ዘሌዋውያን Chapter 1

For English

Read ዘሌዋውያን Chapter 1 Online

Read ዘሌዋውያን Chapter 1 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ዘሌዋውያን in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ዘሌዋውያን and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ዘሌዋውያን 1

ምዕራፍ 1

1. እግዚአብሔርም ከመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሙሴን ጠርቶ እንዲህ ሲል ተናገረው።

2. ፤ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራችው። ከእናንተ ማናቸውም ሰው ለእግዚአብሔር መባ ሲያቀርብ መባችሁን ከእንስሳ ወገን ከላሞች ወይም ከበጎች ታቀርባላችሁ።

3. ፤ መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በእግዚአብሔር ፊት እንዲሠምር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል።

4. ፤ እጁንም በሚቃጠለው መሥዋዕት ራስ ላይ ይጭናል፤ ያስተሰርይለትም ዘንድ የሠመረ ይሆንለታል።

5. ፤ በሬውንም በእግዚአብሔር ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን ያቀርባሉ፤ ደሙንም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ባለው በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።

6. ፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ይገፍፈዋል፥ በየብልቱም ይቈርጠዋል።

7. ፤ የካህኑም የአሮን ልጆች በመሠዊያው ላይ እሳት ያነድዳሉ፥ በእሳቱም ላይ እንጨት ይደረድራሉ፤

8. ፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ የተቈረቱትን ብልቶች ራሱንም ስቡንም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ይረበርቡታል፤

9. ፤ የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባል፤ ካህኑም ሁሉን የሚቃጠል መሥዋዕት የእሳት ቍርባን አድርጎ በእግዚአብሔር ዘንድ ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።

10. ፤ ቍርባኑም የሚቃጠል መሥዋዕት ከበጎች ወይም ከፍየሎች ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርበዋል።

11. ፤ በመሠዊያውም አጠገብ በሰሜን ወገን በእግዚአብሔር ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።

12. ፤ በየብልቱም ራሱንም ስቡንም ይቈርጠዋል፤ ካህኑም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ይረበርበዋል፤

13. ፤ የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባል። ካህኑም ሁሉን አቅርቦ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል፤ የሚቃጠል መሥዋዕት የእሳት ቍርባን በእግዚአብሔር ዘንድ ጣፋጭ ሽታ ነው።

14. ፤ ለእግዚአብሔርም የሚቀርበው ቍርባን የሚቃጠል መሥዋዕት ከወፎች ቢሆን፥ ቍርባኑን ከዋኖስ ወይም ከርግብ ያቀርባል።

15. ፤ ካህኑም ወደ መሠዊያው ያቀርበዋል፥ ራሱንም ይቈለምመዋል፥ በመሠዊያውም ላይ ያቃጥለዋል። ደሙም በመሠዊያው አጠገብ ይንጠፈጠፋል፤

16. ፤ የሆድ ዕቃውንም ከላባዎች ጋር ለይቶ በመሠዊያው አጠገብ በምሥራቅ ወገን በአመዱ ስፍራ ይጥለዋል፤

17. ፤ በክንፎቹም ይቀድደዋል፥ ነገር ግን አይከፍለውም። ካህኑም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ያቃጥለዋል፤ የሚቃጠል መሥዋዕት የእሳት ቍርባን በእግዚአብሔር ዘንድ ጣፋጭ ሽታ ነው።

About ዘሌዋውያን Chapter 1

Read ዘሌዋውያን Chapter 1 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ዘሌዋውያን in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ዘሌዋውያን
Chapter: 1
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ዘሌዋውያን. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ዘሌዋውያን Chapter 1 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ዘሌዋውያን Chapter 1?

ዘሌዋውያን Chapter 1 is part of the Book of ዘሌዋውያን in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ዘሌዋውያን Chapter 1 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ብሉይ ኪዳን

  1. አሞጽ Chapter 2
  2. አሞጽ Chapter 7
  3. አሞጽ Chapter 4
  4. አሞጽ Chapter 3
  5. አሞጽ Chapter 9
  6. አሞጽ Chapter 6
  7. አሞጽ Chapter 1

Explore More from ዘሌዋውያን

  1. ዘሌዋውያን Chapter 26
  2. ዘሌዋውያን Chapter 20
  3. ዘሌዋውያን Chapter 4
  4. ዘሌዋውያን Chapter 9
  5. ዘሌዋውያን Chapter 3
  6. ዘሌዋውያን Chapter 12
  7. ዘሌዋውያን Chapter 5

Related Chapters & Readings

  1. የሐዋርያት ሥራ Chapter 7
  2. ሕዝቅኤል Chapter 22
  3. 1 ዜና መዋዕል Chapter 2
  4. ዘዳግም Chapter 7
  5. ዘጸአት Chapter 24
  6. ዘዳግም Chapter 13
  7. ነህምያ Chapter 11
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *