መሳፍንት Chapter 7

For English

Read መሳፍንት Chapter 7 Online

Read መሳፍንት Chapter 7 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መሳፍንት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መሳፍንት and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

መሳፍንት 7

ምዕራፍ 7

1. ጌዴዎን የተባለውም ይሩበኣል ከእርሱም ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ማልደው ተነሡ፥ በሐሮድ ምንጭ አጠገብም ሰፈሩ፤ የምድያምም ሰፈር ከእነርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበረ።

2. ፤ እግዚአብሔርም ጌዴዎንን። ከአንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝቶአል፤ ስለዚህ እስራኤል። እጄ አዳነኝ ብሎ እንዳይታበይብኝ እኔ ምድያምን በእጃቸው አሳልፌ አልሰጣቸውም።

3. ፤ አሁንም እንግዲህ። የፈራ የደነገጠም ከገለዓድ ተራራ ተነሥቶ ይመለስ ብለህ በሕዝቡ ጆሮ አውጅ አለው። ከሕዝቡም ሀያ ሁለት ሺህ ተመለሱ፥ አሥርም ሺህ ቀሩ።

4. ፤ እግዚአብሔርም ጌዴዎንን። ሕዝቡ ገና ብዙ ነው፤ ወደ ውኃ አውርዳቸው፥ በዚያም እፈትናቸዋለሁ፤ እኔም። ይህ ከአንተ ጋር ይሂድ የምለው እርሱ ከአንተ ጋር ይሄዳል፤ እኔም። ይህ ከአንተ ጋር አይሂድ የምለው እርሱ አይሄድም አለው።

5. ፤ ሕዝቡንም ወደ ውኃ አወረደ። እግዚአብሔርም ጌዴዎንን። ውሻ እንደሚጠጣ ውኃ በምላሱ የሚጠጣውን ሁሉ፥ እርሱን ለብቻው አድርገው፤ እንዲሁም ሊጠጣ በጕልበቱ የሚንበረከከውን ሁሉ ለብቻው አድርገው አለው።

6. ፤ በእጃቸውም ውኃ ወደ አፋቸው አድርገው የጠጡት ቍጥር ሦስት መቶ ነበረ፤ የቀሩት ሕዝብ ግን ውኃ ሊጠጡ በጕልበታቸው ተንበረከኩ።

7. ፤ እግዚአብሔርም ጌዴዎንን። በእጃቸው ውኃ በጠጡት በሦስት መቶ ሰዎች አድናችኋለሁ፥ ምድያማውያንንም በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤ የቀሩት ሕዝብ ሁሉ ግን ወደ ስፍራቸው ይመለሱ አለው።

8. ፤ የሕዝቡንም ስንቅና ቀንደ መለከት በእጃቸው ወሰዱ፤ የቀሩትንም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ድንኳናቸው ሰደዳቸው፥ ሦስቱን መቶ ሰዎች ግን በእርሱ ዘንድ ጠበቃቸው፤ የምድያምም ሰፈር ከእርሱ በታች በሸለቆው ውስጥ ነበረ።

9. ፤ በዚያም ሌሊት እግዚአብሔር። በእጅህ አሳልፌ ሰጥቻቸዋለሁና ተነሥተህ ወደ ሰፈር ውረድ።

10. ፤ አንተም ለመውረድ ብትፈራ አንተ ከሎሌህ ከፉራ ጋር ወደ ሰፈሩ ውረድ፤

11. ፤ የሚናገሩትንም ትሰማለህ፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ትወርድ ዘንድ እጅህ ትበረታለች አለው። እርሱና ሎሌው ፉራ በሰፈሩ ዳርቻ ወደ ነበሩት ሰልፈኞች ወረዱ።

12. ፤ ብዛታቸውም እንደ አንበጣ የሆነ ምድያማውያንና አማሌቃውያን የምሥራቅም ሰዎች ሁሉ በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፤ የግመሎቻቸውም ብዛት ቍጥር እንደ ሌለው በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ነበረ።

13. ፤ ጌዴዎንም በደረሰ ጊዜ አንድ ሰው ሕልምን ለባልንጀራው ሲያጫውት። እነሆ፥ ሕልም አለምሁ፤ እነሆም፥ አንዲት የገብስ እንጎቻ ወደ ምድያም ሰፈር ተንከባልላ ወረደች፥ ወደ ድንኳኑም ደርሳ እስኪወድቅ ድረስ መታችው፥ ገለበጠችውም፥ ድንኳኑም ተጋደመ ይል ነበር።

14. ፤ ባልንጀራውም መልሶ። ይህ ነገር ከእስራኤል ሰው ከኢዮአስ ልጅ ከጌዴዎን ሰይፍ በቀር ሌላ አይደለም፤ እግዚአብሔር ምድያምንና ሠራዊቱን ሁሉ በእጁ አሳልፎ ሰጥቶአል አለው።

15. ፤ ጌዴዎንም ሕልሙንና ትርጓሜውን በሰማ ጊዜ ሰገደ፤ ወደ እስራኤልም ሰፈር ተመልሶ። እግዚአብሔር የምድያምን ሠራዊት በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአልና ተነሡ አለ።

16. ፤ ሦስቱንም መቶ ሰዎች በሦስት ወገን ከፈላቸው፥ በሁሉም እጅ ቀንደ መለከትና ባዶ ማሰሮ፥ በማሰሮውም ውስጥ ችቦ ሰጠ።

17. ፤ እርሱም። እኔን ተመልከቱ፥ እንዲሁም አድርጉ፤ እነሆም፥ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ በደረስሁ ጊዜ እኔ እንደማደርግ እንዲሁ እናንተ አድርጉ፤

18. ፤ እኔ ከእኔም ጋር ያሉት ሁሉ ቀንደ መለከት ስንነፋ፥ እናንተ ደግሞ በሰፈሩ ዙሪያ ሁሉ ቀንደ መለከታችሁን ንፉ። ለእግዚአብሔርና ለጌዴዎን በሉ አላቸው።

19. ፤ ጌዴዎንም ከእርሱም ጋር የነበሩት መቶ ሰዎች በመካከለኛው ትጋት ትጋቱም በተጀመረ ጊዜ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፤ ቀንደ መለከቶችንም ነፉ፥ በእጃቸውም የነበሩትን ማሰሮች ሰባበሩ።

20. ፤ ሦስቱም ወገኖች ቀንደ መለከቶችን ነፉ፥ ማሰሮችንም ሰበሩ፥ በግራ እጃቸውም ችቦችን፥ በቀኝ እጃቸውም ቀንደ መለከቶችን ይዘው እየነፉ። የእግዚአብሔርና የጌዴዎን ሰይፍ ብለው ጮኹ።

21. ፤ ሁሉም በየቦታው በሰፈሩ ዙሪያ ቆመ፤ ሠራዊቱም ሁሉ ሮጠ፥ ጮኸ፥ ሸሸም።

22. ፤ ሦስቱንም መቶ ቀንደ መለከቶች ነፉ፥ እግዚአብሔርም የሰውን ሁሉ ሰይፍ በባልንጀራውና በሠራዊቱ ሁሉ ላይ አደረገ፤ ሠራዊቱም በጽሬራ በኩል እስከ ቤትሺጣ ድረስ በጠባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልምሖላ ዳርቻ ድረስ ሸሸ።

23. ፤ የእስራኤልም ሰዎች ከንፍታሌምና ከአሴር ከምናሴም ሁሉ ተሰብስበው ምድያምን አሳደዱ።

24. ፤ ጌዴዎንም። ምድያምን ለመገናኘት ውረዱ፥ እስከ ቤትባራም ድረስ ያለውን ውኃ፥ ዮርዳኖስን፥ ያዙባቸው ብሎ መልክተኞችን በኤፍሬም ወዳለው ተራራማ አገር ሁሉ ሰደደ። የኤፍሬም ሰዎችም ሁሉ ተሰብስበው እስከ ቤትባራ ድረስ ውኃውን፥ ዮርዳኖስን፥ ያዙ።

25. ፤ የምድያምን ሁለቱን መኳንንት ሔሬብንና ዜብን ያዙ፤ ሔሬብንም በሔሬብ ዓለት አጠገብ ገደሉት፥ ዜብንም በዜብ መጥመቂያ ላይ ገደሉት፤ ምድያምንም አሳደዱ፥ የሔሬብንና የዜብንም ራስ ይዘው ወደ ዮርዳኖስ ማዶ ወደ ጌዴዎን መጡ።

About መሳፍንት Chapter 7

Read መሳፍንት Chapter 7 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መሳፍንት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: መሳፍንት
Chapter: 7
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መሳፍንት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading መሳፍንት Chapter 7 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is መሳፍንት Chapter 7?

መሳፍንት Chapter 7 is part of the Book of መሳፍንት in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete መሳፍንት Chapter 7 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from መሳፍንት

  1. መሳፍንት Chapter 18
  2. መሳፍንት Chapter 20
  3. መሳፍንት Chapter 19
  4. መሳፍንት Chapter 16
  5. መሳፍንት Chapter 8
  6. መሳፍንት Chapter 6
  7. መሳፍንት Chapter 15

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ኢሳይያስ Chapter 18
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 33
  3. ሕዝቅኤል Chapter 37
  4. ኤርምያስ Chapter 13
  5. ዘፍጥረት Chapter 42
  6. ምሳሌ Chapter 15
  7. ዕዝራ Chapter 5

Related Chapters & Readings

  1. ዘፍጥረት Chapter 27
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 107
  3. ማቴዎስ Chapter 4
  4. ዘኍልቍ Chapter 12
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 56
  6. ሮሜ Chapter 15
  7. ዘዳግም Chapter 27
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *