ነህምያ Chapter 5

For English

Read ነህምያ Chapter 5 Online

Read ነህምያ Chapter 5 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ነህምያ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ነህምያ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ነህምያ 5

ምዕራፍ 5

1. በወንድሞቻቸውም በአይሁድ ላይ ትልቅ የሕዝቡና የሚስቶቻቸው ጩኸት ሆነ።

2. ፤ አያሌዎቹም። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን ብዙዎች ናቸው፤ በልተንም በሕይወት እንድንኖር እህልን እንሸምት ይሉ ነበር።

3. ፤ አያሌዎቹም። ከራብ የተነሣ እህልን እንሸምት ዘንድ እርሻችንና ወይናችንን ቤታችንንም አስይዘናል ይሉ ነበር።

4. ፤ ሌሎቹም። ለንጉሡ ግብር እርሻችንንና ወይናችንን አስይዘን ገንዘብ ተበድረናል፤

5. ፤ አሁንም ሥጋችን እንደ ወንድሞቻችን ሥጋ፥ ልጆቻችንም እንደ ልጆቻቸው ናቸው፤ እነሆም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን ባሪያዎች ይሆኑ ዘንድ ሰጥተናል፥ ከሴቶችም ልጆቻችን ባሪያዎች ሆነው የሚኖሩ አሉ፤ ታላላቆችም እርሻችንና ወይናችንን ይዘዋልና ልናድናቸው አንችልም ይሉ ነበር።

6. ፤ እኔም ጩኸታቸውንና ይህን ቃል በሰማሁ ጊዜ እጅግ ተቈጣሁ።

7. ፤ በልቤም አሰብሁ፥ ታላላቆቹንና ሹማምቱንም። ሁላችሁ እያንዳንዳችሁ ወለድ ትወስዳላችሁ ብዬ ተጣላኋቸው፤ ትልቅም ጉባኤ ሰበሰብሁባቸው።

8. ፤ እኔም። ለአሕዛብ የተሸጡትን ወንድሞቻችንን አይሁድን በፈቃዳችን ተቤዠን፤ እናንተስ ወንድሞቻችሁን ትሸጣላችሁን? እነርሱስ ለእኛ የተሸጡ ይሆናሉን? አልኋቸው። እነርሱም ዝም አሉ፥ መልስም አላገኙም።

9. ፤ ደግሞም አልሁ። የምታደርጉት ነገር መልካም አይደለም፤ ጠላቶቻችን አሕዛብ እንዳይሰድቡን አምላካችንን በመፍራት ትሄዱ ዘንድ አይገባችሁምን?

10. ፤ እኔም ደግሞ ወንድሞቼም ብላቴኖቼም ገንዘብና እህል ለእነርሱ አበድረናል፤ እባካችሁ፥ ይህን ወለድ እንተውላቸው።

11. ፤ እርሻቸውንና ወይናቸውን ወይራቸውንና ቤታቸውንም ከእነርሱም የወሰዳችሁትን ገንዘቡንና እህሉን፥ ወይን ጠጁንና ዘይቱን ከመቶ እጅ አንድ እጅ እባካችሁ ዛሬ መልሱላቸው።

12. ፤ እነርሱም። እንመልስላቸዋለን፥ ከእነርሱም ምንም አንሻም፤ እንደ ተናገርህ እንዲሁ እናደርጋለን አሉ። ካህናቱንም ጠርቼ እንደዚህ ነገር ያደርጉ ዘንድ አማልኋቸው።

13. ፤ ደግሞም ልብሴን አራገፍሁና። ይህን ነገር የማያደርገውን ሰው ከቤቱና ከሥራው እንዲሁ እግዚአብሔር ያራግፈው፤ እንዲሁም የተራገፈና ባዶ ይሁን አልሁ። ጉባኤውም ሁሉ። አሜን አሉ፥ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ፤ ሕዝቡም እንደዚህ ነገር አደረጉ።

14. ፤ ንጉሡም በይሁዳ ምድር ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ካዘዘኝ ጊዜ ጀምሮ ከንጉሡ ከአርጤክስስ ከሀያኛው ዓመት እስከ ሠላሳ ሁለተኛው ዓመት ድረስ አሥራ ሁለት ዓመት ያህል እኔና ወንድሞቼ ለአለቃ የሚገባውን ስንቅ አልበላንም።

15. ፤ ከእኔ አስቀድመው የነበሩት አለቆች ግን በሕዝቡ ላይ አክብደው ነበር፤ ስለ እንጀራውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወስዱ ነበር፤ ሎሌዎቻቸውም ደግሞ በሕዝቡ ላይ ይሠለጥኑ ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈራሁ እንዲህ አላደረግሁም።

16. ፤ ደግሞም አጥብቄ የቅጥሩን ሥራ ሠራሁ፥ እርሻም አልገዛንም፤ ብላቴኖቼም ሁሉ ወደዚያው ወደ ሥራው ተሰበሰቡ።

17. ፤ ደግሞም በዙሪያችን ካሉት አሕዛብ ወደ እኛ ከመጡት ሌላ ከአይሁድና ከሹማምቱ መቶ አምሳ ሰዎች በገበታዬ ነበሩ።

18. ፤ ከወፎችም በቀር ለአንድ ቀን አንድ በሬና ስድስት የሰቡ በጎች፥ በአሥር በአሥር ቀንም ብዙ ልዩ ልዩ ዓይነት ወይን ጠጅ ይዘጋጅልኝ ነበር፤ ነገር ግን አገዛዝ በሕዝቡ ላይ ከብዶ ነበርና ለአለቃ የሚገባውን ስንቅ አልሻም ነበር።

19. ፤ አምላኬ ሆይ፥ ለዚህ ሕዝብ ያደረግሁትን ሁሉ ለበጎነት አስብልኝ።

About ነህምያ Chapter 5

Read ነህምያ Chapter 5 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ነህምያ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ነህምያ
Chapter: 5
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ነህምያ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ነህምያ Chapter 5 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ነህምያ Chapter 5?

ነህምያ Chapter 5 is part of the Book of ነህምያ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ነህምያ Chapter 5 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ብሉይ ኪዳን

  1. አሞጽ Chapter 4
  2. አሞጽ Chapter 2
  3. አሞጽ Chapter 7
  4. አሞጽ Chapter 6
  5. አሞጽ Chapter 3
  6. አሞጽ Chapter 1
  7. አሞጽ Chapter 9

Explore More from ነህምያ

  1. ነህምያ Chapter 13
  2. ነህምያ Chapter 2
  3. ነህምያ Chapter 12
  4. ነህምያ Chapter 11
  5. ነህምያ Chapter 8
  6. ነህምያ Chapter 7
  7. ነህምያ Chapter 4

Related Chapters & Readings

  1. ዳንኤል Chapter 1
  2. ዘፍጥረት Chapter 50
  3. ዘኍልቍ Chapter 17
  4. የሐዋርያት ሥራ Chapter 5
  5. ዘሌዋውያን Chapter 20
  6. ራእይ Chapter 8
  7. ዘዳግም Chapter 25
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *