Read ዘሌዋውያን Chapter 9 Online
Read ዘሌዋውያን Chapter 9 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ዘሌዋውያን in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ዘሌዋውያን and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
ዘሌዋውያን 9
ምዕራፍ 9
1. በስምንተኛውም ቀን እንዲህ ሆነ፤ ሙሴ አሮንንና ልጆቹን የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ጠራ።
2. ፤ አሮንንም አለው። ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ከመንጋው እምቦሳውን፥ ስለሚቃጠልም መሥዋዕት አውራውን በግ ነውር የሌለባቸውን ወስደህ በእግዚአብሔር ፊት አቅርባቸው።
3. ፤
4. ፤ የእስራኤልንም ልጆች። ዛሬ እግዚአብሔር ይገለጥላችኋልና ለኃጢአት መሥዋዕት አውራ ፍየልን፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን አንድ ዓመት የሆናቸውን እምቦሳና ጠቦትን፥ ለደኅንነትም መሥዋዕት በሬንና አውራን በግ፥ በዘይትም የተለወሰ የእህልን ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይሠዉ ዘንድ ውሰዱ ብለህ ንገራቸው።
5. ፤ ሙሴም ያዘዛቸውን ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አመጡ፤ ማኅበሩም ሁሉ ቀርበው በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ።
6. ፤ ሙሴም። ታደርጉት ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፤ የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጥላችኋል አለ።
7. ፤ ሙሴም አሮንን። ወደ መሠዊያው ቀርበህ የኃጢአትህን መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን ሠዋ፥ ለራስህና ለሕዝቡም አስተስርይ፤ እግዚአብሔርም እንዳዘዘ የሕዝቡን ቍርባን አቅርብ አስተስርይላቸውም አለው።
8. ፤ አሮንም ወደ መሠዊያው ቀርቦ ስለ ራሱ ኃጢአት መሥዋዕት የሆነውን እምቦሳ አረደ።
9. ፤ የአሮንም ልጆች ደሙን አቀረቡለት፤ ጣቱንም በደሙ ውስጥ ነክሮ የመሠዊያውን ቀንዶች አስነካ፥ ደሙንም ከመሠዊያው በታች አፈሰሰው።
10. ፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ከኃጢአቱ መሥዋዕት ስቡንና ኵላሊቶቹን፥ የጕበቱንም መረብ በመሠዊያው ላይ አቃጠለ።
11. ፤ ሥጋውንና ቁርበቱንም ከሰፈሩ ውጭ በእሳት አቃጠለ።
12. ፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አረደ፤ የአሮንም ልጆች ደሙን አመጡለት፥ እርሱም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ረጨው።
13. ፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በየብልቱ፥ ራሱንም አመጡለት፤ እርሱም በመሠዊያው ላይ አቃጠለው።
14. ፤ የሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም አጠበ፤ በመሠዊያውም በሚቃጠለው መሥዋዕት ላይ አቃጠለው።
15. ፤ የሕዝቡንም ቍርባን አቀረበ፤ ስለ ሕዝቡ ለኃጢአት መሥዋዕት የሆነውን ፍየል ወስዶ አረደው፥ ስለ ኃጢአትም እንደ ፊተኛው ሠዋው።
16. ፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አቀረበ፥ እንደ ሥርዓቱም አደረገው።
17. ፤ የእህሉንም ቍርባን አቀረበ፥ ከእርሱም እፍኝ ሙሉ ወስዶ በጥዋት ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ በመሰዊያው ላይ አቃጠለው።
18. ፤ ስለ ሕዝቡ የሆነውን የደኅንነት መሥዋዕት በሬውንና አውራውን በግ አረደ፤ የአሮንም ልጆች ደሙን አመጡለት፥
19. ፤ በመሠዊያውም ላይ በዙሪያው ረጨው፤ የበሬውንና የአራውንም በግ ስብ፥ ላቱንም፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ ኩላሊቶቹንም፥ የጉበቱንም መረብ አመጡለት።
20. ፤ ስቡንም በፍርምባዎቹ ላይ አደረጉ፥ ስቡንም በመሠዊያው ላይ አቃጠለ፤
21. ፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው አሮን ፍርምባዎቹንና ቀኝ ወርቹን በእግዚአብሔር ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን ወዘወዘው።
22. ፤ አሮንም እጆቹን ወደ ሕዝቡ ዘረጋ ባረካቸውም፤ የኃጢያቱን የሚቃጠለውንም የደኅንነቱንም መሥዋዕት ከሠዋ በኋላ ወረደ።
23. ፤ ሙሴና አሮንም ወደ መገናኛው ድንኳን ገቡ፤ ወጡም፥ ሕዝቡንም ባረኩ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ለሕዝቡ ሁሉ ተገለጠ።
24. ፤ እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጣ፥ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ስቡንም በላ፤ ሕዝቡም ሁሉ አይተው እልል አሉ፥ በግምባራቸውም ወደቁ።
About ዘሌዋውያን Chapter 9
Read ዘሌዋውያን Chapter 9 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ዘሌዋውያን in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: ዘሌዋውያን
Chapter: 9
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ዘሌዋውያን. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading ዘሌዋውያን Chapter 9 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is ዘሌዋውያን Chapter 9?
ዘሌዋውያን Chapter 9 is part of the Book of ዘሌዋውያን in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete ዘሌዋውያን Chapter 9 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from ብሉይ ኪዳን
Explore More from ዘሌዋውያን
- ዘሌዋውያን Chapter 22
- ዘሌዋውያን Chapter 12
- ዘሌዋውያን Chapter 5
- ዘሌዋውያን Chapter 21
- ዘሌዋውያን Chapter 19
- ዘሌዋውያን Chapter 6
- ዘሌዋውያን Chapter 10