1 ሳሙኤል Chapter 10

For English

Read 1 ሳሙኤል Chapter 10 Online

Read 1 ሳሙኤል Chapter 10 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ሳሙኤል in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 1 ሳሙኤል and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

1 ሳሙኤል 10

ምዕራፍ 10

1. ሳሙኤልም የዘይቱን ብርሌ ወስዶ በራሱ ላይ አፈሰሰው፥ ሳመውም፥ እንዲህም አለው። በርስቱ ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶሃል፤ የእግዚአብሔርንም ሕዝብ ትገዛለህ፥ በዙሪያውም ካሉ ጠላቶቻቸው እጅ ታድናቸዋለህ።

2. ፤ ዛሬ ከእኔ በተለየህ ጊዜ በብንያም ዳርቻ በጼልጻህ አገር ባለው በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ፤ እነርሱም። ልትሻቸው ሄደህ የነበርህላቸ አህዮች ተገኝተዋል፤ እነሆም፥ አባትህ ስለ አህዮች ማሰብ ትቶ። የልጄን ነገር እንዴት አደርጋለሁ? እያለ ስለ እናንተ ይጨነቃል ይሉሃል።

3. ፤ ከዚያም ደግሞ ወደ ፊት ትሄዳለህ፤ ወደ ታቦር ወደ ትልቁ ዛፍ ትደርሳለህ፤ በዚያም ሦስት ሰዎች፥ አንዱ ሦስት ሰዎች፥ አንዱ ሦስት የፍየል ጠቦቶች፥ ሁለተኛው ሦስት ዳቦ፥ ሦስተኛውም የወይን ጠጅ አቁማዳ ይዘው ወደ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ያገኙሃል፤

4. ፤ ሰላምታም ይሰጡሃል፥ ሁለትም ዳቦ ይሰጡሃል፥ ከእጃቸውም ትቀበላለህ።

5. ፤ ከዚያም በኋላ የፍልስጥኤማውያን ጭፍራ ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ኮረብታ ትመጣለህ፤ ወደዚያም ወደ ከተማይቱ በደረስህ ጊዜ፥ በገናና ከበሮ እምቢልታና መሰንቆ ይዘው ትንቢት እየተናገሩ ከኮረብታው መስገጃ የሚወርዱ የነቢያት ጉባኤ ያገኙሃል።

6. ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ይወርድብሃል፥ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ትናገራለህ፥ እንደ ሌላ ሰውም ሆነህ ትለወጣለህ።

7. ፤ እነዚህም ምልክቶች በደረሱህ ጊዜ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና እጅህ የምታገኘውን ሁሉ አድርግ።

8. ፤ በፊቴም ወደ ጌልገላ ትወርዳለህ፤ እኔም፥ እነሆ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀርብ ዘንድ፥ የደኅንነትም መሥዋዕት እሠዋ ዘንድ ወደ አንተ እወርዳለሁ፤ እኔ ወደ አንተ እስክመጣና የምታደርገውን እስክነግርህ ድረስ ሰባት ቀን ትቆያለህ።

9. ፤ ከሳሙኤልም ዘንድ ለመሄድ ፊቱን በመለሰ ጊዜ እግዚአብሔር ሌላ ልብ ለወጠለት፤ በዚያም ቀን እነዚህ ምልክቶች ሁሉ ደረሱለት።

10. ፤ ወደዚያም ኮረብታ በደረሰ ጊዜ፥ እነሆ፥ የነቢያት ጉባኤ አገኙት፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ወረደበት፥ በመካከላቸውም ትንቢት ተናገረ።

11. ፤ ቀድሞም የሚያውቁት ሁሉ ከነቢያት ጋር ትንቢት ሲናገር ባዩት ጊዜ ሕዝቡ እርስ በርሳቸው። የቂስን ልጅ ያገኘው ምንድር ነው? በውኑ ሳኦል ከነቢያት ወገን ነውን? ተባባሉ።

12. ፤ ከዚያም ስፍራ ያለ አንድ ሰው። አባታቸውስ ማን ነው? ብሎ መለሰ። ስለዚህም። ሳኦል ደግሞ ከነቢያት ወገን ነውን? የሚል ምሳሌ ሆነ።

13. ፤ ትንቢት መናገሩንም በፈጸመ ጊዜ ወደ ኮረብታው መስገጃ መጣ።

14. ፤ አጎቱም ሳኦልንና ብላቴናውን፥ ወዴት ሄዳችሁ ኖሮአል? አላቸው። እርሱም። አህዮችን ልንሻ ሄደን ነበር፤ ባጣናቸውም ጊዜ ወደ ሳሙኤል መጣን አለ።

15. ፤ የሳኦልም አጎት። ሳሙኤል የነገረህን፥ እባክህ፥ ንገረኝ አለው።

16. ፤ ሳኦልም አጎቱን። አህዮች እንደ ተገኙ ገለጠልን አለው፤ ነገር ግን ሳሙኤል የነገረውን የመንግሥትን ነገር አላወራለትም።

17. ፤ ሳሙኤልም ሕዝቡን ወደ እግዚአብሔር ወደ ምጽጳ ጠራ።

18. ፤ የእስራኤልንም ልጆች። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እስራኤልን ከግብጽ አወጣሁ፥ ከግብጻውያንም እጅ ከሚያስጨንቁአችሁም ነገሥታት ሁሉ እጅ አዳንኋችሁ።

19. ፤ ዛሬ ግን ከመከራችሁና ከጭንቃችሁ ሁሉ ያዳናችሁን አምላካችሁን ንቃችሁ። እንዲህ አይሁን፥ ነገር ግን ንጉሥ አታንግሥልን አላችሁት። አሁንም በየነገዳችሁና በየወገናችሁ ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ አላቸው።

20. ፤ ሳሙኤልም የእስራኤልን ነገዶች ሁሉ አቀረበ፥ ዕጣውም በብንያም ነገድ ላይ ወደቀ።

21. ፤ የብንያምንም ነገድ በየወገናቸው አቀረበ፥ ዕጣውም በማጥሪ ወገን ላይ ወደቀ። የማጥሪንም ወገን በየሰዉ አቀረበ፥ ዕጣውም በቂስ ልጅ በሳኦል ላይ ወደቀ፤ ፈለጉትም፥ አላገኙትምም።

22. ፤ ከእግዚአብሔርም። ገና ወደዚህ የሚመጣ ሰው አለን? ብለው ደግሞ ጠየቁት፤ እግዚአብሔርም። እነሆ፥ በዕቃ መካከል ተሸሽጎአል ብሎ መለሰ።

23. ፤ እነርሱም ሮጠው ከዚያ አመጡት፤ እርሱም በሕዝቡ መካከል ቆመ፥ ከሕዝቡም ሁሉ ይልቅ ከትከሻው ወደ ላይ ከፍ ያለ ቁመተ ረጅም ነበረ።

24. ፤ ሳሙኤልም ለሕዝቡ ሁሉ። ከሕዝቡ ሁሉ እርሱን የሚመስል እንደሌለ እግዚአብሔር የመረጠውን ታያላችሁን? አላቸው፤ ሕዝቡም ሁሉ። ንጉሥ ሕያው ይሁን እያሉ እልልታ አደረጉ።

25. ፤ ሳሙኤልም የመንግሥቱን ወግ ነገረ፥ በመጽሐፍም ጻፈው በእግዚአብሔርም ፊት አኖረው። ሳሙኤልም ሕዝቡን ሁሉ ወደ እየቤታቸው አሰናበታቸው።

26. ፤ ሳኦልም ወደ ቤቱ ወደ ጊብዓ ሄደ፤ እግዚአብሔር ልባቸውን የነካ ኃያላንም ከእርሱ ጋር ሄዱ።

27. ፤ ምናምንቴዎች ሰዎች ግን። ይህ ሰው እንዴት ያድነናል? ብለው ናቁት፥ እጅ መንሻም አላመጡለትም።

About 1 ሳሙኤል Chapter 10

Read 1 ሳሙኤል Chapter 10 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ሳሙኤል in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 1 ሳሙኤል
Chapter: 10
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 1 ሳሙኤል. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 1 ሳሙኤል Chapter 10 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 1 ሳሙኤል Chapter 10?

1 ሳሙኤል Chapter 10 is part of the Book of 1 ሳሙኤል in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 1 ሳሙኤል Chapter 10 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 1 ሳሙኤል

  1. 1 ሳሙኤል Chapter 9
  2. 1 ሳሙኤል Chapter 22
  3. 1 ሳሙኤል Chapter 20
  4. 1 ሳሙኤል Chapter 3
  5. 1 ሳሙኤል Chapter 30
  6. 1 ሳሙኤል Chapter 13
  7. 1 ሳሙኤል Chapter 29

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ኢሳይያስ Chapter 14
  2. ኤርምያስ Chapter 17
  3. ሕዝቅኤል Chapter 46
  4. ኢያሱ Chapter 12
  5. አሞጽ Chapter 7
  6. ሆሴዕ Chapter 5
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 71

Related Chapters & Readings

  1. 1 ሳሙኤል Chapter 30
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 105
  3. ዘጸአት Chapter 40
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 149
  5. ዘጸአት Chapter 32
  6. መዝሙረ ዳዊት Chapter 29
  7. ኢዮብ Chapter 23
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *