ነህምያ Chapter 12

For English

Read ነህምያ Chapter 12 Online

Read ነህምያ Chapter 12 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ነህምያ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ነህምያ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ነህምያ 12

ምዕራፍ 12

1. ከሰላትያል ልጅ ከዘሩባቤልና ከኢያሱ ጋር የወጡት ካህናትና ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤

2. ፤ ሠራያ፥ ኤርምያስ፥ ዕዝራ፥ አማርያ፥

3. ፤ መሉክ፥ ሐጡስ፥ ሴኬንያ፥ ሬሁም፥ ሜሪሞት፥

4.

5. ፤ አዶ፥ ጌንቶን፥ አብያ፥ ሚያሚን

6. ፤ መዓድያ፥ ቢልጋ፥ ሸማያ፥ ዮያሪብ፥ ዮዳኤ፥

7. ፤ ሰሉ፥ ዓሞቅ፥ ኬልቅያስ፥ ዮዳኤ፤ እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቻቸው አለቆች ነበሩ።

8. ፤ ሌዋውያኑም፤ ኢያሱ፥ ቢንዊ፥ ቀድምኤል፥ ሰራብያ፥ ይሁዳ፥ ከወንድሞቹም ጋር በመዘምራን ላይ የነበረ መታንያ።

9. ፤ ወንድሞቻቸውም በቅቡቅያና ዑኒ በየሰሞናቸው በአንጻራቸው ነበሩ።

10. ፤ ኢያሱም ዮአቂምን ወለደ፥ ዮአቂምም ኤልያሴብን ወለደ፥ ኤልያሴብም ዮአዳን ወለደ፥

11. ፤ ዮአዳም ዮናታንን ወለደ፥ ዮናታንም ያዱአን ወለደ።

12. ፤ በዮአቂምም ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች እነዚህ ካህናቱ ነበሩ፤ ከሠራያ ምራያ፥

13. ፤ ከኤርምያስ ሐናንያ፥ ከዕዝራ ሜሱላም፥

14. ፤ ከአማርያ ይሆሐናን፥ ከመሉኪ ዮናታን፥

15. ፤ ከሰበንያ ዮሴፍ፥ ከካሪም ዓድና፥ ከመራዮት ሔልቃይ፥

16. ፤ ከአዶ ዘካርያስ፥ ከጌንቶን ሜሱላም፥

17. ፤ ከአብያ ዚክሪ፥ ከሚያሚን ሞዓድያ፥

18. ፤ ፈልጣይ፥ ከቢልጋ ሳሙስ፥ ከሸማያ ዮናታን፥

19. ፤ ከዮያሪብ መትናይ፥ ከዮዳኤ ኦዚ፥

20. ፤ ከሳላይ ቃላይ፥ ከዓሞቅ ዔቤር፥

21. ፤ ከኬልቅያስ ሐሸብያ፥ ከዮዳኤ ናትናኤል።

22. ፤ ከሌዋውያኑም በኤልያሴብና በዮአዳ፥ በዮሐናንና በያዱአ ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች ተጻፉ፤ ካህናቱም በፋርሳዊው በዳርዮስ መንግሥት ዘመን ተጻፉ።

23. ፤ የሌዊ ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች እስከ ኤልያሴብ ልጅ እስከ ዮሐናን ዘመን ድረስ በታሪክ መጽሐፍ ተጻፉ።

24. ፤ የሌዋውያኑም አለቆች፤ ሐሸብያ፥ ሰራብያ፥ የቀድምኤልም ልጅ ኢያሱ እንደ እግዚአብሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእዛዝ በየሰሞናቸው በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ያከብሩና ያመሰግኑ ነበር።

25. ፤ መታንያ፥ በቅቡቅያ፥ አብድዮ፥ ሜሱላም፥ ጤልሞን፥ ዓቁብ በበሮች አጠገብ የሚገኙትን ዕቃ ቤቶች ለመጠበቅ በረኞች ነበሩ።

26. ፤ እነዚህ በኢዮሴዴቅ ልጅ በኢያሱ ልጅ በዮአቂም በአለቃውም በነህምያ በጸሐፊውም በካህኑ በዕዝራ ዘመን ነበሩ።

27. ፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር በቀደሱ ጊዜ ቅዳሴውን በደስታና በምስጋና በመዝሙርም በጸናጽልም በበገናም በመሰንቆም ለማድረግ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸው ዘንድ ሌዋውያኑን በየስፍራቸው ሁሉ ፈለጉ።

28.

29. ፤ መዘምራኑም በኢየሩሳሌም ዙሪያ መንደሮች ሠርተው ነበርና የመዘምራኑ ልጆች ከኢየሩሳሌም ዙሪያና ከነጦፋውያን መንደሮች፥ ከቤትጌልገላም፥ ከጌባና ከዓዝሞት እርሻዎች ተሰበሰቡ።

30. ፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አነጹ፤ ሕዝቡንም በሮቹንም ቅጥሩንም አነጹ።

31. ፤ የይሁዳንም አለቆች ወደ ቅጥሩ ላይ አወጣኋቸው፤ አመስጋኞቹንም በሁለት ታላላቅ ተርታ አቆምኋቸው፤ አንዱም ወደ ቀኝ በቅጥሩ ላይ ወደ ጕድፍ መጣያው በር ሄደ።

32. ፤ ከእነርሱም በኋላ ሆሻያ፥ የይሁዳም አለቆች እኵሌታ፥

33. ፤ ዓዛርያስ፥ ዕዝራ፥

34. ፤ ሜሱላም፥ ይሁዳ፥ ብንያም፥ ሸማያ፥ ኤርምያስ፥

35. ፤ መለከትም ይዘው ከካህናቱ ልጆች አያሌዎች፥ የአሳፍም ልጅ የዘኩር ልጅ የሚካያ ልጅ የመታንያ ልጅ የሸማያ ልጅ የዮናታን ልጅ ዘካርያስ፥

36. ፤ ወንድሞቹም ሸማያ፥ ኤዝርኤል፥ ሚላላይ፥ ጊላላይ፥ መዓይ፥ ናትናኤል፥ ይሁዳ፥ አናኒ የእግዚአብሔርን ሰው የዳዊትን የዜማውን ዕቃ ይዘው ሄዱ፤ ጸሐፊውም ዕዝራ በፊታቸው ነበረ።

37. ፤ በምንጭም በር አቅንተው ሄዱ፤ በዳዊትም ከተማ ደረጃ፥ በቅጥሩም መውጫ፥ ከዳዊትም ቤት በላይ እስከ ውኃው በር ድረስ በምሥራቅ በኩል ሄዱ።

38. ፤ ሁለተኛውም የአመስጋኞቹ ተርታ ወደ ግራ ሄደ፤ እኔና የሕዝቡም እኵሌታ በስተኋላቸው ነበርን፤ በቅጥሩም ላይ፥ በእቶኑ ግንብ በላይ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ፥ ከኤፍሬምም በር በላይ፥

39. ፤ በአሮጌው በርና በዓሣ በር በሐናንኤልም ግንብ፥ በሃሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፤ በዘበኞችም በር አጠገብ ቆሙ።

40. ፤ እንዲሁ ሁለቱ የአመስጋኞች ተርታዎች በእግዚአብሔር ቤት ቆሙ፤ ከእነርሱም ጋር እኔና የአለቆች እኵሌታ፥

41. ፤ ካህናቱም ኤልያቄም፥ መዕሤያ፥ ሚንያሚን፥ ሚካያ፥ ኤልዮዔናይ፥

42. ፤ ዘካርያስ፥ ሐናንያ መለከት ይዘው፥ መዕሤያ፥ ሸማያ፥ አልዓዛር፥ ኦዚ፥ ይሆሐናን፥ መልክያ፥ ኤላም፥ ኤጽር ቆምን። መዘምራኑም በታላቅ ድምፅ ዘመሩ፥ አለቃቸውም ይዝረሕያ ነበረ።

43. ፤ እግዚአብሔርም በታላቅ ደስታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥዋዕት አቀረቡ፥ ደስም አላቸው፤ ሴቶቹና ልጆቹም ደግሞ ደስ አላቸው፤ የኢየሩሳሌምም ደስታ ከሩቅ ተሰማ።

44. ፤ ይሁዳም በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን እድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለእጅ ማንሣት ቍርባንና ለበኵራት ለአሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎች ተሾሙ።

45. ፤ እነርሱም መዘምራኑና በረኞቹም የአምላካቸውን ሥርዓት የመንጻታቸውንም ሥርዓት እንደ ዳዊትና እንደ ልጁ እንደ ሰሎሞን ትእዛዝ ጠበቁ።

46. ፤ አስቀድሞም በዳዊትና በአሳፍ ዘመን እግዚአብሔርን በዜማ ለማመስገንና ለማክበር የመዘምራን አለቆች ነበሩ።

47. ፤ እስራኤልም ሁሉ በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን ለመዘምራኑና ለበረኞቹ እድል ፈንታቸውን በየዕለቱ ይሰጡ ነበር፤ የተቀደሰውንም ነገር ለሌዋውያን ሰጡ፥ ሌዋውያኑም ከተቀደሰው ነገር ለአሮን ልጆች ሰጡ።

About ነህምያ Chapter 12

Read ነህምያ Chapter 12 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ነህምያ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ነህምያ
Chapter: 12
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ነህምያ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ነህምያ Chapter 12 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ነህምያ Chapter 12?

ነህምያ Chapter 12 is part of the Book of ነህምያ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ነህምያ Chapter 12 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ብሉይ ኪዳን

  1. አሞጽ Chapter 4
  2. አሞጽ Chapter 1
  3. አሞጽ Chapter 3
  4. አሞጽ Chapter 6
  5. አሞጽ Chapter 2
  6. አሞጽ Chapter 7
  7. አሞጽ Chapter 5

Explore More from ነህምያ

  1. ነህምያ Chapter 4
  2. ነህምያ Chapter 5
  3. ነህምያ Chapter 3
  4. ነህምያ Chapter 1
  5. ነህምያ Chapter 8
  6. ነህምያ Chapter 6
  7. ነህምያ Chapter 11

Related Chapters & Readings

  1. 1 ነገሥት Chapter 4
  2. ሉቃስ Chapter 6
  3. ኢሳይያስ Chapter 14
  4. ዘኍልቍ Chapter 32
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 48
  6. ሕዝቅኤል Chapter 29
  7. ዮናስ Chapter 1
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *