2 ነገሥት Chapter 19

For English

Read 2 ነገሥት Chapter 19 Online

Read 2 ነገሥት Chapter 19 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ነገሥት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 2 ነገሥት and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

2 ነገሥት 19

ምዕራፍ 19

1. ንጉሡም ሕዝቅያስ ይህን በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀደደ፥ ማቅም ለበሰ፥ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ገባ።

2. ፤ የቤቱንም አዛዥ ኤልያቄምን ጸሐፊውንም ሳምናስን የካህናቱንም ሽማግሌዎች ማቅ ለብሰው ወደ ነቢዩ ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ኢሳይያስ ይሄዱ ዘንድ ላካቸው።

3. ፤ እነርሱም። ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል። ይህ ቀን የመከራና የተግሣጽ የዘለፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል፥ ለመውለድም ኃይል የለም።

4. ፤ ምናልባት በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ ጌታው የአሦር ንጉሥ የላከውን የራፋስቂስን ቃል ሁሉ አምላካህ እግዚአብሔር ይሰማ እንደ ሆነ፥ አምላክህ እግዚአብሔርም ስለ ሰማው ቃል ይገሥጸው እንደ ሆነ፥ ስለዚህ ለቀረው ቅሬታ ጸልይ አሉት።

5. ፤ እንዲሁ የንጉሡ የሕዝቅያስ ባሪያዎች ወደ ኢሳይያስ መጡ።

6. ፤ ኢሳይያስም። ለጌታችሁ። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። የአሦር ንጉሥ ባሪያዎች ስለ ሰደቡኝ፥ ስለ ሰማኸው ቃል አትፍራ።

7. ፤ እነሆ፥ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፥ ወሬንም ይሰማል፥ ወደ ምድሩም ይመለሳል፤ በምድሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርገዋለሁ በሉት አላቸው።

8. ፤ የአሦርም ንጉሥ ከለኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ነበርና ራፋስቂስ ተመልሶ በልብና ሲዋጋ አገኘው።

9. ፤ እርሱም። የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊወጋህ መጥቶአል የሚል ወሬ በሰማ ጊዜ ደግሞ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ፥ እንዲህ ሲል።

10. ፤ ለይሁዳ ንጉሥ ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት። ኢየሩሳሌም በአሦር ንጉሥ እጅ አትሰጥም ብሎ የምትታመንበት አምላክህ አያታልልህ።

11. ፤ እነሆ፥ የአሦር ነገሥታት በምድር ሁሉ ላይ ያደረጉትን፥ እንዴትስ እንዳጠፋአቸው ሰምተሃል፤ አንተስ ትድናለህን?

12. ፤ አባቶቼ ያጠፉአቸውን፥ ጎዛንን፥ ካራንን፥ ራፊስን፥ በተላሳር የነበሩትንም የዔድንን ልጆች፥ የአሕዛብ አማልክት አዳኑአቸውን?

13. ፤ የሐማት ንጉሥ፥ የአርፋድ ንጉሥ፥ የሴፈርዋይም ከተማ ንጉሥ፥ የሄናና የዒዋ ንጉሥ ወዴት አሉ?

14. ፤ ሕዝቅያስም ደብዳቤውን ከመልእክተኞች እጅ ተቀብሎ አነበበው፤ ሕዝቅያስም ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጥቶ በእግዚአብሔር ፊት ዘረጋው።

15. ፤ ሕዝቅያስም ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ጸለየ። በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ የእስራኤል አምላክ አቤቱ፥ አንተ ብቻህን የምድር ነገሥታት ሁሉ አምላክ ነህ፤ ሰማይንና ምድርን ፈጥረሃል።

16. ፤ አቤቱ፥ ጆሮህን አዘንብልና ስማ፤ አቤቱ፥ ዓይንህን ክፈትና እይ፤ በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ የላከውን የሰናክሬምን ቃል ስማ።

17. ፤ አቤቱ፥ በእውነት የአሦር ነገሥታት አሕዛብንና ምድራቸውን አፍርሰዋል፥

18. ፤ አማልክቶቻቸውንም በእሳት ላይ ጥለዋል፤ የእንጨትና የድንጋይ የሰው እጅ ሥራ ነበሩ እንጂ አማልክት አልነበሩምና፤ ስለዚህ አጥፍተዋቸዋል።

19. ፤ እንግዲህም አምላካችን አቤቱ፥ የምድር መንግሥታት ሁሉ አንተ ብቻ እግዚአብሔር አምላክ እንደ ሆንህ ያውቁ ዘንድ ከእጁ እንድታድነን እለምንሃለሁ።

20. ፤ የአሞጽም ልጅ ኢሳይያስ እንዲህ ብሎ ወደ ሕዝቅያስ ላካ። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰናክሬም ወደ እኔ የለመንኽውን ሰምቻለሁ።

21. ፤ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የተናገረው ቃል ይህ ነው። ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ቀላል አድርጋሃለች፥ በንቀትም ስቃብሃለች፤ የኢየሩሳሌም ልጅ በላይህ ራስዋን ነቅንቃብሃለች።

22. ፤ የተገዳደርኸው፥ የሰደብኸውስ ማን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደረግኸው ዓይንህንም ወደ ላይ ያነሣኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ ነው።

23. ፤ አንተስ። በሰረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባኖስ ጥግ ላይ ወጥቻለሁ፤ ረጃጅሞቹንም ዝግባዎች የተመረጡትንም ጥዶች እቈርጣለሁ፥ ወደ አገሩም ዳርቻና ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ።

24. ፤ ቈፈርሁም፥ እንግዳውንም ውኃ ጠጣሁ፤ የተገደበውንም ውኃ ሁሉ በእግሬ ጫማ አደርቃለሁ ብለህ በመልእክተኞችህ እጅ በእግዚአብሔር ላይ ተገዳደርህ።

25. ፤ እኔ ጥንቱን እንደ ሠራሁት፥ ቀድሞውንም እንዳደረግሁት አልሰማህምን? አሁንም የተመሸጉትን ከተሞች የፍርስራሽ ክምር እስኪሆኑ ድረስ እንድታፈርስ አደረግሁህ።

26. ፤ ስለዚህም የሚኖሩባቸው ሰዎች እጃቸው ዝሎአል፥ ደንግጠውም ታውከዋል፤ እንደ ምድረ በዳ ሣር፥ እንደ ለምለምም ቡቃያ፥ በሰገነትም ላይ እንዳለ ሣር፥ ሳይሸት ዋግ እንደ መታውም እህል ሆነዋል።

27. ፤ እኔ ግን መቀመጫህንና መውጫህንም መግቢያህንም፥ በእኔም ላይ የተቈጠኸውን ቍጣ አውቄአለሁ።

28. ፤ ቍጣህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአልና ስለዚህ ስናጋዬን በአፍንጫህ፥ ልጓሜንም በከንፈርህ አደርጋለሁ፥ በመጣህበትም መንገድ እመልስሃለሁ።

29. ፤ ይህም ምልክት ይሆንሃል፤ በዚህ ዓመት የገቦውን፥ በሁለተኛውም ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላላችሁ፤ በሦስተኛውም ዓመት ትዘራላችሁ፥ ታጭዱማላችሁ፥ ወይንንም ትተክላላችሁ፥ ፍሬውንም ትበላላችሁ።

30. ፤ ያመለጠው የይሁዳ ቤት ቅሬታ ሥሩን ወደ ታች ይሰድዳል፥ ወደ ላይም ያፈራል።

31. ፤ ከኢየሩሳሌም ቅሬታ ከጽዮንም ተራራ ያመለጡት ይወጣሉና፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።

32. ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል። ወደዚች ከተማ አይመጣም፥ ፍላጻንም አይወረውርባትም፥ በጋሻም አይመጣባትም፥ የአፈርንም ድልድል አይደለድልባትም።

33. ፤ በመጣበት መንገድ በዚያው ይመለሳል፥ ወደዚህችም ከተማ አይመጣም፥ ይላል እግዚአብሔር።

34. ፤ ስለ እኔም፥ ስለ ባሪያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ።

35. ፤ በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ፥ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ።

36. ፤ የአሦርም ንጉሥ ሰናክሬም ተነሥቶ ሄደ፥ ተመልሶም በነነዌ ተቀመጠ።

37. ፤ በአምላኩም በናሳራክ ቤት ሲሰግድ ልጆቹ አደራሜሌክና ሳራሳር በሰይፍ ገደሉት፤ ወደ አራራትም አገር ኰበለሉ። ልጁም አስራዶን በእርሱ ፋንታ ነገሠ።

About 2 ነገሥት Chapter 19

Read 2 ነገሥት Chapter 19 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ነገሥት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 2 ነገሥት
Chapter: 19
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 2 ነገሥት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 2 ነገሥት Chapter 19 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 2 ነገሥት Chapter 19?

2 ነገሥት Chapter 19 is part of the Book of 2 ነገሥት in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 2 ነገሥት Chapter 19 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 2-ነገሥት

  1. 2 ነገሥት Chapter 12
  2. 2 ነገሥት Chapter 2
  3. 2 ነገሥት Chapter 13
  4. 2 ነገሥት Chapter 1
  5. 2 ነገሥት Chapter 20
  6. 2 ነገሥት Chapter 15
  7. 2 ነገሥት Chapter 3

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. አሞጽ Chapter 5
  2. ኢሳይያስ Chapter 17
  3. መክብብ Chapter 9
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 22
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 119
  6. ሕዝቅኤል Chapter 27
  7. አሞጽ Chapter 8

Related Chapters & Readings

  1. ኢያሱ Chapter 21
  2. 1 ዜና መዋዕል Chapter 16
  3. 3 ዮሐንስ Chapter 1
  4. 1 ዜና መዋዕል Chapter 25
  5. ያዕቆብ Chapter 2
  6. መክብብ Chapter 12
  7. ሉቃስ Chapter 6
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *