ሕዝቅኤል Chapter 22

For English

Read ሕዝቅኤል Chapter 22 Online

Read ሕዝቅኤል Chapter 22 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሕዝቅኤል in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ሕዝቅኤል and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ሕዝቅኤል 22

ምዕራፍ 22

1. የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።

2. ፤ አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ትፈርዳለህን? ደም በምታፈስስ ከተማ ላይ ትፈርዳለህን? ርኵሰትዋን ሁሉ አስታውቃት።

3. ፤ እንዲህም በል። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ጊዜሽ እንዲደርስ በመካከልሽ ደምን የምታፈስሺ እንድትረክሺም በራስሽ ላይ ጣዖታትን የምታደርጊ ከተማ ሆይ!

4. ፤ ባፈሰስሽው ደም በድለሻል ባደረግሽውም ጣዖታት ረክሰሻል፤ ቀንሽን አቀረብሽ ዘመንሽንም አሳጠርሽ፤ ስለዚህ ለአሕዛብ መሰደቢያ ለአገሮችም ሁሉ መሳለቂያ አደረግሁሽ።

5. ፤ አንቺ ስምሽ የረከሰ ሽብርም የሞላብሽ ሆይ፥ ወደ አንቺ የቀረቡና ከአንቺ የራቁ ይሳለቁብሻል።

6. ፤ እነሆ፥ የእስራኤል አለቆች እያንዳንዱ እንደ ችሎቱ ደም ያፈስሱ ዘንድ በአንቺ ውስጥ ነበሩ።

7. ፤ በአንቺ ውስጥ አባትንና እናትን አቃለሉ፤ በመካከልሽ በመጻተኛው ላይ በደልን አደረጉ፤ በአንቺ ውስጥ ድሀ አደጉንና መበለቲቱን አስጨነቁ።

8. ፤ ቅድሳቴንም ናቅሽ ሰንበታቴንም አረከስሽ።

9. ፤ ደምን ያፈስሱ ዘንድ ቀማኞች ሰዎች በአንቺ ውስጥ ነበሩ፤ በአንቺ ውስጥ በተራሮች ላይ በሉ፤ በመካከልሽ ሴሰኝነትን አደረጉ።

10. ፤ በአንቺ ውስጥ የአባቶቻቸውን ኀፍረተ ሥጋ ገለጡ፤ በአንቺም ውስጥ አደፍ ያለባትን አዋረዱ።

11. ፤ ሰውም በባልንጀራው ሚስት ርኵሰትን አደረገ፥ አባትም የልጁን ሚስት አረከሰ፥ በአንቺም ዘንድ ወንድም የአባቱን ልጅ እኅቱን አሳፈረ።

12. ፤ በአንቺ ውስጥ ደምን ያፈስሱ ዘንድ ጉቦን ተቀበሉ፤ አንቺም አራጣና ትርፍ ወስደሻል፥ ከባልንጀሮችሽም በቅሚያ የስስትን ትርፍ አገኘሽ፥ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

13. ፤ ስለዚህ፥ እነሆ፥ አንቺ ባደረግሽው ስስት በመካከልሽም በነበረው ደም ላይ እጄን አጨበጨብሁ።

14. ፤ በውኑ እኔ በማደርግብሽ ወራት ልብሽ ይታገሣልን? ወይስ እጅሽ ትጸናለችን? እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ አደርገውማለሁ።

15. ፤ ወደ አሕዛብም እበትንሻለሁ ወደ አገሮችም እዘራሻለሁ፥ ርኵሰትሽንም ከአንቺ ዘንድ አጠፋለሁ።

16. ፤ በአሕዛብም ፊት አንቺ ትረክሻለሽ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂአለሽ።

17. ፤ የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።

18. ፤ የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤል ቤት ለእኔ እንደ አተላ ሆኑብኝ፤ እነርሱ ሁሉ በከውር ውስጥ መዳብና ቈርቈሮ ብረትና እርሳስ ናቸው፤ የብር አተላ ናቸው።

19. ፤ ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ሁላችሁ አተላ ሆናችኋልና ስለዚህ፥ እነሆ፥ በኢየሩሳሌም ውስጥ እሰበስባችኋለሁ።

20. ፤ እንዲያቀልጡት እሳት ያናፉበት ዘንድ ብርንና መዳብን ብረትንና እርሳስን ቈርቈሮንም በከውር እንደሚሰበስቡ፥ እንዲሁ በቍጣዬና በመዓቴ እሰበስባችኋለሁ፥ በዚያም ውስጥ እጨምራችኋለሁ አቀልጣችሁማለሁ።

21. ፤ አሰበስባችሁማለሁ የመዓቴንም እሳት አናፋባችኋለሁ በውስጡም ትቀልጣላችሁ።

22. ፤ ብርም በከውር ውስጥ እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ በውስጡዋ ትቀልጣላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር መዓቴን እንዳፈሰስሁባችሁ ታውቃላችሁ።

23. ፤ የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።

24. ፤ የሰው ልጅ ሆይ። አንቺ ያልነጻሽ በቍጣም ቀን ያልዘነበብሽ ምድር ነሽ በላት።

25. ፤ በውስጥዋ ያሉ ነቢያት እንደሚጮኽና እንደሚናጠቅ አንበሳ አንድ ሆነው ተማማሉ፤ ነፍሶችን በልተዋል፥ ብልጥግናና ሀብትን ወስደዋል፥ በውስጥዋም መበለቶችን አብዝተዋል።

26. ፤ ካህናቶችዋም ሕጌን በድለዋል ቅድሳቴንም አርክሰዋል፤ ቅዱስ በሆነና ቅዱስ ባልሆነ መካከልም አልለዩም፥ በንጹሕና በርኩስ መካከል ያለውን ልዩነት አላስታወቁም፤ ዓይናቸውንም ከሰንበታቴ ሰወሩ እኔም በመካከላቸው ረከስሁ።

27. ፤ በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ የስስትን ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ደምን ያፈስሱ ዘንድ ነፍሶችንም ያጠፉ ዘንድ እንደሚናጠቁ ተኵላዎች ናቸው።

28. ፤ እግዚአብሔርም ሳይናገር ነቢያቶችዋ። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል እያሉ ከንቱን ራእይ በማየት የሐሰትንም ምዋርት ለእነርሱ በማምዋረት ያለ ገለባ በጭቃ ይመርጓቸዋል።

29. ፤ የምድርን ሕዝብ ግፍ አደረጉ ቅሚያም ሠሩ፤ ድሆችንና ችግረኞችን አስጨነቁ፥ መጻተኛውንም በደሉ።

30. ፤ ቅጥርን የሚጠግንን፥ ምድሪቱንም እንዳላጠፋት በፈረሰበት በኩል በፊቴ የሚቆምላትን ሰው በመካከላቸው ፈለግሁ፥ ነገር ግን አላገኘሁም።

31. ፤ ስለዚህ ቍጣዬን አፈሰስሁባቸው፥ በመዓቴም እሳት አጠፋኋቸው፤ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ መለስሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

About ሕዝቅኤል Chapter 22

Read ሕዝቅኤል Chapter 22 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሕዝቅኤል in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ሕዝቅኤል
Chapter: 22
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ሕዝቅኤል. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ሕዝቅኤል Chapter 22 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ሕዝቅኤል Chapter 22?

ሕዝቅኤል Chapter 22 is part of the Book of ሕዝቅኤል in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ሕዝቅኤል Chapter 22 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ሕዝቅኤል

  1. ሕዝቅኤል Chapter 32
  2. ሕዝቅኤል Chapter 18
  3. ሕዝቅኤል Chapter 46
  4. ሕዝቅኤል Chapter 41
  5. ሕዝቅኤል Chapter 36
  6. ሕዝቅኤል Chapter 27
  7. ሕዝቅኤል Chapter 4

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. 2 ዜና መዋዕል Chapter 12
  2. 1 ነገሥት Chapter 22
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 149
  4. ሕዝቅኤል Chapter 25
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 12
  6. ዘጸአት Chapter 24
  7. ዘዳግም Chapter 22

Related Chapters & Readings

  1. አስቴር Chapter 5
  2. 1 ዜና መዋዕል Chapter 17
  3. 2 ነገሥት Chapter 16
  4. ሕዝቅኤል Chapter 45
  5. የሐዋርያት ሥራ Chapter 17
  6. 2 ነገሥት Chapter 11
  7. ኢሳይያስ Chapter 66
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *