ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ከባድ እንቅልፍ ወድቆባቸው ነበርና ሁሉ ተኝተው ነበር እንጂ የነቃ አልነበረም።

13. ፤ ዳዊትም ወደዚያ ተሻገረ፤ በተራራውም ራስ ላይ ርቆ ቆመ፤ በመካከላቸውም ሰፊ ስፍራ ነበረ።

14. ፤ ዳዊትም ለሕዝቡና ለኔር ልጅ ለአበኔር። አበኔር ሆይ፥ አትመልስምን? ብሎ ጮኸ። አበኔርም መልሶ። ለንጉሡ የምትጮኸው አንተ ማን ነህ? አለ።

15. ፤ ዳዊትም አበኔርን። አንተ ጕልማሳ አይደለህምን? በእስራኤል ዘንድ አንተን የሚመስል ማን ነው? ጌታህን ንጉሡን ለመግደል አንድ ሰው ገብቶ ነበርና ጌታህን ንጉሡን የማትጠብቅ ስለ ምን ነው?

16. ፤ ይህ ያደረግኸው ነገር መልካም አይደለም፤ ሕያው እግዚአብሔርን! እናንተ እግዚአብሔር የቀባውን ጌታችሁን አልጠበቃችሁምና ሞት ይገባችኋል፤ አሁንም የንጉሡ ጦርና በራሱ አጠገብ የነበረው የውኃው መንቀል የት እንደ ሆነ ተመልከት አለው።

17. ፤ ሳኦልም የዳዊት ድምፅ እንደ ሆነ አውቆ። ልጄ ዳዊት ሆይ፥ ይህ ድምፅህ ነውን? አለው። ዳዊትም። ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ድምፄ ነው አለው።

18. ፤ ደግሞ አለ። ጌታዬ ባሪያውን ስለ ምን ያሳድዳል? ምን አደረግሁ? ምንስ ክፋት በእጄ ላይ ተገኘብኝ?

19. ፤ አሁንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የእኔን የባሪያህን ቃል ትሰማ ዘንድ እለምንሃለሁ፤ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አስነሥቶህ እንደ ሆነ፥ ቁርባንን ይቀበል፤ የሰው ልጆች ግን ቢሆኑ። ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ ብለው በእግዚአብሔር ርስት ላይ እንዳልቀመጥ ዛሬ ጥለውኛልና በእግዚአብሔር ፊት ርጉማን ይሁኑ።

20. ፤ አሁንም በተራራው ላይ ሰው ቆቅን እንደሚሻ የእስራኤል ንጉሥ ነፍሴን ለመሻት ወጥቶአልና ደሜ ከእግዚአብሔር ፊት ርቆ በምድር ላይ አይፍሰስ።

21. ፤ ሳኦልም። በድያለሁ፤ ልጄ ሆይ ዳዊት፥ ተመለስ፤ ዛሬ ነፍሴ በዓይንህ ፊት ከብራለችና ከዚህ በኋላ ክፉ አላደርግብህም እነሆ፥ ስንፍና አድርጌአለሁ፥ እጅግ ብዙም ስቻለሁ አለ።

22. ፤ ዳዊትም መልሶ አለ። የንጉሥ ጦር እነሆ፥ ከብላቴኖችም አንድ ይምጣና ይውሰዳት።

23. ፤ ዛሬም እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ሰጥቶህ ሳለ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን እዘረጋ ዘንድ አልወደድሁምና ለሁሉ እያንዳንዱ እግዚአብሔር እንደ ጽድቁና እንደ እምነቱ ፍዳውን ይክፈለው።

24. ፤ ነፍስህም ዛሬ በዓይኔ ፊት እንደ ከበረች እንዲሁ ነፍሴ በእግዚአብሔር ዓይን ፊት ትክበር፥ ከመከራም ሁሉ ያድነኝ።

25. ፤ ሳኦል ዳዊትን። ልጄ ዳዊት ሆይ፥ ቡሩክ ሁን፤ ማድረግን ታደርጋለህ፥ መቻልንም ትችላለህ አለው። ዳዊትም መንገዱን ሄደ፥ ሳኦልም ወደ ስፍራው ተመለሰ።

About 1 ሳሙኤል Chapter 26

Read 1 ሳሙኤል Chapter 26 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ሳሙኤል in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 1 ሳሙኤል
Chapter: 26
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 1 ሳሙኤል. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 1 ሳሙኤል Chapter 26 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 1 ሳሙኤል Chapter 26?

1 ሳሙኤል Chapter 26 is part of the Book of 1 ሳሙኤል in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 1 ሳሙኤል Chapter 26 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 1 ሳሙኤል

  1. 1 ሳሙኤል Chapter 9
  2. 1 ሳሙኤል Chapter 30
  3. 1 ሳሙኤል Chapter 22
  4. 1 ሳሙኤል Chapter 20
  5. 1 ሳሙኤል Chapter 13
  6. 1 ሳሙኤል Chapter 29
  7. 1 ሳሙኤል Chapter 16

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ኢሳይያስ Chapter 5
  2. 2 ሳሙኤል Chapter 12
  3. ዘኍልቍ Chapter 31
  4. ሶፎንያስ Chapter 3
  5. ኢሳይያስ Chapter 50
  6. ዘጸአት Chapter 32
  7. 2 ዜና መዋዕል Chapter 22

Related Chapters & Readings

  1. ምሳሌ Chapter 10
  2. ኤርምያስ Chapter 46
  3. ምሳሌ Chapter 31
  4. ዮሐንስ Chapter 18
  5. ቲቶ Chapter 2
  6. ሕዝቅኤል Chapter 10
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 13
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *