ማርቆስ Chapter 7

For English

Read ማርቆስ Chapter 7 Online

Read ማርቆስ Chapter 7 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ማርቆስ in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ማርቆስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ማርቆስ 7

ምዕራፍ 7

1. ፈሪሳውያንና ከጻፎች ወገን ከኢየሩሳሌም የመጡትም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ።

2. ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንድ በርኵስ ማለት ባልታጠበ እጅ እንጀራ ሲበሉ አዩ።

3. ፈሪሳውያንና አይሁድም ሁሉ የሽማግሎችን ወግ ሲጠብቁ እጃቸውን ደኅና አድርገው ሳይታጠቡ አይበሉምና፥

4. ከገበያም ተመልሰው ካልታጠቡ አይበሉም፥ ጽዋንም ማድጋንም የናስ ዕቃንም አልጋንም እንደ ማጠብ ሌላ ነገር ሊጠብቁት የተቀበሉት ብዙ አለ።

5. ፈሪሳውያንም ጻፎችም። ደቀ መዛሙርትህ እንደ ሽማግሌዎች ወግ ስለ ምን አይሄዱም? ነገር ግን እጃቸውን ሳይታጠቡ እንጀራ ይበላሉ ብለው ጠየቁት።

6. እርሱ ግን እንዲህ አላቸው። ኢሳይያስ ስለ እናንተ ስለ ግብዞች። ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤

7. የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ በእውነት ትንቢት ተናገረ።

8. የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ ጽዋን ማድጋንም እንደ ማጠብ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ፥ ይህንም የመሰለ ብዙ ሌላ ነገር ታደርጋላችሁ።

9. እንዲህም አላቸው። ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እጅግ ንቃችኋል።

10. ሙሴ። አባትህንና እናትህን አክብር፤ ደግሞ። አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት ብሎአልና።

11. እናንተ ግን ትላላችሁ። ሰው አባቱን ወይም እናቱን። ከእኔ የምትጠቀምበት ነገር ሁሉ ቍርባን ማለት መባ ነው ቢል፥

12. ለአባቱና ለእናቱ ምንም እንኳ ሊያደርግ ወደ ፊት አትፈቅዱለትም፤

13. ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ እንደዚሁም ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ።

14. ደግሞም ሕዝቡን ጠርቶ። ሁላችሁ እኔን ስሙ አስተውሉም።

15. ከሰው የሚወጡት ሰውን የሚያረክሱ ናቸው እንጂ ከሰው ውጭ የሚገባውስ ሊያረክሰው የሚችል ምንም የለም።

16. የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ አላቸው።

17. ከሕዝቡ ዘንድ ወደ ቤት ከገባ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ምሳሌውን ጠየቁት።

18. እርሱም። እናንተ ደግሞ እንደዚህ የማታስተውሉ ናችሁን? ከውጭ ወደ ሰው የሚገባ ሊያረክሰው ምንም እንዳይችል አትመለከቱምን?

19. ወደ ሆድ ገብቶ ወደ እዳሪ ይወጣል እንጂ ወደ ልብ አይገባምና፤ መብልን ሁሉ እያጠራ አላቸው።

20. እርሱም አለ። ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ያ ነው።

21. ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፥

22. ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና፤

23. ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውን ያረክሰዋል።

24. ከዚያም ተነሥቶ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና አገር ሄደ። ወደ ቤትም ገብቶ ማንም እንዳያውቅበት ወደደ ሊሰወርም አልተቻለውም፤

25. ወዲያው ግን ታናሺቱ ልጅዋ ርኵስ መንፈስ ያደረባት አንዲት ሴት ስለ እርሱ ሰምታ መጣችና በእግሩ ላይ ተደፋች

26. ሴቲቱም ግሪክ፥ ትውልድዋም ሲሮፊኒቃዊት ነበረች፤ ከልጅዋ ጋኔን ያወጣላት ዘንድ ለመነችው።

27. ኢየሱስ ግን። ልጆቹ በፊት ይጠግቡ ዘንድ ተዪ የልጆቹን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባምናአላት።

28. እርስዋም መልሳ። አዎን፥ ጌታ ሆይ፥ ቡችሎች እንኳ ከማዕድ በታች ሆነው የልጆችን ፍርፋሪ ይበላሉ አለችው።

29. እርሱም። ስለዚህ ቃልሽ ሂጂ ጋኔኑ ከልጅሽ ወጥቶአል አላት።

30. ወደ ቤትዋም ሄዳ ጋኔኑ ወጥቶ ልጅዋም በአልጋ ላይ ተኝታ አገኘች።

31. ደግሞም ከጢሮስ አገር ወጥቶ በሲዶና አልፎ አሥር ከተማ በሚባል አገር መካከል ወደ ገሊላ ባሕር መጣ።

32. ደንቆሮና ኰልታፋም የሆነ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፥

33. እጁንም ይጭንበት ዘንድ ለመኑት። ከሕዝቡም ለይቶ ለብቻው ወሰደው፥ ጣቶቹንም በጆሮቹ አገባ እንትፍም ብሎ መላሱን ዳሰሰ፤

34. ወደ ሰማይም አሻቅቦ አይቶ ቃተተና። ኤፍታህ አለው፥ እርሱም ተከፈት ማለት ነው።

35. ወዲያውም ጆሮቹ ተከፈቱ የመላሱም እስራት ተፈታ አጥርቶም ተናገረ።

36. ለማንም አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው እነርሱ ግን ባዘዛቸውም መጠን ይልቅ እጅግ አወሩት።

37. ያለ መጠንም ተገረሙና። ሁሉን ደኅና አድርጎአል፤ ደንቆሮችም እንዲሰሙ ዲዳዎችም እንዲናገሩ ያደርጋል አሉ።

About ማርቆስ Chapter 7

Read ማርቆስ Chapter 7 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ማርቆስ in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ማርቆስ
Chapter: 7
Testament: New Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ማርቆስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ማርቆስ Chapter 7 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ማርቆስ Chapter 7?

ማርቆስ Chapter 7 is part of the Book of ማርቆስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ማርቆስ Chapter 7 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ማርቆስ

  1. ማርቆስ Chapter 10
  2. ማርቆስ Chapter 16
  3. ማርቆስ Chapter 14
  4. ማርቆስ Chapter 8
  5. ማርቆስ Chapter 2
  6. ማርቆስ Chapter 1
  7. ማርቆስ Chapter 13

Explore More from አዲስ ኪዳን

  1. የሐዋርያት ሥራ Chapter 14
  2. ቆላስይስ Chapter 1
  3. ገላትያ Chapter 3
  4. ሉቃስ Chapter 6
  5. 1 ጢሞቴዎስ Chapter 2
  6. 1 ጢሞቴዎስ Chapter 4
  7. ማርቆስ Chapter 10

Related Chapters & Readings

  1. ኤርምያስ Chapter 4
  2. ዘጸአት Chapter 16
  3. ዘኍልቍ Chapter 13
  4. ኢያሱ Chapter 18
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 100
  6. መኃልየ መኃልይ Chapter 8
  7. ሆሴዕ Chapter 7
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *